loading
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ከደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት አደረጉ::

በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ አንዲሁም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ ከክልሉ የባህል እና ስፖርት እንዲሁም የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ጋር በመሆን የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንትን በሀዋሳ በመገኘት የሲዳማ እና የወላይታ ዲቻ ክለቦች በስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት ጨዋታዎቻቸውን በገለልተኛ ሜዳ […]

በዩሮፓ ሊግ አርሰናል ሲያሸንፍ ቼልሲ ከሜዳው ውጭ ነጥብ ተጋርቷል፡፡

የዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ተካሂደዋል፡፡ እንግሊዝ ምድር ላይ አርሰናል ኤመሬትስ ላይ የስፔኑን ቡድን ቫሌንሲያ አስተናግዶ ከመመራት ተነስቶ ጨዋታውን በ3 ለ 1 ውጤት አሸናፊ ሁኗል፡፡ እንግዳው ቫሌንሲያ ጎል ለማስቆጠር በጨዋታው ጅማሮ ላይ እንቅስቃሴዎችን ያደረገ ሲሆን ተሳክቶለት ፈረንሳያዊው ሙክታር ዲያካቢ በ11ኛው ደቂቃ በጭንቅላቱ የገጫት ኳስ ፒተር ቼክ መረብ ላይ አርፋለች፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ […]

የ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ጀምሮ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ይቀጥላሉ፡፡

የ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ጀምሮ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ይቀጥላሉ፡፡ በፖርቱጋሉ ማርኮ ሲልቫ የሚመራው የመርሲ ሳይዱ ክለብ ኤቨርተን በጉዲሰን ፓርክ የሲን ዳይቹን በርንሊ ምሽት 4፡00 ላይ ይደረጋል፡፡ በነገው ዕለት ደግሞ አምስት ያህል ግጥሚያዎች ሲደረጉ፤ ቀን 8፡30 ቦርንመዝ በዲን ኮርት የማውሪሲዮ ፖቼቲኖውን ቶተንሃም ሆተስፐርን ያስተናግዳል፡፡   ስፐርሶች አሁንም የቀጣይ ዓመት የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፏቸውን ባለማረጋገጣቸው […]

48ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል

ከ1963 ጀምሮ በየዓመቱ ሲካሄድ የነበረው ይህ ውድድር ዘንድሮ ለ48ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከሚያዚያ 29- ግንቦት 4/2011 ዓ/ም በ36 ክለቦችና ተቋማት መካከል ሲደረግ በአጠቃላይ 1376 አትሌቶች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሁሉንም የአትሌቲክስ የውድድር ተግባራት በመካተት የሚካሄድ ይሆናል፡፡   የውድድሩ ዓላማ በአገር ውስጥ የውድድር ዕድል መፍጠር ፤ በክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና ክለቦች እንዲሁም ተቋማት መካከል የአትሌቲክስ […]