loading
የእንጦጦ ሀመረ ኖህ ኪዳነምህረት አካባቢ ተወለጆች በአካባቢያቸው ለሚገኙ  አቅመ ደካሞች  የምግብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 የእንጦጦ ሀመረ ኖህ ኪዳነምህረት አካባቢ ተወለጆች በአካባቢያቸው ለሚገኙ  አቅመ ደካሞች  የምግብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ::   የእንጦጦ ሀመረ ኖህ ኪዳነምህረት አካባቢ ተወለጆች   የኮቪድ 19 በሽታ ወረርሽኝ  የሚያስከትለውን  ችግር ለመከላከል በአካባቢያቸው ለሚገኙ  ከ 3 መቶ በላይ  ለሚሆኑ ድጋፍ ፈላጊዎች   የምግብና የአይነት ድጋፍ ማድረጋቸውን የወጣቶቹ አስታባበሪ አቶ  አሳልፈው ጌትነት   ገልፀዋል፡፡  እነዚህ ወጣቶች ለወገናቸው […]

የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚጠቅሙ ተብሎ በጤና ባለሙያዎች የተለዩ ምግቦች እንደሌሉ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚጠቅሙ ተብሎ በጤና ባለሙያዎች የተለዩ ምግቦች እንደሌሉ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ:: የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ለመከላከልና ከበሽታው የሚያድኑ ተብሎ እስካሁን በጤና ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ ተመሥርተው የቀረቡ የተለዩ የምግብ ዓይነቶች አለመኖራቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ገለጹ።ኅብረተሰቡ አሁንም በመንግሥትና በጤና ባለሙያዎች የሚቀርቡለትን መመሪያዎች ተግባራዊ በማድረግ ከቫይረሱ ራሱንና ወገኑን መከላከል እንደሚገባው […]

ስፔን ከሶስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ ሰው ሳይሞትባት 24 ሰዓታት ተቆጥረዋል::

ስፔን ከሶስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ ሰው ሳይሞትባት 24 ሰዓታት ተቆጥረዋል:: በስፔን የኮሮናቫይረስ እንደከተሰተ የመጀመሪያው ሞት በፈረንጆቹ ማርች 3 ቀን ነበር የተመዘገበው፡፡ቀስበቀስ የበሽታው ስርጭት እየተስፋፋ መጥቶ ስፔን በርካታ ዜጎቿን በቫይረሱ ምክንያት አጥታለች፡፡ አልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው በሀገሪቱ ታሪክ በ24 ሰዓታት ውስጥ በጣም ከፍተኛው የሞት መጠን 950 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የሀገሪቱ የአስቸኳይ የጤና ጉዳዮች ምላሽ ሀላፊ ፌርናንዶ […]

ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ድጋፍ የሚውል ከ500 ሺህ በላይ ማስክና የገንዘብ ድጋፍ ተበረከተ።

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2012 ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ድጋፍ የሚውል ከ500 ሺህ በላይ ማስክና የገንዘብ ድጋፍ ተበረከተ። በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከ6 የቻይና ተቋማት የተሰባሰቡ 500 ሺህ ማስኮችና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለከተማ አስተዳደሩ አበርክተዋል። የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ተቋማትም 1ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በተጨማሪም 180 ሺህ ብር የሚገመት በእግር የሚሰራ እጅ መታጠቢያ ድጋፍ ተደርጓል። ድጋፉን የተረከቡት […]

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ማዕከላት ቁጥር 46 ደረሰ፡፡

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ማዕከላት ቁጥር 46 ደረሰ፡፡የጤና ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ እንዳስታወቀዉ የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ መግባቱ ሲረጋገጥ ምንም ዓይነት የመመርመሪያ ማዕከል ያልነበራት ኢትዮጵያ በአሁን ወቅት 46 ማዕከላት አላት ብሏል፡፡የጤና ሚኒስቴር ይህን ችግር በመረዳት በአጭር ጊዜ በአገር ውስጥ የመመርመሪያ መሳሪዎችን በሟሟላት እና ባለሙያዎችን በማሰልጠን የላብራቶሪ ምርመራ ማዕከላትን አደራጅቷል፡፡ የሚኒስቴሩ የመመርመር አቅም ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ እንደመጣም ገልጿል፡፡እስከ ግንቦት […]

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደቦ የተሰኘ የሰዎች ንክኪ መለያ የአንድሮይድ ስልክ መተግበሪያ ይፋ አደረገ ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012  የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደቦ የተሰኘ የሰዎች ንክኪ መለያ የአንድሮይድ ስልክ መተግበሪያ ይፋ አደረገ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮቪድ-19 በሽታ ስርጭትን ለመከላከል የሚያግዝ ደቦ የተሰኘ የሰዎች ንክኪ መለያ የአንድሮይድ ስልክ መተግበሪያ ይፋ አድርጓል።የንክኪ መለያው የአንድሮይድ መተግበሪያ የስልክን የብሉቱዝ ሞገድ በማብራት የራሱን የብሉቱዝ ፕሮቶኮል ተጠቅሞ ከሁለት ሜትር በታች ቅርበት ያላቸውን […]

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ምርመራ 1 መቶ 42 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸዉ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ምርመራ 1 መቶ 42 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸዉ፡፡ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት ባለፉት 24 ሰዓታት ዉስጥ በተደረገዉ የ4 ሺህ 1መቶ 20 የላብራቶሪ ምርመራ 1 መቶ 42 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 4 መቶ 86 ደርሷል፡፡ቫይረሱ […]

ፔፕሲኮ ኢትዮጵያ “ ምግብ ይለግሱ -ተስፋን ይቀጥሉ “የሚል ፕሮግራም ይፋ አደረገ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 27፣ 2012 ፔፕሲኮ ኢትዮጵያ “ ምግብ ይለግሱ -ተስፋን ይቀጥሉ “የሚል ፕሮግራም ይፋ አደረገ ፡፡በፕሮግራሙም 2 ሺህ ሰዎችን ለሶስት ወራት ምሳና እራት እንዲመገቡ ይደረጋል፡፡ድርጅቱ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንደስታወቀዉ ፤ ድጋፉ በኢትዮጵያ በኮቪድ 19 ስርጭት ምክንያት ለተጎዱና ጫና ለደረሰባቸዉ አካላት የሚዉል ሲሆን 8ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡ድርጅቱ ድጋፉን ከሜቅዶንያ በጎ አድራጎት ተቋም ጋር […]

ብራዚል በ24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ ተባለውን የኮሮናቫይረስ ሞት አስመዘገበች፡፡

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 27፣ 2012 ብራዚል በ24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ ተባለውን የኮሮናቫይረስ ሞት አስመዘገበች፡፡ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ለማንሳት እየተንቀሳቀሰች ያለችው ብራዚል ለሁለት ተከታታይ ቀናት በርካታ ዜጎቿ እንደሞቱባት ተገልጿል፡፡ አልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው በብራዚል በአንድ ቀን ብቻ 1 ሺህ 349 ሰዎች በኮቪድ 19 ምክንያት ህይዎታቸው ማለፉ ተረጋግጧል፡፡ ብራዚል እስካሁን ከ32 ሺህ 500 በላይ ዜጎቿ የሞቱባት ሲሆን በበሽታው የተያዙት […]

ይህን ክፉ ጊዜ ያለው ለሌለው በማጋራት በመተጋገዝ ልናልፈው ይገባል-አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 ይህን ክፉ ጊዜ ያለው ለሌለው በማጋራት በመተጋገዝ ልናልፈው ይገባል-አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፡፡ ይህን ክፉ ጊዜ ለማለፍ እርሾ ለሚያጥራቸው ጎረቤቶች ያለው ለሌለው በማጋራት ማለፍ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ጥሪ አቅርበዋል።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመኖሪያ አካካቢያቸው ለሚገኙ ከ114 በላይ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የተለያዩ ምግብ ነክ ድጋፎችን አበርክተዋል።  አቶ […]