loading
ደቡብ አፍሪካ ወደ አምስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማዕበል መግባቷ ተነገረ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2014 ደቡብ አፍሪካ ወደ አምስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማዕበል መግባቷ ተነገረ:: ደቡብ አፍሪካ ወደ አዲስ የኮቪድ- 19 ማዕበል እየገባች መሆኑን የሀገሪቱ የወረርሽኝ ምላሽ እና ፈጠራ ማዕከል አስታውቋል። የቤታ እና ኦሚክሮን ልውጥ ባህሪ ያላቸውን ቫይረሶችን በመለየት ዝነኛ የሆነው የጥናት ማዕከል ሃላፊ አምስተኛው ዙር የወረርሽኝ ስርጭት መከሰቱን በትዊተር ገፁ ላይ ይፋ […]

የግብፅ የፀጥታ ሃይሎችና የ”አይ ኤስ አይ ኤል” ግብግብ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 በሲናይ በርሃ ለተገደሉት የግብፅ ወታደሮች አይ ኤስ አይ ኤል ሃላፊነቱን እደሚወስድ ገለጸ፡፡ ቡድኑ ባለፈው ቅዳሜ እለት በሲናይ በርሃ 11 የግብፅ ወታደሮችን መግደሉንና መሳሪያቸውን መማረኩን ነው ይፋ ያደረገው፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው ከስዊዝ ካናል በስተምስራቅ በምትገኘው ኢማኢሊያ ከተማ መሆኑን አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ አይ ኤስ አይ ኤል በሲናይ ባህረ ገብ በኬላ ጥበቃ ላይ በነበሩ […]

በደቡብ ሱዳን የኮሌራ በሽታ መከሰቱ በደቡብ ሱዳን በተከሰተው የኮሌራ በሽታ አንድ ሰው ሲሞት 31 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ታውቋል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 በደቡብ ሱዳን የኮሌራ በሽታ መከሰቱ በደቡብ ሱዳን በተከሰተው የኮሌራ በሽታ አንድ ሰው ሲሞት 31 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ታውቋል ተባለ፡፡ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2017 ወዲህ በደቡብ ሱዳን የኮሌራ በሽታ ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡ በሽታው የተከሰተው በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ዩኒቲ ግዛት ሩቦንካ ካውንቲ ሲሆን በበሽታው […]

ለቶማስ ሳንካራ ቤሰቦች የተወሰነው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዩሮ የካሳ ክፍያ…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 በፕሬዚዳንት ቶማስ ሳናካራ ግድያ የተጠረጠሩት ፕሬዚዳንት ብላሲ ኮምፓዎሬና አጋሮቻቸው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዩሮ ካሳ እንዲከፍሉ ተወሰነባቸው፡፡ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ብሌስ ኮምፓወሬ ከሌሎች 9 ተከሳሾች ጋር ነው ላደረሱት የሞራልና የኢኮኖሚ ጉዳት ካሳውን እንዲከፍሉ የተወሰነባቸው፡፡ ከኮምፓዎሬ ጋር ፍርድ ከተላለፈባቸው ግለሰቦች መካከል የፕሬዚዳንቱ ጥበቃ ክፍል አዛዥ የነበሩት ሃይሲንቴ ካፋዶ፣ የመከላከያ ኢታማጆር ሹሙ ጊልበርት […]

የማሊ ወታደራዊ መንግስት ለተቃጣበት መፈንቅለ መንግስት ምዕራባዊያንን ወቀሰ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 የማሊ ወታደራዊ መንግስት ለተቃጣበት መፈንቅለ መንግስት ምዕራባዊያንን ወቀሰ፡፡ ራሱ በመፈንቅለ መንግስ ስልጣን የያዘው የኮሎኔል አሲሚ ጎይታ አስተዳደር የተቃጣበትን መልሶ ግልበጣ የጸጥታ ሃይሎች እንዳከሸፉት ገልጿል፡፡ የአሁኑ የመንግስት ግልበጣ ሙከራ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2020 ወዲህ ሁለት መፈንቅለ መንግስት ላስተናገደችው ማሊ ፖለቲካዊ ትኩሳቷ እንዳይበርድ ያደርጋል የሚል ስጋት ፈጥሯል ነውየተባለው፡፡ ወታደራዊ መንግስቱ በመግለጫው ከከሸፈው […]

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሸይክ ሞሐመድ በቅርብ ጊዜ የፀጥታ ስራውን ከሰላም አስከባሪ ሃይሉ እንረከባለን አሉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሸይክ ሞሐመድ በቅርብ ጊዜ የፀጥታ ስራውን ከሰላም አስከባሪ ሃይሉ እንረከባለን አሉ፡፡በሀገሪቱ የደህንነት ስጋት የሆነውን አልሸባብን ለማጥፋት ቁጥር አንድ መፍትሄ ወታደራዊ ጥንካሬ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል እስካሁን ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ከአናዶሉ የዜና ወኪል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሀገራቸው ቀዳሚ ችግሯ የፀጥታ […]

የሱዳኑ ኡማ ፓርቲ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ከሚገኘው ወታደራዊ ሃይል ጋር በአጋርነት እንደማይሰራ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 የሱዳኑ ኡማ ፓርቲ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ከሚገኘው ወታደራዊ ሃይል ጋር በአጋርነት እንደማይሰራ አስታወቀ፡፡ፓርቲው በሰጠው መግለጫ በሲቪልና ተወካዮችና በወታደራዊ ሃይሉ መካከል ያልው ግንኙነት ከተሳትፎ በዘለለ በአጋርነት ደረጃ መሆን የለበትም ብሏል፡፡ የነፃነትና የለውጥ ሃይሎች አባል የሆነው ኡማ ፓርቲ የዚህ ፖለቲካዊ ጥምረት ትልቁ ምሶሶ ተደርጎ እንደሚቆጠር ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡ የፓርቲው ዋና ፀሃፊ አል […]

የሶማሊያው አዲሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውን በይፋ ተረክበው ስራ ጀመሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2014 የሶማሊያው አዲሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውን በይፋ ተረክበው ስራ ጀመሩ፡፡ ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ፋርማጆ በስልጣን ርክክቡ ወቅት ባደረጉት ንግግር አዲሱ መሪ ወደ ስልጣን የመጡበት ወቅት ፈታኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለዓመታት በአልቃኢዳ መራሹ አልሸባብ የምትታመሰው ሶማሊያ በቅርቡ ያጋጠማት የድርቅ አደጋ ሌላው ራስ ምታት ነው ብለዋል ፋርማጆ፡፡ እናም ይህን ሁኔታ ለማስተካከል ፕሬዚዳንት ሀሰን ሸይክ […]

በሴኔጋል በአንድ ሆስፒታል በተከሰተ የእሳት አደጋ የ11 ህፃናት ህይወት ማለፉ በሀገሪቱ ከፍተኛ ሀዘን ፈጥሯል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 በሴኔጋል በአንድ ሆስፒታል በተከሰተ የእሳት አደጋ የ11 ህፃናት ህይወት ማለፉ በሀገሪቱ ከፍተኛ ሀዘን ፈጥሯል ተባለ፡፡የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በጨቅላ ህፃናቱ ላይ የደረሰውን አሰቃቂ አደጋ በሰማሁ ጊዜ ልቤ በሀዘን ተሰብሯል ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት መልእክትም ለህፃናቱ ወላጆችና ለመላው ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ በማለት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡ የጤና ሚኒስትሩ አብዱላየ ዲዩፍ ሳር በበኩላቸው […]

ውስጣዊና የውጭ ጫና የበረከተባት ሱዳን የጣለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳች፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 ውስጣዊና የውጭ ጫና የበረከተባት ሱዳን የጣለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳች፡፡ ወታደራዊ አስተዳደሩን የሚመሩት ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ከወራት በፊት ተጥሎ የነበረው የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ መነሳቱን ይፋ ሲያደርጉ ከአዋጁ ጋር በተገናኘ የታሰሩ ሰዎች እደሚፈቱም ፍንጭሰጥተዋል ተብሏል፡፡ የአዋጁ መነሳት የተሰማው በሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ በሳምንቱ መጨረሻ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች ባፀጥታ ሃይሎች መገደላቸው […]