loading
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ግምት የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012  የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ግምት የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች፡፡ ቤተክርስትያንዋ ላደረገችዉ ድጋፍ በአማራ እና አፋር ክልል በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ሳቢያ ለችግር ለተጋለጡ 10 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች የሚሰራጭ ነዉ፡፡ ለደቡብ ወሎ ዞን የተደረገውን 800 ሺህ ብር በሚጠጋ ወጪ የሙቀት መለኪያ፣የምግብ ዘይት፣ዱቄትና የተለያዩ የንፅህና […]

በኮሮና ዙርያ የተሰሩ ከ20 በላይ ጥናቶች በኦን ላይን ኮንፈረንስ ለውይይት በመቅረብ ላይ ናቸው ።

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2012 በኮሮና ዙርያ የተሰሩ ከ20 በላይ ጥናቶች በኦን ላይን ኮንፈረንስ ለውይይት በመቅረብ ላይ ናቸው ።የኦንላይን ኮንፍረንሱ ምሁራን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ ያከናወኑዋቸው ጥናቶች ለማሳወቅና ቫይረሱን አስመልክቶ የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።ውይይቱ ላይ የመቐለ አዲስ አበባ ፣ ባህርዳር እና ሃረማያ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን የተሳተፉበት መሆኑን ዶክተር አዲሱ ተናግረዋል ።ጥናታዊ ጽሁፎቹ […]

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሚከሰትን የደም አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ የምስራቅ ወለጋ ዞን አመራሮች ደም ለገሱ፡፡

የዞኑ ኮሚኒኬሽን ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ቀደም ሲል የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አገራዊ የደም አቅርቦት በመቀነሱ የልገሳ ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ ነዉ ፡፡ በልገሳ መረሓ ግብሩ የተገኙት የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አስመራ ኢጃራ በሰጡት አስተያየት፤ የኮሮናቫይረስ ከመግባቱ በፊት ሲቀርብ የነበረው ደም በመቀነሱ በችግር ጊዜ ሕዝብና አገርን የማሻገር ሃላፊነታችንን እንወጣለን […]

የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመግታት የቻይና አፍሪካ ትብብር የማይተካ ሚና አለው አሉ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ለአርትስ በላከዉ መግለጫ  እንዳስታወቀዉ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዓለም ላይ የተከሰተውን የኮቪድ19 ወረርሽኝ ለመግታት የቻይና አፍሪካ ትብብር የማይተካ ሚና አለዉ ብለዋል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ትናንት “ዓለም አቀፉ የአንድ ቀበቶ አንድ መንገድ ኢኒሸቲቭ” የቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄገበት ወቅት እንዳሉት ፤የዓለም ስጋት የሆነውን የኮቪድ19 ወረርሽኝ ለመግታት በቻይና እና አፍሪካ መካከል የሚደረገው ትብብር ከምንጊዜውም በላይ ወሳኝ ነዉ። ቻይና የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመግታት የተከተለችውን ስትራቴጂ እና የተገኘውን ውጤትም አድንቀዋል። ኢትዮጵያ የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመግታት እያደረገች ባለው እንቅስቃሴ የቻይና መንግስት እና እንደ ጃክማ የመሳሰሉ የቻይና በለሃብቶች እያደረጉት ላለው ድጋፍ ያመሰገኑት አቶ ገዱ፥ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። በኮንፈረንሱ ላይ የቻይና ስቴት ካውንስልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል። “የአንድ ቀበቶ አንድ መንገድ ኢኒሸቲቭ” ዓለም አቀፍ ትብብርን በማሳደግ የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመግታት የሚያስገኘውን ጠቀሜታ በተመለከተ በስፋት መብራራቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት የላከልን መግለጫ  ያመለክታል።

በኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታዞን ለኮቪድ 19 ህሙማን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወሰነ ።

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012  በኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታዞን ለኮቪድ 19 ህሙማን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወሰነ ።የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት ;ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት በተመለከተ በእንግሊዝ መንግስት የተካሄደውን ጥናት እና ሪፖርት በዝርዝር ተመልክተነዋል ብለዋል፡፡የህክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድናችን እና የጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት፣ የሰጠንን ምክረ ሀሳብ […]

በኮቪድ 19 ተይዘው በሆስፒታሉ ህክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 37 ታካሚዎች አገግመው ወጡ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17፣ 2012  በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማዕከል የኮቪድ 19 ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ 37 ታካሚዎች አገግመው መዉጣታቸዉን ሆስፒታሉ አስታዉቋል ፡፡በኮቪድ 19 ፓዘቲቭ ሆነው ወደ ሆስፒታሉ የገቡት በአጠቃላይ 178 ነበሩ፡፡ በመጀመሪያ ዙር 44 ታካሚዎች አገግመው መውጣታቸው የሚታወቅ ሲሆን በሁለቱ ዙር አጠቃላይ 81 ሰዎች አገግመው ወጥተዋል ። በሆስፒታሉ የኮቪድ 19 ቫይረስ ሊኖርባቸው ይችላሉ ተብለው […]

ኢራቅ 13 ዶክተሮቿ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ማጣቷን ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 ኢራቅ 13 ዶክተሮቿ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ማጣቷን ይፋ አደረገች:: የሀገሪቱ ባለስልጣናት በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ካለፈው ፌብሯሪ ወር ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ 13 ዶክተሮቿ በኮቪድ 19 ሞተውባቸዋል፡፡ የኢራቅ የሀኪሞች ማህበር ሀላፊ አብዱል አላሚር አል ሺማሪ በመላ ሀገሪቱ ከ700 በላይ ዶክተሮች በበሽታው መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡ ሀኪሞቻችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለመርዳት የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው […]

የዓለም ጤና ድርጅት አሁንም የአፍሪካ ጉዳይ እንደሚያሳስበው ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ14፣ 2012 የዓለም ጤና ድርጅት አሁንም የአፍሪካ ጉዳይ እንደሚያሳስበው ገለፀ:: የድርጅቱ የአስከቸኳይ የጤና ነክ ጉዳዮች ሀላፊ የሆኑት ሚካኤል ሪያን በሰጡት መግለጫ መላው አፍሪካ የደቡብ አፍሪካን ሁኔታ ተመልክቶ መጠንቀቅ አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ደቡብ አፍሪካ ከ373 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙባት ከ5 ሺህ በላይ ዜጎቿ በኮቪድ19 ሳቢያ ህይታቸው አልፏል፡፡ በመጀመሪያ አካባቢ ሀብታም በሆኑ የአፍሪካ ሀገራት የጀመረው […]

በአፍሪካ ከ10 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ19 መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ አደረገ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 በአፍሪካ ከ10 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ19 መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ አደረገ:: ድርጅት ባወጣው ሪፖርት የሄን ያህል ቁጥር ያላቸው የጤና ባለሙያዎች በበሽታው የተያዙት በ40 የአፍሪካ ሀገራት ነው፡፡ ድርጅቱ የጤና ባለሞያዎቹ በአህጉሩ በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ወደ ኋላ የሚጎትት ፈተና ነው ብሏል፡፡ ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት […]

የዓለም ጤና ድርጅት በቀጣዮቹ አምስት ወራት በኮቪድ 19 የሚያዙ ወጣቶች ቁጥር በሦስት እጥፍ ያድጋል ሲል አሳሰበ፡፡

አዲስ አበባ፣ሐምሌ29፣ 2012 የዓለም ጤና ድርጅት በቀጣዮቹ አምስት ወራት በኮቪድ 19 የሚያዙ ወጣቶች ቁጥር በሦስት እጥፍ ያድጋል ሲል አሳሰበ፡፡በዓለም አቀፍ የሚገኙ እድሜያቸው ከ15 እስከ 24 ዓመት የሆናቸው ወጣቶች በቫይረሱ የመያዝ እድላቸው በቀጣዮቹ አምስት ወራት ውስጥ በሶስት እጥፍ ያድጋል ብሏል ድርጅቱ፡፡ በቫይረሱ ስርጭት የመጀመሪያውን ስፍራ የያዘቸው አሜሪካን ጨምሮ ስፔን፣ጀርመን፣ ፈረንሳይና ጃፓን አዲስ በቫይረሱ ከሚያዙት ሰዎች መካከል […]