loading
በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በሃይማኖት ተቋማት መካከል ስመምነት ተፈረመ

የሀይማኖት ተቋማት ለዜጎች በተናጥል የሚያደርጉትን ድጋፍ ውጤት በሚያመጣ መልኩ ለማቀናጀት የሚያስችል ነው የተባለ የመግባቢያ ስምምነት በሃይማኖት ተቋማትና በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተፈረመ። ሚኒስቴር መስሪያቤቱና  የሃይማኖት ተቋማት አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችን እና ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ጋር መፈራረማቸውን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ስምምነቱ ለማህበራዊ እና […]

“ሃገሪቷ ያሏት ቅርሶች ብዛት ከእንክብካቤ እና እድሳት አቅም በላይ ነው” – ዶክተር ሂሩት ካሳው

በኢትዮጵያ ቅርሶችን ለመጠገን እና ለማደስ አስቸጋሪ የሆነው  ሃገሪቱ ያሏት ቅርሶች ብዛት ካላት የመንከባከብ  አቅም ጋር ስላልተመጣጠነ መሆኑን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው ተናገሩ። ሚኒስትሯ ይህን ያሉት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ለመወጣት ያደረገውን ጥረት እና የገጠሙትን ችግሮች በሚመለከት ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡ ዶ/ር ሂሩት በመግለጫቸው በሀገራችን የቅርሶች ቁጥር […]

የሴቶችን ተጠቃሚነት እና እኩልነትን ለማረጋገጥ የተቀናጀና ትብብርን መሰረት ያደረገ እንቅስቃሴ” ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ

በኢትዮጵያ የሴቶችን ተጠቃሚነት እና እኩልነትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ የተቀናጀና ትብብርን መሰረት ያደረገ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አስገነዘቡ። “መተባበር ለላቀ ውጤት” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው እና በሥርዐተ ጾታ እኩልነት እና ሴቶችን በማብቃት ዙሪያ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የውይይት መድረክ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ አዳራሽ ዛሬ ረፋድ ላይ ሲጀመር ፕሬዚዳንቷ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተፈጠረውን መልካም […]

በጅግጅጋ ቶጎ ውጫሌ የአሜሪካ ዶላርና ጥይቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጅግጅጋ ቶጎ ውጫሌ የአሜሪካ ዶላርና ጥይቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ ተባለ፡፡ ከገቢዎች ሚኒስቴር  እንዳገኘነው መረጃ ለዛሬ አጥቢያ ከሌሊቱ 9 ሰዓት ሲሆን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-50322 ኦሮ በሆነ ተሽከርካሪ 39 ሺ 700 ዶላር ይዞ ወደ ውጪ ሃገር ሊያስወጣ የነበረ ግለሰብ በቶጎ ውጫሌ የኬላ ተቆጣጣሪዎች ሊያዝ ችሏል ፡፡ ግለሰቡ ዶላሩን በጥቁር ፕላስተር ከጠቀለለ […]

በአፍሪካ ታዳጊዎች እና ወጣቶች ውድድር ላይ 4ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አቀባበል እና ሽልማት ተበረከተለት

በኮትዲቯር አስተናጋጅነት ከሚያዝያ 8-12/2011 ዓ.ም በተከናወነው የአፍሪካ ከ – 18 እና ከ – 20 አመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በሁለቱም የእድሜ እርከኖች 82 አትሌቶችን ጨምሮ 111 ልኡካንን በመያዝ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ስድስት ወርቅ ፤ አስር ብር እና አስራ አራት ነሀስ በማምጣት በድምሩ 30 ሜዳሊያዎችን በማሳካት ፤ ከዉድድሩ ተሳታፊ ሀገራት በአጠቃላይ ሜዳሊያ ብዛት 4ኛ ደረጃን በመያዝ […]

ለ5 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዞ የአሻራ ምርመራ አገልግሎት ተጀመረ

ለ5 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዞ የአሻራ ምርመራ አገልግሎት ተጀመረ። ለ5 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዞ የፎረንሲክ ምርመራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ አገልግሎቱን  ሚያዚያ 14/2011 ጀምሮ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡ አገልግሎቱ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት ተቋርጦ የነበረው የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዞ በሰራተኛና […]

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የኤሌክትሪክ ሀይል ለማቅረብ የሚያስችል የ264 ሚሊየን ዶላር ብድር ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የኤሌክትሪክ ሀይል ለማቅረብ የሚያስችል የ264 ሚሊየን ዶላር ብድር ስምምነት ተፈራረሙ ። ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የ264 ሚሊየን ዶላር ቀላል ብድር ማቅረብ የሚያስችል የማዕቀፍ ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን የደቡብ ኮሪያ ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ እና የገንዘብ ሚኒስቴር የተፈራረሙ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚከናወኑ የልማት ፕሮክቶች የሚውል ነው ተብሏል። የመጀመሪያው የ170 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት በደቡብ ኢትዮጵያ ለሚገኘው […]