loading
የአድዋን ታሪክ በሚገባ በመለየት አሁን ላለንበት ችግር መፍቻ ቁልፍ ማድረግ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ ጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ገለጹ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 የአድዋን ታሪክ በሚገባ በመለየት አሁን ላለንበት ችግር መፍቻ ቁልፍ ማድረግ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ ጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ገለጹ። ለ126ኛ ጊዜ “አድዋን ለኢትዮጵያውያን ኅብረት፣ ለአፍሪካ የነፃነት ጮራ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚከበረውን የአድዋ ድል በዓል አስመልክቶ የውይይት መድረክ ተካሄዷል፡፡ የቢሮ ኃላፊዋ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ […]

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 31 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ ተበረከተ::

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 31 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ ተበረከተ በሶማሌ ክልል በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙ ጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውል 31 ሚሊዮን ብር የሚገመት የተለያዩ መድሃኒቶች፣ የተመጣጠነ ምግብ እና የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል። በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሀረላ አብዱላሂ የተመራ ከጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ መድሃኒት […]

ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ‘ኤችአር 6600’ ረቂቅ ሕግን የሚቃወሙበት ሰልፍ በኒውጄርሲ ሊካሄድ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 ሰላማዊ ሰልፉ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም በአሜሪካ ኒውጄርሲ ግዛት እንደሚካሄድ የኒውዮርክ ኒውጄርሲ ተስፋ ለኢትዮጵያ ድርጅት ዋና ሰብሳቢ አቶ አክሊሉ ታፈሰ ለኢዜአ ገልጸዋል። ሕጉን ያረቀቁት የኒውጄርሲ የኮንግረስ አባል ቲም ማሊኖውስኪ በሚሰሩበት ቢሮ ፊት ለፊት እንደሚከናወንና እሳቸውንና ሕጉን የሚቃወሙ መልዕክቶች በሰልፉ ላይ እንደሚተላለፉ አመልክተዋል። ሕጉን በአሜሪካ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት […]

በህገ ወጦች ላይ ምህረት የለሽ እርምጃ እንወስዳለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 በህገ ወጦች ላይ ምህረት የለሽ እርምጃ እንወስዳለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአቋራጭ ለመክበር በሚሞክሩ አካላት ላይ ምህረት የለሽ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባዋ በከተማዋ ዘይትን ጨምሮ በሌሎች ሸቀጦች ላይ ዋጋ የሚያስጨምር ምንም አይነት ምክንያት የለም በማለት ተናግረዋል፡፡ የምርት እጥረት ቢኖርም እንኳ ያለውን ምርት ግን በትክክል […]

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በጦር ግንባር ጀብድ ፈፅመው ድል ላመጡ ሴቶች ምስጋና አቀረቡ::

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በመከላከያ መኮንኖች ክበብ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ተከብሯል። ፕሬዚዳንቷ በዚህ ወቅት ሴት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በናንተ ድርብ መስዋዕትነት ሀገር ትቀጥላለችና ለናንተ ክብር መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የሀገራችን ሰላም በሴቶች ተጋድሎ ይረጋገጣል፤ በጀግና ሴቶች ሰማዕትነት ሀገራችን ታፍራ እና ተከብራ ትኖራለችም ብለዋል፡፡ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ […]

ያማረ ቢሮ ብቻ ሳይሆን ያማረች አገር ለመገንባት እንሥራ – ጠ/ሚ ዐቢይ::

አዲስ አበባ፣መጋቢት 5፣2014 ያማረ ቢሮ ብቻ ሳይሆን ያማረች አገር ለመገንባት መሥራት አለብን ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡ ዶክትር ዐቢይ ፓርቲው ዛሬ ባስመረቀው ዋና ጽህፈት ቤት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ህንጻውን የሚመጥን ሥራ መስራት አለብን፤ ሀገር በዘይትና በስኳር የተነሳ ችግር ውስጥ እያለች ለመፍትሔውመስራት ካልቻልን አስቸጋሪ ነው ብለዋል። በቢሯችን ልክ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የምንሠራ ሊሆን […]

በኢትዮጵያ አማካይ የመኖሪያ እድሜ 69 ዓመት ደረሰ በኢትዮጵያ 45 የነበረው አማካይ የመኖሪያ እድሜ ምጣኔ ወደ 69 ዓመት ማደጉ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣መጋቢት 5፣2014 በኢትዮጵያ 45 ዓመት የነበረው አማካይ የመኖሪያ እድሜ ምጣኔ ወደ 69 ዓመት ማደጉን  በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብሔራዊ የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራ እና ትንተና ማእከል አስታውቋል፡፡   ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የጤና አትላስ ይፋ ባደረገበት ወቅት ፤ በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ1980 አማካይ የመኖሪያ እድሜ ዘመን 45 ዓመት የነበረው በ2019 ወደ 69 ዓመት ማደጉን አስታውቋል። በፈረንጆቹ 1990 […]

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 5፣2014 ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ :: በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ከፍተኛ ውድመት ተፈፅሞበት ተዘግቶ የቆየው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል። የዩኒቨርሲቲው ጥበቃና ደህንነት ሰራተኞች አስፈላጊውን የፍተሻ ስራ እያከናወኑ ጥሪ የተደረገላቸውተማሪዎች ከዛሬ ጠዋት ጀምረው ወደ ግቢ በመግባት ላይ ናቸው፡፡ ዩኒቨርሲቲው መጋቢት 5 እና 6 ቀን 2014 ዓ.ም ለተማሪዎቹ ምዝገባ የሚያካሂድ ሲሆን÷ለተማሪዎቹም የትራንስፖርት […]

2 ሺህ 574 አመራሮችን ከሃላፊነት አንስቼያለሁ- ብልጽግና ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 ብልጽግና ፓርቲ በቅድመ ጉባኤ ግምገማ 2 ሺህ 574 አመራሮች ከሃላፊነት እንዲነሱ አድርጌያለሁ አለፓርቲው ይህን ያለው የመጀመሪያ ጉባኤ መካሄዱን ተከትሎ ከቅድመ ጉባኤ እስከ ፍፃሜው ድረስየነበረውን ክንውን በማስመልከት መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በፓርቲው ቅድመ ጉባኤ ግምገማ 108 ሺህ 258አመራሮች ተገምግመው በ10 ሺህ 658 አመራሮች ላይ የተለያየ ደረጃ ያለው […]

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ምግብን መሠረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ ይፋ ተደረገ::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ምግብን መሠረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ ይፋ ተደረገ:: መመሪያውን በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስተባባሪነት የጤና ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴርና አጋር አካላት ናቸው በጋራ ያዘጋጁት፡፡ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ የ2019 ጥናት እንደሚያመለክተው በሀገራችን 54 በመቶ የሚሆኑ ቤተሰቦች እንዲመገቡ ከሚመከረው ሰባት የምግብ ምድቦች ውስጥ ከአራት በታች የሚመገቡመሆናቸው ተረጋግጧል ነው የተባለው፡፡ በተለይም ህፃናትና […]