loading
መንግሥት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2014 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ እና ለመሳተፍ ፍላጎት ካላቸው የህንድ ባለሀብቶች እና ከህንድ የኢንቨስትመንት ፎረም አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡ አምባሳደር ሬድዋን ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከአሁን በፊት ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ያልሆኑ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ጭምር ክፍት ማድረጓን አስታውሰዋል። የሕንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ […]

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ማካሄድ ጀመረ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2014 የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጣሂር መሐመድ ያለፉት ጊዜያት የፓርቲው እንቅስቃሴ እንደሚዳሰስና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችም እንደሚቀመጡ አስታውቀዋል። የማዕከላዊ ኮሚቴው ስብሰባ በወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታ አብን ለሕዝቡ ሊያበረክት ስለሚችለው አስተዋጽኦ፣ በቅርቡ በሚደረገው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባዔ ቅድመ ዝግጅት ላይ፣ ስድስተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ምን ይመስል እንደነበርና በሂደቱ የአብን ሚና ምን እንደነበር በስፋት […]

በኢትዮጵያ በየዓመቱ 5 ሺህ የሚደርሱ ህፃናት ከእግር መቆልመም ችግር ጋር ይወለዳሉ ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 በኢትዮጵያ በየዓመቱ 5 ሺህ የሚደርሱ ህፃናት ከእግር መቆልመም ችግር ጋር ይወለዳሉ ተባለ፡፡ ይሁን እንጂ የህክምና አገልግሎቱን ከሚፈልጉት የችግሩ ተጠቂ ህጻናት መካከል 50 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን የጤና ሚስቴር ገልጿል፡፡ በሚኒስቴሩ የህክምና አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር አባስ ሀሰን ችግሩ ያለባቸውን ህጻናት በጊዜ መለየትና ፈጥኖ ማከም ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ ለሙያተኞች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ የጤና […]

የግብርና ሚኒስቴር  በሰው ሰራሽ ዘዴ ሴት ጥጃ ብቻ የሚያስወልድ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊያደርግ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 የግብርና ሚኒስቴር  በሰው ሰራሽ ዘዴ ሴት ጥጃ ብቻ የሚያስወልድ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊያደርግ ነው፡፡ ፕሮጀክቱን በይርጋለም ከተማ በይፋ ያስጀመሩት የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ የወተት ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ  ነው ብለዋል።በሀገሪቱ በተመረጡ 58 ወረዳዎች ከዓለም ባንክ በተገኘ 176 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በወተት ላም፣ በዶሮ፣ በዓሣና በስጋ ከብት ላይ […]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአመራር ለውጥ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ፡፡ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ ነው አቶ መስፍን የሃላፊነቱን ቦታ የተረከቡት፡፡ አቶ መስፍን በኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ የጥገናና ኢንጂነሪንግ፣ እንዲሁም የኦፕሬሽን ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል። በተቋሙ ውስጥ ላለፉት 38 አመታት በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች […]

የኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ መፅደቅ ኢትዮጵያን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥገኛ የሚያደርግ በመሆኑ እንዳይፀድቅ ሁሉም ሊሰራ እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጠየቁ።

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 የኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ መፅደቅ ኢትዮጵያን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥገኛ የሚያደርግ በመሆኑ እንዳይፀድቅ ሁሉም ሊሰራ እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጠየቁ። አምባሳደር ዲና ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ስታተርፊልድ ጋር በተለያዩ […]

የኢትዮጵያ መንግስት የግጭት ማቆም እርምጃ በምዕራባዊን ዓይን…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን አሜሪካና አውሮፓ ህብረት አደነቁ:: የአውሮፓ ህብረት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ መዘጋጀቱን ነው የገለጸው፡፡ ህብረቱ አክሎም ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ድጋፉ በፍጥነት እንዲደርስ እንደሚሰራም አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ከመንግስት በኩል እንደተደረገው ሁሉ […]

ስራውን ቆጥሮ ያስረከበው ምክር ቤት ውጤቱን በአግባቡ ቆጥሮ ይረከብ ይሆን?

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቆጥሮ የሰጠውን ስራ ቆጥሮ መረከብ የሚያስችለውን የፊርማ ስነስርዓት አከናወነ፡፡ ምክር ቤቱ አስፈፃሚውን የመከታተልና መቆጣጠር ስልጣን ተግባራዊ ለማድረግ ብሎም የተጠያቂነትን ስርዓት ለማስፈን ይረዳው ዘንድ ነው ይህን ያደረገው፡፡ ሥምምነቱ በዋናነት በምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎችና በአስፈፃሚዎች (የቢሮ ሃላፊዎች) መካከል የተቋማቱን እቅድ መሰረት ያደረገ ይዘት ያለው ሲሆን ከንቲባ አዳነች አቤቤ […]

ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የሚሳተፉበት ‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ይካሄዳል።

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2014 ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የሚሳተፉበት ‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ይካሄዳል።ከቀኑ 10 ሰአት ጀምሮ በአሜሪካ መንግስት መቀመጫ ‘ካፒቶል ሂል’ ፊት ለፊት በሚካሄደው ሰልፍ ረቂቅ ሕጎቹ የኢትዮጵያን ሕልውና የሚጎዱ በመሆኑ ውድቅ መሆን አለበት የሚሉ መልዕክቶች ይተላለፋሉ ተብሏል፡፡ ሕጎቹ ለረጅም ጊዜ የቆየውን በኢትዮጵያና አሜሪካ […]

ረመዳን ሙስሊሞች ራሳቸውን ከምግብና ከመጠጥ ብቻ ሳይሆን ከራስ ወዳድነት የሚያርቁበት ወር ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 ታላቁ የረመዳን ወር ይቅር የምንባባልበት መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ገልጸዋል፡፡ተቀዳሚ ሙፍቲው ይህን ያሉት የታላቁ ረመዳንን ወር ፆም አስመልክቶ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡ በመግለጫቸውም ረመዳን ሙስሊሞች ራሳቸውን ከምግብና ከመጠጥ ብቻ የሚያርቁበት ወር ብቻ ሳይሆን መልካም በመስራት ራሳቸውን ከፈጣሪያቸው ጋር ይበልጥ የሚያቀራርቡበት ነው […]