loading

ቅዱስ ጊዮርጊስ ደረጃውን ማሻሻል የቻለበትን ውጤት አስመዝግቧል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሀግብር ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል ።

በክልል ስታዲየም ጅማ ላይ ጅማ አባ ጅፉር ወላይታ ድቻን አስተናግዶ በአስቻለው ግርማ እና ማማዱ ሲዲቤ ጎሎች 2 ለ 0 መርታት ችሏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ በወጣቶች የተገነባውን ደደቢት ገጥሞ በተመሳሳይ 2 ለ 0 አሸንፏል ።

ለፈረሰኞቹ የድል ጎሎቹን በመጀመሪያው አጋማሽ አጥቂው ሳላዲን ሰኢድ በቅጣት ምት በማስቆጠር ቀዳሚ ሲያደርግ፤ በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ላይ በጌታነህ ከበደ ተቀይሮ የገባው  አቤል ያለው ምርጥ ችፕ አስቆጥሯል።

ጊዮርጊሶች ያገኟቸውን የግብ አጋጣሚዎች ቢጠቀሙ ኑሮ የሚቆጠረው የጎል መጠን ከፍ ባለ ነበር ።

ድሉን ተከትሎ ፈረሰኞቹ አንድ ተስተካካይ ግጥሚያ እየቀራቸው ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ቡና በአንድ ነጥብ አንሰው በ21 ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ደረጃውን ማሻሻል የቻለበትን ውጤት አስመዝግቧል።

በቡና እና ጊዮርጊስ መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ዝቅ ብሏል ።

ኢትዮጵያ በአመታዊ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተካፈለች 

ኢትዮጵያ በአመታዊ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተካፈለች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የተመራ የኢትዮጵያ መንግስት የልዑካን ቡድን በብራስልስ ቤልጂየም በተካሄደው በአመታዊው የአፍሪካ ህብረትና የአውሮፓ የአውሮፓ ህብረት የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተካፍሏል። ጉባኤው ላይ የአፍሪካ ህብረት አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና የአውሮፓ ህብረት አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተገኙ ሲሆን፣ ስብሰባውን በጋራ የመሩት […]

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን የሚገኘውን የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክት በትናንትናው ዕለት ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅትም የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክት በሙሉ አቅም የማምረት ሽግግር ሂደት ውጤታማ መሆኑን የፕሮጀክቱ የስራ ሃላፊዎች […]