loading
ለሪልስቴት ልማት መሬት ወስደው ወደተግባር ያልገቡት ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው

ለሪልስቴት ልማት መሬት ወስደው ወደተግባር ያልገቡት ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው ተባለ።   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዳስታወቀው በከተማዋ ውስጥ በሪልስቴት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን የግንባታ ሁኔታ እና ህጋዊነት የሚያጠና ግብረሃይል አዋቅሮ የዳሰሳ ጥናት ሲያከናውን ቆይቷል።   በዚህም ግብረሃይሉ በፋይል ፣ የግንባታ ሳይት ላይ ጉብኝት በማድረግ እና መጠይቆችን በመጠቀም የሪልስቴቶቹን የህግ አግባብነት ፣ የሊዝ ውል እና የግንባታ […]

በደቡብ ክልል ዘጠኝ ሆስፒታሎች መገንባት የሚችል ገቢ ሳይሰበሰብ ቀርቷል ተባለ

በደቡብ ክልል ዘጠኝ ሆስፒታሎች መገንባት የሚችል ገቢ ሳይሰበሰብ ቀርቷል ተባለ። በክልላዊ የታክስ ንቅናቄ ዙሪያ በሃዋሳ ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተወጣጡ የክልሉ ነዋሪዎች ጋር ምክክር በተካሄደበት ወቅት የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ አስረስ እንደተናገሩት የክልሉ ያለፉት ሁለት ዓመታት የተሰበሰበው የታክስ ገቢ መሰብሰብ ከሚገባው አንፃር ሲታይ 9 ደረጃቸውን የጠበቁ ዲስትሪክት ሆስፒታሎችን መገንባት የሚያስችል ገቢ ሳይሰበሰብ […]

የመንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት ባለፉት ሰባት ወራት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ

የመንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት ባለፉት ሰባት ወራት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡ገቢው ለመንገድ ጥገናና ለመንገድ ደህንነት እርምጃዎች ማስፈጸሚያ ይውላል ብሏል። ጽህፈት ቤቱ ለአርትስ ቲቪ የላከው የተቋሙ የ2011 በጀት አመት የሰባት ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያመለክተው በሰባት ወራት የስራ አፈጻጸሙ  1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ችሏል። […]

ጠ/ሚር አብይ አሕመድ የጊዴቦ ግድብ ስራ ፕሮጀክትን ዛሬ መረቁ::

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የጊዴቦ ግድብ ስራ ፕሮጀክትን ዛሬ ጥር 26 ቀን 2011 መረቁ:: በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች የሚገኘው ይህ ግድብ 25.8 ሜትር ከፍታና 335 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ከ62.5 ሚሊዮን ኪዩብ በላይ ውሃ የመያዝ አቅም አለው:: ግድቡን ሰርቶ ለማጠናቀቅም ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ፈጅቷል:: በዛሬው ምረቃ ስነስርዓት ላይም የኦሮምያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ለማ መገርሳና የደቡብ ክልል […]

˝የግብር ፍትሃዊነት  ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት˝ የተሰኘ አዲስ ጽህፈት ቤት ሊቋቋም ነው

˝የግብር ፍትሃዊነት  ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት˝ የተሰኘ አዲስ ጽህፈት ቤት ሊቋቋም ነው ጽህፈት ቤቱ የግብር አሰባሰብ ሂደቱን የተቃና ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል በሀገራችን  መሰብሰብ ከነበረበት ግብር ከ 80 ቢሊዩን ብር በበላዩ ሳይሰበሰብ እንደቀረ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከንግድ ስርዓት ውጭ በመሆን፤ ለመንግስት የሚገባውን  ከፍያ አለመፈጸም ፤በታክስ መረብ ውስጥ አለመታወቅ እና በአግባቡ ተመዝገበው የቲን ስርዓት ውስጥ አለመካተት […]

ባለፉት 7 ወራት ኢትዮጵያ ወደውጭ ከላከቸው ቡና ያገኘችው የውጭ ምንዛሬ መጠን በ56 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ተባለ

ባለፉት 7 ወራት ኢትዮጵያ ወደውጭ ከላከቸው ቡና ያገኘችው የውጭ ምንዛሬ መጠን በ56 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ተባለ በሰባቱ ወራት ወደውጭ ገበያ ለመላክ ከታቀደው ከ16 ሺህ 546 ቶን ቡና ውስጥም  መላክ የተቻለው 11ሺህ 165 ቶን መሆኑ ታውቋል። የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አንደሚጠቁመው በ2011 በጀት ዓመት ጥር ወር  16 ሺህ 5 መቶ 46 ቶን […]