loading
በደቡባዊ ምስራቅ የህንድ ግዛቶች የተከሰተው አውሎ ንፋስ በርካታ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ ጥሏል::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2013 በደቡባዊ ምስራቅ የህንድ ግዛቶች የተከሰተው አውሎ ንፋስ በርካታ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ ጥሏል:: ሳይክሎን ኒቫር በመባል የሚታወቀው አውሎ ንፋስ በደቡብ ምስራቅ ህንድ በሚገኙ ሶስት ግዛቶች በፍጥነት እየገሰገሰ መሆኑን ተከትሎ ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል፡፡ ሰዎች በአደባባይ እንዳይሰባሰቡና ተጨማሪ መመሪያዎች እስኪተላለፉላቸው ድረስ በጥንቃቄ እንዲቆዩ የአካባቢው ባለስልጣናት አስጠንቅቀዋል ነው የተባለው፡፡ አደጋው ሊያደርስ የሚችልውን […]

ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ በአሜሪካ በቅርቡ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ሊባባስ እንደሚችል አስጠነቀቁ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ በአሜሪካ በቅርቡ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ሊባባስ እንደሚችል አስጠነቀቁ:: ዶክተር ፋውቺ ይህን አስተያየት የሰጡት አሜሪካዊያን ሰሞኑን ያከበሩትን የምስጋና ቀን በማስታወስ ነው፡፡ ፋውቺ በሰጡት መግለጫ በዓሉን ለማክበር ከቤታቸው ውጭ ጉዞ ያደረጉ አሜሪካዊያን እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ከሆኑ አዛውንቶችን እንዳይጎበኙ አሳስበዋል፡፡ በዓሉን ለመታደም ከ26 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን አየር መንገዶችን አጨናንቀው እንደነበር […]

የተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶክተር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 የተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶክተር ስኮት አትላስ የስራ መልቀቂያ አስገቡ፡፡ የፕሬዜዳንቱ የኮሮናቫይረስ ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶክተር ስኮት አትላስ በገዛ ፈቃዳቸውን ስራ መልቀቃቸውን የዋይት ሃውስ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ የኮቪድ 19 በመከላከል ዙሪያ ከተቀሩት የግብረ ሃይል አባላት ጋር አራት ወራትን ከፈጀ ንትርክ በኋላ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ነው የተነገረው፡፡የአትላስ […]

የኒውዚ ላንዷ ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደርን በክሪስት ቸርች የጅምላ ግድያ ህዝባችውን ይቅርታ ጠየቁ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 የኒውዚ ላንዷ ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደርን በክሪስት ቸርች የጅምላ ግድያ ህዝባችውን ይቅርታ ጠየቁ:: ጠቅላይ ሚኒስትሯ ይቅርታ የጠየቁት ብሪንተን ታራንት የተባለው ትውልደ አውስትራሊያዊ ወጣት ያደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋ ከጦር መሳሪያ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር የተያያዘ ስህተት ነበር በማለት ነው፡፡ የሀገሪቱ የወንጀል መርማሪ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ፖሊስ ግለሰቡ የጦር መሳሪያ ፈቃድ ሲሰጠው አስፈላጊውን ማጣራት […]

ቤናሚን ኔታኒያሁ በፓርቲያቸው ውስጥ አዲስ የስልጣን ተቀናቃኝ ግለሰብ ተነስቶባቸዋል::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 ቤናሚን ኔታኒያሁ በፓርቲያቸው ውስጥ አዲስ የስልጣን ተቀናቃኝ ግለሰብ ተነስቶባቸዋል:: በጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያ የሚመራው የሊኩድ ፓርቲ ሁነኛ ሰው የሆኑት ጌዲዮን ሳር ራሳቸውን ከፓርቲው ማግለላቸውን አስታውቀዋል፡፡ ለዚህ ምክንያታቸው ደግሞ ኔታኒያሁ ከሀገራቸው ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ያስቀድማሉ ስለዚህ ከሳቸው ጋር መስራት አልፈልግም የሚል ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት የምርጫ ተቀናቃኛቸው የነበሩትና አብረዋቸው የጥምር መንግስት የመሰረቱት […]

አሜሪካ ከሩሲያ የሚሳኤል መከላከያ ሲስተም ገዝታለች በሚል ምክንያት በቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 06፣ 2013 አሜሪካ ከሩሲያ የሚሳኤል መከላከያ ሲስተም ገዝታለች በሚል ምክንያት በቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች:: የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ቱርክ ከሩሲያ የገዛችው የሚሳኤል መከላከያ ስርዓት ለአሜሪካ ደህንነት ስጋት መሆኑን ደጋግመን ነግረናት ነበር ብለዋል፡፡ ዋሽንግተን ያሳለፈችው ውሳኔ የቱርክን ወታራዊ አቅም የማዳከም ሳይሆን የራሷን ደህንነት የማስጠበቅ ነው በማለትም አክለዋል ፖምፒዮ፡፡ ቱርክ ባለፈው ጥቅምት ወር […]

አዲሱ ተገኘ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ለዓለም ሀገራት ስጋት እየሆነ ነው ተባለ ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013 አዲሱ ተገኘ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ለዓለም ሀገራት ስጋት እየሆነ ነው ተባለ :: በዚህም አዲሱ ቫይረስ በመጀመሪያ  ታይቷል ከተባለበት ከእንግሊዝ ወደ ተለያዩ አገራት የሚደረጉ በረራዎችን ታግደዋል። የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት በዚህ ዙሪያ የጋራ ፖሊሲ ለማውጣት እየተወያዩ ነው የተባለው፡፡ ሲሆን ዴንማርክ ውስጥም አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በመታየቱ ስዊድን ወደ ዴንማርክ የሚደ ረገዉንም ጉዞ አግዳለች። የወረርሽኙ […]

እስራኤል በሁለት ዓመት ውስጥ አራተኛ ምርጫ ማካሄዷ የግድ ሆኖባታል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013 እስራኤል በሁለት ዓመት ውስጥ አራተኛ ምርጫ ማካሄዷ የግድ ሆኖባታል ተባለ:: የጠቅላይ ሚንስትር ቤናሚን ኔታኒያሁና የአጣማሪያቸው ቤኒ ጋንትዝ የአንድነት መንግስት በገጠመው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ድንገቴ ምርጫ የማካሄድ ግዴታ ውስጥ ገብቷል፡፡ ባለፉት ሳምንታት የሀገሪቱ ምክር ቤት ፈርሶ አዲስ ምርጫ ይካሄድ የሚል ሀሳብ በህግ አውጭ አባላት መቅረቡን ተከትሎ ፓርላማው ፈርሷል ነው የተባለው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ምርጫው […]

በእንግሊዝና ፈረንሳይ መካከል ተጥሎ የነበረው የጉዞ እገዳ መነሳቱን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ዳግም ተጀምሯል፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013 በእንግሊዝና ፈረንሳይ መካከል ተጥሎ የነበረው የጉዞ እገዳ መነሳቱን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ዳግም ተጀምሯል፡፡ በእንግሊዝ አዲሱ የኮሮናቫይረስ በመከሰቱ በርካታ ሀገራት የጉዞ እቀባ መጣላቸውን የሚታወስ ሲሆን ፈረንሳይም አንዷ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ አሁን ላይ ሀገራቱ በደረሱት ስምምነት መሰረት በእንግሊዝና ፈረንሳይ መካከል የሚደረጉ የባቡር ፣የአየርና የባህር ጉዞዎች ዳግም እንደሚጀመሩ ነው የተነገረው፡፡ የፈረንሳይ ዜጎችና በፈረንሳይ የሚኖሩ የእንግሊዝ […]

እስራኤል በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 በጋዛ ሰርጥ 300 ጥቃቶችን መፈፀሟን ይፋአደረገች::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 እስራኤል በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 በጋዛ ሰርጥ 300 ጥቃቶችን መፈፀሟን ይፋአደረገች:: የሀገሪቱ መከላከለያ ተቋም ባወጣው መግለጫ በአካባቢው በተመረጡ 300 ኢላማዎችላይ ጥቃት ማድረሱንና 38 የጥቃት ሙከራዎችን ማክሸፉን ተናግሯል፡: ከጋዛ በኩል 176 ሮኬቶች ተተኩሰውብን ነበር ያለው የእስራኤል ጦር ሃይል ከነዚህ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት ባዶ ሜዳ ላይ ነው ያረፉት ብሏል፡፡ በሪፖርቱ እንደተገለፀው የእስራኤል ተዋጊ […]