loading
ባለፉት 24 ዓመታት በኢትዮጵያ በትምህርትና ስልጠና ሥርዓት በታዩ ችግሮች ዙርያ ዛሬ ውይይት ይደረጋል

የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ከዛሬ ጀምሮ የሚደረገው የውይይት መድረክ ዋነኛ ዓላማ ለፍኖተ-ካርታው ዝግጅት እንዲረዳ በተዘጋጀው የመጀመሪያ ደረጃ ረቂቅ ጥናት ዙሪያ ውይይት በማድረግ ለፍኖተ-ካርታው ዝግጅት የሚረዳ ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ የማሻሻያ ሀሳቦች ዙሪያ በሚደረገው ውይይት በተሳታፊዎች የሚቀርቡ ተጨማሪ የማሻሻያ ሀሳቦች በቂ ውይይት ከተደረገባቸውና መግባባት ከተደረሰባቸው በኋላ ለ15 ዓመታት […]

የዘንድሮ አረፋ በዓል በአዲስ አበባ በአንድነት በአንድ ቦታ በስቴዲም ይከበራል፡፡

በነገው ዕለት የሚከበረው ዒድ አል አድሃ አረፋ ከሌሎች ግዜያቶች በተለየ መልኩ በአንድነት እና በፍቅር ስሜት እንድሚከበር ነዉ የአድስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤት ፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ሸሪፍ ሃሰን ለአርትስ ቲቪ የተናገሩት፡፡ የዘንድሮው አረፋ ልዩነታችን ተገፎ በአንድነት እና በእርቅ ማከበራችን ለየት ያደርገዋል ብለዋል፡፡ በዓሉም ‹ሰላም እና አንድነት ለኢትዮጵያ›› በሚል መሪ-ቃል እንደሚከበርም ሼህ መሀመድ ነግረዉናል፡፡ የ አረፋ […]

በትምህርት ፖሊሲያችን ላይ ሁሉን አቀፍ ለዉጥ እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

በትምህርት ፖሊሲያችን ላይ ሁሉን አቀፍ ለዉጥ እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በቲዉተረ ገጻቸዉ እንዳስታወቁት ዶክተር አብይ ይህንን የተናገሩት ዛሬ የተጀመረዉን ሀገር አቀፍ የትምህርት ፖሊሲ ማሻሻያ ፍኖተካርታ ፎረምን በንግግር በከፈቱበት ወቅት ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ማሻሻያ ተደረገበት፡፡

በዚህም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ባለስልጣኑ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ላይ ብቻ እንዲያተኩርና ቀደም ሲል በባለስልጣኑ ይሰጡ የነበሩ ሌሎች አገልግሎቶች ወደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ሌሎች ተጠሪ ተቋማት እንዲዛወሩ መደረጉን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በቲዉተርና በፌስቡክ ገጻቸዉ አስታዉቀዋል፡፡ በቀጣይም የስራ ኃላፊዎች፣ሰራተኞችና የአሰራር ስርዓቱ ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን በማለት ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት በተያዘው አቅጣጫ መሰረት […]

አርሷደሯ ጌሪ አሜሪካ ተብሎ ለሚጠራው የእህል ፈጅ ትል መድሀኒት አገኙ፡፡

አርሷደሯ ወ/ሮ ታቦቴ አባተ በቦኖ በደሌ ዞን አርሶ አደር ናቸው። ከችግራቸው በመነሳትም ጌሪ አሜሪካ ለተባለ ትል አዲስ የትል ማጥፊያ ፈጥረዋል። የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ሴንተር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ ጌሪ አሜሪካ በቆሎን በብዛት የሚያጠቃ ትል ነው።ትሉ ቁጥጥር ካልተደረገበት በበቆሎ ምርት ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳል። በአንድ ሌሊት በ1500 እጥፍ ሊራባ ይችላል። ወ/ሮ ታቦቴ ታዲያ ይህን ትል የሚገድል መድሀኒት […]

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሕግ የበላይነት ለማስከበር ሕጋዊ እርምጃዎች ተወሰዱ።

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሕግ የበላይነት ለማስከበር ሕጋዊ እርምጃዎች ተወሰዱ። ሱሉልታ በቄሮ ስም እንቅስቃሴ በማድረግ ሌሊት የግለሰቦችን ቤት በማፍረስና ቆርቆሮ በመውሰድ ላይ የተሰማሩ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ሻሸመኔ ባለፈው ሳምንት በከተማው የተፈጸመው ወንጀል እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 7 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ቡራዩ የቄሮ አመራር ነኝ በማለት መታወቂያ አዘጋጅቶ የተለያዩ ተቋማት በግድ ስፖንሰር እንዲያደርጉት […]

የአሸንዳ ክብረ በአል ከባህላዊ እሴትነቱ ባሻገር ለነጋዴዎች የገቢ ማስገኛ መንገድ ነው ።

አርትስ ቲቪ በመቀሌ ከተማ ያነጋገራቸው ነጋዴዎች በአሸንዳ በአል ነጋዴዎች ልጃገረዶች የሚለብሷቸውን ባህላዊ አልባሳት፣ፀጉርላይ የሚታሰሩ (እንቁ)የሚባሉ ማጌጫዎች ፣ በቀሚስ ላይ የሚደረግ የተገመደ ክር (ድሪ) የአንገትና የጆሮ ጌጣጌጦች በአዘቦቱ ቀን ከሚሸጡበት የ20 እና 30 ብር ጭማሪ አንዳለው ነው የተናገሩት። በአሉን ልጃገረዶች በተለየ መንገድ ስለሚያከብሩት የፀጉር ባለሙያዎችንም ትርፋማ የሚያደርግ እንደሆነ ተመልክተናል ።

በነገው እለት የሚከበረውን የአሸንዳ በአል አስመልክቶ በመቀሌ ከተማ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

የፓናል ውይይቱ አብይ አላማ ያለፉት አመታት የበዓሉን አከባበር መገምገም፣አሸንዳን በአለም አቀፍ ደረጃ ስለማስተዋወቅ እንዲሁም ከዩኔስኮ ጋር የተያያዙ ጥናቶች እና ሀሳቦችን ማንሳት ነው ተብሏል፡፡ የትግራይ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ዘነቡ ሐለፎም እንደገለፁት አሸንዳ ከባህላዊ እና ሃይማኖታዊ አንድምታው በተጨማሪ ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር እንዲሁም ፖለቲካዊ ተሳትፎአቸውን የሚያሳይ የነጻነት ቀን ነው ብለዋል፡፡ በውይይቱ የቀደሙ […]

ተወረወረች ጨረቃ …በመድሃኒዓለም ጫንቃ

ተወረወረች ጨረቃ በመድሃኒዓለም ጫንቃ . ይሄ አዳራሽ ….ኧኸ የማን አዳራሽ የጌታዬ ድርብ ለባሽ። . ይኸው ሲዞር ወገቧ ባቄላ ነው ቀለቧ . ይሄው ወገቤ ነጭ ጤፍ ነው ቀለቤ። በሚለው የልጃገረዶች ጨዋታ ለሚደምቀው አሸንድዬ በላሊበላ ዝግጅት እየተደረገ ነው።