የ2011 የአለም የወባ ቀንን በማስመልከት የተዘጋጀው ፕሮግራም በድሬደዋ ተጀመረ
የ2011 የአለም የወባ ቀንን በማስመልከት የተዘጋጀው ፕሮግራም በድሬደዋ ተጀመረ። በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት ሰለሞን እንደገለፁት በአለም አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የወባ ማጥፋት ዘመቻ የተቀላቀለችው ኢትዮጵያ በስድስት ክልሎችና 239 ወረዳዎች የዘረጋችው መርሀ ግብር ውጤታማ መሆኑ ተነግሯል የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ፉአድ ከድር በበኩላቸው ከአሁን ቀደም በድሬደዋ ነዋሪዎች በእለት ተእለት ኑሮ […]
አዲስ አበባ ዘመናዊ ቤተ መፅሐፍት ለገነባላት ነው
አዲስ አበባ ዘመናዊ ቤተ መፅሐፍት ለገነባላት ነው። የቤተ-መፅሐፍት ግንባታው አራት ኪሎ ከፓርላማ ፊትለፊት ከአርበኞች ህንፃ ጎን የሚገነባ ሲሆን በ38,687 ካሬ ሜትር ላይ ያርፋል ተብሏል፡፡ በአንድ ጊዜ 3ሺህ 500 ሰው የማስተናገድ አቅም ያለውና በቀን እስከ 10,000 ሰው መቀበል የሚችለው ማዕከሉ ለህፃናት እና አዋቂዎች የሚሆን የማንበቢያ እና የአረንጓዴ ስፍራ አለው ነው የተባለው፡፡ እንደ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ገለፃ […]
አዲስ የተቋቋመው የጉሙሩክ ፖሊስ ስራ ጀመረ
አዲስ የተቋቋመው የጉሙሩክ ፖሊስ ስራ ጀመረ ኮንትሮባንድንና ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተቋቋመው የጉምሩክ ፖሊስ ስራ መጀመሩ ተገለፀ፡፡ ኮንትሮባንድን መከላከል ዋነኛ ተግባሩ መሆኑ የተነገረው ይኸው የጉሙሩክ ፖሊስ ተጠሪነቱ ለፌዴራል ፖሊስ መሆኑም ተነግሯል፡፡ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮንትሮባንድ ፖሊስ ዳይሬክቶሬትን ለማቋቋም የሚያስችል የስምምነት ሰነድ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና በጉሙሩክ ኮሚሽን መካከል ተፈርሟል። በጉምሩክ የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ቀደም ሲል ሌሎች […]
የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣን የሚያስረክብበትን ቀነ ገደብ አራዘመ፡፡
የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣን የሚያስረክብበትን ቀነ ገደብ አራዘመ፡፡ የአፍሪካ መሪዎች በሱዳን እና በሊቢያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር ካይሮ ላይ በተገናኙበት ወቅት ነው ውሳኔው የተላለፈው፡፡ ህብረቱ ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ ወታደራዊ ምክር ቤቱ በ15 ቀናት ውስጥ ስልጣኑን ለሲቪል የሽግግር መንግስት እንዲያስረክብ ይህ ባይሆን ግን ሱዳን ከህብረቱ እንደምትባረር አስጠንቅቆ ነበር፡፡ የግብፁ የዜና ወኪል ሜና […]