loading
የቀድሞ የአፋር ክልል ፕሬዝደንት የነበሩት ሱልጣን ሀንፍሬ አሊ ሚራህ አዲስ አበባ ገቡ፡፡

በሱልጣን ሐንፈሬ አሊ ሚራህ የሚመራውና በስደት በውጭ አገራት ሲኖሩ የነበሩ ልኡካን ቡድን አባላት ዛሬ አዲስ አበባ መግባቱን ኢብኮ ዘግቧል፡፡ ከአፋር ህዝብ ፓርቲ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ ፣ከአፋር ሰብዓዊ መብት አቶ ጋአስ አህመድ እና ከአፋር ነፃ አውጪ ግንባር አቶ ኡመር አሊሚራህ ይገኙበታል፡፡ ልኡካኑ አዲስ አበባ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዲሪ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የአፋር ብሄራዊ […]

ከአዲስ አበባ የተለያዩ የጤና ተቋማት የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች በጅግጅጋ ጉዳት ለደረሰባቸው 128 ሰዎች የህክምና አገልግሎት ሰጡ፡፡

የህክምና ቡድን መሪ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ትላንት አመሻሽ ላይ ከጅግጂጋ ሲመለሱ በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ላይ ተገኝተው እንደገለጹት ቡድኑ በስምንት ቀን ቆይታው ለ128 ጉዳት ለደረሰባቸው ግለሰቦች የህክምና አገልግሎት ድጋፍ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ ከተጎጅዎቹ መካከልም ግማሽ ያህሎቹ የጭንቅላት፣ የደረት፣ የሆድና የደረት ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገላቸው መሆኑን ዶ/ር ብርሃኑ ገልጸዋል፡፡ የህክምና ቡድኑ ወደ ጅግጂጋ ከማቅናቱ በፊትም በድሬዳዋ ከተማ […]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀጅ ተጓዦች ላይ የተፈጠረውን የበረራ መስተጓጎል ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ የሀጅ ተጓዦች በረራቸው ተሰርዞ በአየር መንገድ ውስጥ ያለ በቂ ምግብና ማረፊያ እየተጉላላን ነው ብለዋል፡ ይህን ተከትሎ አቢሲ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ስልክ ደውሎ ስለ ሁኔታው ለማጣራት ቢሞክርም አየር መንገድ ስለ ጉዳዩ በፌስ ቡክ ገፁ ካወጣው መረጃ ተጨማሪ የሚሰጠው መረጃ እንደሌለው የህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል፡፡ አየር መንገዱ በፌስ ቡክ ገፁ ባወጣው መግለጫ በሀጅ […]

ስምንት ኮንቴይነር የታሸገ የኤሌክትሪክ እቃና አልባሳት በህገ-ወጥ መንገድ ሲገባ ተያዘ፡፡

በጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ጥሬ እቃ ስም በስምንት ኮንቴነር የታሸገ ያለቀለት የኤሌክትሮኒክስ እቃና አልባሳት ወደ ሃገር ውስጥ ሊገባ ሲል መያዙን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ጠቅሶ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በድረ ገጹ አስታዉቋል ። በባለስልጣኑ የሞጆ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የጉምሩክ ስነ-ስርዓት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ግርማ በንቲ እንደገለጹት እቃው የተያዘው ተመሳስሎ ሊያልፍ ሲል በሞጆ ደረቅ ወደብ […]

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ጥሪ አቀረቡለት

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ወደሀገሩ እንዲመለስ መጋበዛቸውን ያስታወቁት። በመግለጫቸውም በሪዮ ኦሎምፒክ እና በልዩ ልዩ የዓለም አትሌቲክስ መድረኮች በመሳተፍ የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አስተዋጽኦ ያበረከተው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ፍላጎታቸው መሆኑን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተዘጋጁት […]

ከ12 ከተሞች ተገልጋዮች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በሚሰጠው አገልግሎት አልረካንም አሉ፡፡

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ከዋልታ ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት ጋር በመተባበር በከተሞች የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ ከተሞች የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ቅንጅታዊ አሰራር ሊከተሉ ይገባል ተብሏል፡፡ ከተሞቻችን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር እጦት የሰፈነባቸው የምሬት ማዕከል ሆነዋል ያሉት የከተማ ልማትና ቤቶች ሚንስትር አቶ ጃንጥራር አባይ፤ በአመራሮችና ፈጻሚዎች ድክመት፣ የብቃት ችግር ፣ቀልጣፋና ፍትሃዊ […]

ቅዱስ ጊዮርጊስ ጌታነህ ከበደን አስፈረመ፡፡

የቀድሞ የደቡብ ፖሊስ እና የደደቢት እንዲሁም በፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወቱ የደቡብ አፍሪካዎቹን ቢድቬስት ዊትስ እና ፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲ ያሳለፈው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ጌታነህ ከበደ (ሰበሮ) በዛሬው ዕለት ለ2 ዓመት ፈረሰኞቹን ተቀላቅሏል። ጌታነህ ደደቢት ቡድኑን በአዲስ መልክ ለማደረጀት፤ በአነስተኛ ክፍያ ወጣቶች ላይ ትኩረት ለማድረግ ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ በተለያዩ ክለቦች ሲፈለግ ቆይቶ በመጨረሻ ፈረሰኞቹን ተዋህዷል፡፡ የ26 አመቱ ተጫዋች […]

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ።

ልዑኩ ወደ ሀገር ቤት የመጣውም በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መካከል ባሳለፍነው ነሃሴ 1 2010 ዓ.ም የእርቅ ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ነው። ልዑኩ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም የኦህዴድ የከተማ ፖለቲካና የድርጅት ዘረፍ ሀላፊ አቶ ከፍያለው አያና እናሌሎች የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውለታል። የልዑካን ቡድኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስራ አስፈጻሚ […]

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አንድነት ላይ ያተኮሩ በዓላትን ላዘጋጅ ነዉ አለ፡፡

ከነሐሴ አጋማሽ አስከ መስከረም 30 የሚቆየዉ የበዓላት ዝግጅት “አንድ ሆነን አንድ እንበል” በሚል መሪቃል የሚከበር ነዉ፡፡ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ዛሬ በሰጡት መግለጫ የሚዘጋጁት የተለያዩ በዓላት ለአዲስ አመት የሚመጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ቱሪስቶችን መቀበል ላይ ያተኮረ ነዉ ብለዋል፡፡ ሚኒስትሯ በሆቴሎች በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በአስጎብኚ ድርጅቶች ያገልግሎት ዋጋ ቅነሳ በተጨማሪ ሁላችንም ኢትዮጵያዉን ፤ኢትዮጵያዊ በሆነ […]