loading
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከህመማቸው አገግመው በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ስራ ይመለሳሉ ተባለ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከህመማቸው አገግመው በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ስራ ይመለሳሉ ተባለ:: በቤተ መንግስታቸው ተወሽበው የከረሙት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኮሮናቫይረስ ማገገማቸውን ሀኪሞቻቸው ተናግረዋል፡፡ በመጀመሪያ በዋይት ሀውስ ቀጥሎም በወታደራዊ ሆስፒታል ህክምናቸውን የተከታተሉት ትራምፕ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ጊዜየን ማጥፋት አልፈልግም የምጫ ክርክሬን በፊት ለፊት ማድረግ እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ […]

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ተቀናቃኝ ሀይሎች ቅድሚያ ለሀገር ሰጥተው እንዲስማሙ ጠየቀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ተቀናቃኝ ሀይሎች ቅድሚያ ለሀገር ሰጥተው እንዲስማሙ ጠየቀ:: ድርጅቱ በሁለት ጎራ ተከፍለው ጦርነት ውስጥ የገቡት ወገኖች ከራሳቸው ይልቅ ቅድሚያ ለሀገራቸውና ለህዝቡ በመስጠት እርቀ ሰላም እንዲያወርዱ ነው ያሳሰበው፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ተጠባባቂ ልዩ ልኡክ ስቴፋኒ ዊሊያምስ በድርድሩ ወቅት ከራስ የፖለቲካ አከንዳ ይልቅ የሀገሩን ጉዳይ የሚያስቀድም ተወያይ እንጠብቃለን […]

ዓለም ባንክ ለታዳጊ ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባት ግዢ የሚውል 12 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 ዓለም ባንክ ለታዳጊ ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባት ግዢ የሚውል 12 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ::የባንኩ ዳሬክተሮች ቦርድ ይፋ ባደረገው መሰረት ለታዳጊ ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባት ግዢና ለዜጎቻቸው ምርመራና እንክብካቤ የሚውል 12 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አጽድቋል የገንዘብ ድጋፉ ለአንድ ቢሊዮን ሰዎች ክትባት ማዳረስ የሚያስችል ሲሆን የዓለም ባንክ እስከ ፈረንጆቹ […]

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልጅ ባሮን ትራምፕ በኮሮናቫይረስ መያዙ ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2013 የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልጅ ባሮን ትራምፕ በኮሮናቫይረስ መያዙ ተሰማ:: ከሁለት ሳምንት በፊት ከባለቤታቸው ጋር ጋር በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ማቆያ የሰነበቱት ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ የልጃቸውን በበሽታው መያዝ ይፋ አድርገዋል፡፡ የ14 ዓመቱ ባሮን ትራምፕ ተመርምሮ የመጀመሪያ ውጤቱ ኔጌቲቨ እንደነበር የገለፁት ቀዳማዊት እመቤቷ እኔና ባለቤቴ በበሽታው መያዛችንን ሳውቅ ስለልጃችን አብዝቸ ስጨነቅ ነበር […]

ጣሊያን የኮሮናቫይረስ ስርጭት መባባሱን ተከትሎ የእንቅስቃሴ ገደቦችን መጣል ጀመረች::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2013 ጣሊያን የኮሮናቫይረስ ስርጭት መባባሱን ተከትሎ የእንቅስቃሴ ገደቦችን መጣል ጀመረች:: ፕሬዚዳንት ጁሴፔ ኮንቴ በሀገራቸው ዳግም የተስፋፋውን የኮቪድ-19 ስርጭት ለመግታት ሁለተኛው ዙር የእንቅስቃሴ እቀባ እንደሚያስፈልግ በአፅንዖት ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ ከተሞች ከንቲባዎች ህዝብ በብዛት የሚስተናገድባቸውን አካባቢዎች ለደህንት ሲባል አንዲዘጉ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል ነው የተባለው፡፡ ጣሊያን ይህን እምጃ ለመውሰድ የተገደደችው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎቿ እንደ አዲስ […]

እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች አዳዲስ ስምምነቶችን ተፈራረሙ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013  እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች አዳዲስ ስምምነቶችን ተፈራረሙ::በቅርቡ የዲፕሎማሲ ስምምነት ያደረጉት ሁለቱ ሀገራት ያለ ቪዛ ጉዞዎችን መፍቀድን ጨምሮ አራት የሚሆኑ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል ነው የተባለው፡፡ሌሌቹ የስምምነት ዘርፎች ደግሞ የአቬሽን ኢንዱስትሪ፣ የኢኮኖሚ ትብብር እና ኢንቨስትመንትን የተመለከቱ ናቸው፡፡ አልጀዚራ እደዘገበው ቴል አቪቭ እና አቡዳቢ በቅርቡ የጀመሩት የዲፕሎማሲ ግንኙነት በፍጥነት መሻሻል እየታየበት ነው፡፡ሁለቱ ሀገራት […]

በአየር ብክለት ምክንያት ከ400 ሺህ በላይ ህፃናት ህይዎታቸው ማለፉን አንድ ጥናት አመለከተ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013በፈረንጆቹ 2019 በአየር ብክለት ምክንያት ከ400 ሺህ በላይ ህፃናት ህይዎታቸው ማለፉን አንድ ጥናት አመለከተ::ሄልዝ ኢፌክት ኢንስቱትዩት የተባለ ተቋም እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2019 በዓለማችን 476 ሺህ ጨቅላ ህፃናት የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ችግር ሳቢያ ህይዎታቸው ማለፉን በጥናት አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ከነዚህ የችግሩ ሰለባ ከሆኑት ህፃናት መካከል አብዛኞቹ ከህንድና ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው […]

በፈረንሳይ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በአንድ ሳምንት ውስጥ በ40 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 በፈረንሳይ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በአንድ ሳምንት ውስጥ በ40 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተባለ::በመላው አውሮፓ እንደ አዲስ እየተስፋፋ የመጣው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ፈረንሳይንም ከፍተኛ ስጋት ለይ ጥሏታል፡፡ የፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂያን ካንቴክስ በሰጡት መግለጫ ችግሩ በጠቅላላው አውሮፓም በሀገራችንም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡የወረርሽኙ ስርጭት ያሳሰባት ፈረንሳይ በተመረጡ አካባቢዎች የሰአት እላፊ ገደቦችን ለመጣል ተገዳለች፡፡ዩሮ […]

ስፔን የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ብሄራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የሰዓት እላፊ ገደቦችን ደነገገች::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 ስፔን የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ብሄራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የሰዓት እላፊ ገደቦችን ደነገገች::የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቸዝ ለመነሻነት ለ15 ቀናት የተጣለው ድንጋጌ ለስድት ወራት እንዲራዘም ፓርላማቸዉን እንደሚጠይቁ ተናግረዋል፡፡በተለያዩ ግዛቶች የተጣሉት የምሽት ጊዜ የሰዓት እላፊ ገደቦች እንደአስፈላጊነቱ ሊያጥሩና ሊረዝሙ አንደሚችሉ ነው የተነገረው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው አዲሱ የስፔን የእንቅስቃሴ እቀባ በግልም ሆነ በመንግስት […]

በፓኪስታንዋ ፔሻወር ከተማ በትምህርት ቤት ዉስጥ በደረሰ ፍንዳታ 7 ሰዎች ሞቱ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013 በፓኪስታንዋ ፔሻወር ከተማ በትምህርት ቤት ዉስጥ በደረሰ ፍንዳታ 7 ሰዎች ሞቱ::ከሞቱት መካከልም አራቱ ህጻናት ናቸዉ ተብሏል::በቢሲ እንደዘገባዉ ፖሊስ በሀይማኖታዊ ትምህርትቤቱ በደረሰዉ ጥቃትም ከ50 በላይ ሰዎች መቁሰላቸዉን ገልጿል:: የሆስፒታል ምንጮች እንደገለጹት ወደ ሆስፒታሉ ቆስለዉ እና ህይወታቸዉ አልፎ የመጡ ሰዎች በፍንዳታ የተጎድ እንደሆኑ አረጋግጧል በጥቃቱ ህይወታቸዉ ካለፉት አራት ህጻናት በተጨማሪ ሌሎቹ ከ20 […]