የኦሮሚያ የከተሞች ስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በ2011 በጀት ዓመት ስራ አጥና በግል ስራ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች 3.283 ቢሊዮን ብር ለመስጠት አዘጋጅቻለሁ አለ፡፡
በዚህም 1.1 ሚሊዮን ወጣቶችን በ90 ማህበራት ለማደራጀት ተወስኗል፡፡ ከነዚህ መካከል 64 ሺህ የሚሆኑት ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ናቸው፡፡ ለመፍጠር በተዘጋጀው የስራ ዕድል 52205 ሄክታር የከተማና የገጠር መሬት ተዘጋጅቷል፡፡ እንዲሁም 4648 አዳዲስ ሼዶች የሚገነቡ ይሆናል፡፡ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ በወቅቱ እንዳሳወቁት ወጣቶች የተፈጠረላቸውን የስራ ዕድል ብቻ ሳይሆን በሃገር የኢኮኖሚ እድገት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ […]