loading
ሱዳናዊያን በሀገሪቱ የስልጣን መጋራት ስምምት የተደረገበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት ሰልፍ አካሂደዋል::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 ሱዳናዊያን በሀገሪቱ የስልጣን መጋራት ስምምት የተደረገበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት ሰልፍ አካሂደዋል:: ነዋሪዎቹ ካርቱም ውስጥ ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ አሁን ባለው የሉዓላዊ ምክር ቤት አስተዳደር ቅሬታ እንደገባቸው ተናግረዋል፡፡ ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት ፕሬዚዳንት አልበሽርን በሃይል ከስልጣናቸው ያስወገዱት ጄኔራሎችና ህዝቡን ወክለው ስልጣን የተጋሩት ፖለቲከኞች ሀገር መምራት ከጀመሩ አንድ ዓመት ቢያስቆጥሩም የተፈለገው ለውጥ አልመጣም በማለት ነው፡፡ […]

የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) አባል ሀገራት መሪዎችም የማሊ ወታደሮች የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠራቸውን አወገዘ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 15፣ 2012 የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) አባል ሀገራት መሪዎችም የማሊ ወታደሮች የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠራቸውን አወገዘ::በወቅታዊ የማሊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባውን ያደረገወ የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ አባል ሀገራት (ኢኮዋስ) የማሊወታደሮች ፕሬዚዳንት ቡበከር ኬታን በቁጥጥር ስር አውሎ የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠራቸውን አወገዟል፡፡ ኢኮዋስ በትላንትናው ዕለት ባደረገው የቪድዮ ስብሰባ ፕሬዝዳንቱ ቡበከር ኬታና በእስር የሚገኙ ባለስልጣናት […]

ሱዳን ከዓለም ዓቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አይ ሲ ሲ ጋር በጦር ወንጀሎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማማች፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 18፣ 2012 ሱዳን ከዓለም ዓቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አይ ሲ ሲ ጋር በጦር ወንጀሎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማማች፡፡ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሃምዶክ ዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሱዳን ዳርፉር ተከስቶ በነበረው ግጭት የጦር ወንጀሎችንና የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የፈጸሙትን አካላት ለፍርድ ለማቅረብ በሚደረገው ሂደት በትብብር እንሰራለን ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር […]

ከአፍሪካ ፖሊዮ ቫይረስ በመጥፋቱ የጤና ሚኒስትሯ የእንኳን ደስላችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 20፣ 2012 ከአፍሪካ ፖሊዮ ቫይረስ በመጥፋቱ የጤና ሚኒስትሯ የእንኳን ደስላችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡ የአለም ጤና ድርጅት አፈሪካ ከፖሊዮ ነጻ መሆንዋን መግለጹን ተከተሎ ነዉ ፖሊዮን ለማጠፋት ለሰሩት የጤና ባለሞያዎች ለማህበረሰብ መሪዎች እና አባላት ወላጆችና አሳዳጊዎች እነዲሆም ለአጋር አካላት በሙሉ እንኳን ደስ አለን ብለዋል፡፡ አፍሪካ የዋይልድ ፖሊዮ ቫይረስ መጥፋት ማረጋገጫ የሆነዉን የምስክር ወረቅ መቀበሏንም ዶክተር ሊያ […]

የአንጎላ ፖሊሶች የኮሮና ቫይረስ ገደብን በተላለፉ ሰዎች ላይ በወሰዱት እርምጃ የ7ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 20፣ 2012 የአንጎላ ፖሊሶች የኮሮና ቫይረስ ገደብን በተላለፉ ሰዎች ላይ በወሰዱት እርምጃ የ7ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ፖሊሶች በተጠቀሙት ያልተገባ ሀይል ከሞቱት ዉስጥ ወጣቶችና አፍላ እድሜ ላይ የነበሩ ታዳጊዎችም ይገኑበታል፡፡ ለኮሮና ቫይረስ የተቀመጠዉን ገደብ ተላለፈዉ በመገኘታቸዉ በፖሊስ ተተኩሶባቸዉ መገደላቸዉ ነዉ የተሰማዉ ፡፡ ድርጊቱን በተመለከተ የዓለም አቀፍ መብት ተማጓቹ አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ሰዎች እንዳይሞቱ የዓለም […]

ኬንያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የጣለችው የሰዓት እላፊ ገደብ ለተጨማሪ አንድ ወር አራዘመች::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 21፣ 2012 ኬንያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የጣለችው የሰዓት እላፊ ገደብ ለተጨማሪ አንድ ወር አራዘመች::የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በመግለጫቸው እንዳሉት በዚህ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የምት ከለቦችና መጠጥ ቤቶች ዝግ እንደሆኑ ይቆያሉ፡፡ በሰርግ፣ በቀብር ስነ ስርዓቶችና በሌሎችም ሁነቶች ላይ የሚገኙ ሰዎች ግን ቁጥራቸው ካልበዛና እርቀታቸውን እስከጠበቁ ድረስ አይከለከሉም ነው የተባለው፡፡ ኬንያታ ምንም እንኳ በሀገራችን የቫይረሱ […]

የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት ቡበከር ኬታ ታው ሆስፒታል ገብተዋል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 28፣ 2012  የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት ቡበከር ኬታ ታው ሆስፒታል ገብተዋል ተባለ:: በመፈንቅለ መንግስት መካሄዱን ተከትሎ ለ10 ቀናት በወታደራዊ ጁንታው ቁጥጥር ስር የነበሩት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ በተለቀቁ በጥቂት ቀናት ውስጥ ነው ሀኪም ቤት የገቡት፡፡ አሶሼትድ ፕሬስ በዘገባው እንዳስነበበው የፕሬዚዳንቱ የጤና ሁኔታ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እስካሁን የተብራራ መረጃ የለም፡፡ ኤን 5 የተሰኘው የሀገሪቱ ተቃዋሚ […]

የሊቢያ የሰላም ጥሪ

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 29፣ 2012 ግብፅ የሊቢያ የሰላም ጉዳይ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪ አቀረበች:: የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ ካይሮ የትኛውንም የተኩስ አቁም ስምምነትና የሰላም ድርድር ሂደት ለመደገፍ ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡ ሽኩሪ ከአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳዮች ፖሊሲ ከፍተኛ ልዑክ ጆሴፍ ቦሬል ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው ይህን ያሉት፡፡ በእርስ በርስ ጦርነት የምትታመሰው […]

የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ለህክምና ወደ አቡዳቢ መጓዛቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2012 የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ለህክምና ወደ አቡዳቢ መጓዛቸው ተሰማ:: በቅርቡ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተባረሩት ኬታ ህክምናቸውን ለመከታተል ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች መጓዛቸውን የቀድሞው የጦር አዛዣቸው ማማዱ ካማራ ተናግረዋል፡፡ ለአስር ቀናት ያህል በወታራዊ ጁንታው ቁጥጥር ስር የነበሩት ኬታ ባማኮ ውስጥ በሚገኝ አንድ የግል የህክምና ተቋም የጤናቸውን ሁኔታ ሲከታተሉ […]