loading
በአሜሪካ የጆ ባይደን መመረጥ በአፍሪካ ተስፋንም ጥርጣሬንም ይዞ መጥቷል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 02፣ 2013 በአሜሪካ የጆ ባይደን መመረጥ በአፍሪካ ተስፋንም ጥርጣሬንም ይዞ መጥቷል ተባለ፡፡ ጆ ባይደን አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ዋሽንግተን ከአፍሪካ ጋር ስለሚኖራት ግንኙነት ከወደዲሁ መላ መላ ምቶች ተበራክተዋል፡፡ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የባይደን ወደ ስልጣን መምጣት ለአህጉሪቱ ቀና አመለካት የላቸውም በሚባሉት ዶናልድ ትራምፕ ዘመን የሻከሩ ግንኙነቶች ይስተካከላሉ የሚል ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በተለይ […]

የአልጀሪያው ፕሬዚዳንት የኮቪድ-19 ህክምናቸውን አጠናቀቁ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 07፣ 2013 የአልጀሪያው ፕሬዚዳንት የኮቪድ-19 ህክምናቸውን አጠናቀቁ::ባለፈው ኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ ተመርምረው ቫይረሱ እንዳለበባቸው ያወቁት ፕሬዚዳንት አብደልመጂድ ቲቦኒ ለህክምና ክትትል ወደ ጀርመን ተጉዘው ነበር ተብሏል፡፡ ቲቦኒ ከዚህ በኋላ ተበቤተ መንግስታቸው ሆነው ጨማሪ የህክምና ክትትሎች እንደሚደረጉላቸው ከፕሬዚዳንቱ ቢሮ አስታውቋል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ፕሬዚዳንቱ ያሉበትን ሁኔታ አስመልክተው ለዘህዝቡ መግለጫ እንዲሰጡ ቢሯቸው ወስኗል፡፡ ቲቦኒ […]

የናይጄሪያ ሳይንቲስቶች በዋጋው ርካሽና በፍጥንት ዉጤትን ለማወቅ የሚያስችል የኮቪድ 19 የምርመራ ኪት መስራታቸዉን አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 08፣ 2013 የናይጄሪያ ሳይንቲስቶች በዋጋው ርካሽና በፍጥንት ዉጤትን ለማወቅ የሚያስችል የኮቪድ 19 የምርመራ ኪት መስራታቸዉን አስታወቁ፡፡ ሲኤን ኤን እንደዘገበዉ ሳይኒቲስቶቹ ሰራነው ያሉት አዲሱ የመመርመሪያ ኪት እርካሽና በቀላሉ ማገኘት ሚያስችል ነዉ ፤ዉጤቱንም ከ 40- ደቂቃ ባነሰ ግዜ ዉስጥ ያሳዉቃል፡፡ የመመርመሪያ ኪቱን ዉጤት የሚያሳዉቅ ማሽን አዲስ የተሰራ ሳይሆን ከዚህ በፊት ለኮቪድ 19 መመርመሪያ የሚዉለዉን […]

በአፍሪካ የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ቁጥር ከ2 ሚሊዮን ማለፉ ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 09፣ 2013 በአፍሪካ የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ቁጥር ከ2 ሚሊዮን ማለፉ ተሰማ:: ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ እንዳስታወቀው በአሁኑ ጊዜ በአህጉሩ በወረርሽኙ የተያዙ ሰወች ከ1 ሚሊዮን 986 ሺህ በላይ ደርሰዋል፡፡ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 47 ሺህ 647 መድረሱን የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከለያና መቆጣጠሪያ ማእከል በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡ ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው በበሽታው ከተያዙት […]

የፖፕ ሙዚ አቀንቃኙና ፖለቲከኛው ሮበርት ኪያጉላኒ መታሰሩን ተከትሎ በዩጋንዳ አመፅ ተቀስቅሷል::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2013 የፖፕ ሙዚ አቀንቃኙና ፖለቲከኛው ሮበርት ኪያጉላኒ መታሰሩን ተከትሎ በዩጋንዳ አመፅ ተቀስቅሷል:: በቅፅል ስሙ ቦቢ ዋን በመባል የሚታወቀው ዩጋንዳዊው ፖለቲከኛን መታሰር ለመቃወም አደባባይ በወጡ ደጋፊዎችና የፀትታ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 7 ሰዎች መሞታቸውም ተሰምቷል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ለተቃውሞ አደባባይ ከወጡት ሰዎች መካከል ከ40 በላይ የሚሆኑት የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ ቦቢ ዋይን በዩጋንዳ […]

በቡርኪናፋሶ ምርጫ ፕሬዚዳንት ክርስቲያን ካቦሬ አብላጫ ድምፅ ማግኘት አልቻሉም ተባለ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 በቡርኪናፋሶ ምርጫ ፕሬዚዳንት ክርስቲያን ካቦሬ አብላጫ ድምፅ ማግኘት አልቻሉም ተባለ:: ፕሬዚዳንት ካቦሬ በምርጫው 57.87 በመቶ በሆነ ድምፅ በማግኘት ቢያሸንፉም በቂ የምክር ቤት ወንበር ባለማግኘታቸው መንግስት መመስረት አይችሉም ነው የተባለው፡፡ ፕሬዚዳንቱ የወከሉት ገዥው ፓርቲ ራሱን ችሎ መንግስት ለመመስረት ከጠቅላላው 127 የምክር ቤቱ ወንበሮች መካከል 64ቱን ማግኘት ይጠበቅበት ነበር፡፡ ይሁን እና በፕሬዚዳንት […]

በናይጄሪያ በደረሰ ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ደርሷል ተባለ ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 በናይጄሪያ በደረሰ ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ደርሷል ተባለ :: በአህመድ ላዋን የተመራው የናይጄሪያ ሴኔት ልዑክ፤ በሳምንቱ መጨረሻ በገበሬዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች በተገደሉበት፤ የሰሜን ምስራቅ ቦርኖ ጉብኝት አድርጓል ፡፡ በተፈፀመው ጥቃት 43 አርሶ አደሮች መገደላቸው የተዘገበ ሲሆን ከአከባቢው ባለሥልጣናት ተሻሽለው እየወጡ ያሉ አኃዛዊ መረጃዎች የሟቾች ቁጥር ወደ […]

የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት አዲስ የጥምር ፓርቲ ለመመሰረት መወሰናቸውን ይፋ አደረጉ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት አዲስ የጥምር ፓርቲ ለመመሰረት መወሰናቸውን ይፋ አደረጉ:: ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ሺሴኬዲ ይህን ያሉት በሳቸውና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ፓርቲዎች መካከል አለመግበባት በመፈጠሩ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በፓርላማው ብዙ መቀመጫ ያላቸው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ካቢላ ደጋፊዎችና ሀገሪቱን በመንግስትነት የሚያስተዳድረው የሺሴኬዲ ፓርቲ ፖለቲካዊ ልዩነታቸውን ማስታረቅ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ […]

ሶማሊያ ለኬንያ ዜጎች ፈቅዳው የነበረውን የጉዞ መዳረሻ ቪዛ መከልከሏን ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 ሶማሊያ ለኬንያ ዜጎች ፈቅዳው የነበረውን የጉዞ መዳረሻ ቪዛ መከልከሏን ይፋ አደረገች:: በሁለቱ ሀገራት መካከል በቅርቡ የጠፈጠረው የዲፕሎማሲ መሻከር ነወ ሶማሊያን ለዚህ ወሳኔ ያነሳሳት ተብሏል፡፡ የሶማሊያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ባለስልጣን መስሪያቤት ከዚህ በኋላ ወደ ሶማሊያ የሚጓዙ ኬንያዊያን አስቀድመው ቪዛ ማስመታት ይጠበቅባቸዋል ብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የዲፕሎማሲ ጉዙ የሚያደርጉ ግለሰቦች ሳይቀሩ ከሶማሊያ […]

አመንስቲ ኢንተርናሽናል አረጋዊያንን ከሽብርተኞች ጥቃት መጠበቅ ይገባል የሚል ጥሪ አቀረበ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013  በተለያዩ ሀገራት የሚደርሱ የሽብር ጥቃቶች በእድሜ የገፉ አረጋዊያን ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት ነው ያለው ተቋሙ፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በተለይ እንደ ናይጄሪያ፣ ማሊ፣ እንዲሁም በአብዛኛው የመካከለኛው አፍሪካ ሀገራት ችግሩ ከፋ ነው፡፡ የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ገና ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት የሚያደርሰውን ቦኩ ሃራምን […]