loading
ሱዳን ለፀጥታው ምክር ቤት የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር እንዲጀምር የሚያሳስብ ደብዳቤ ላከች::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 ሱዳን ለፀጥታው ምክር ቤት የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር እንዲጀምር የሚያሳስብ ደብዳቤ ላከች:: የሱዳን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ተደራዳሪዎቹ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የሶስትዮሽ ውይይቱን በፍጥነት እንዲጀምሩና በተናጠል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ የሚጠይቅ ደብዳቤ ነው የላከው ተብሏል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ አሳም ሞሀመድ አብደላ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በላኩት ደብዳቤ በድርድሩ ሂደት […]

የሊቢያ መንግስት የትሪፖሊ አየር ማረፊያን አስመልሻለሁ አለ፡፡

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 27፣ 2012 የሊቢያ መንግስት የትሪፖሊ አየር ማረፊያን አስመልሻለሁ አለ፡፡አለም አቀፍ እውቅና ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አልሳራጅ መንግስት በጄኔራል ከሊፋ ሀፍታርጦር ተይዞ የነበረውን አየር መንገድ በውጊያ መልሶ መቆጣጠሩን ተናግሯል፡፡አልጀዚራ እንደዘገበው አየር መንገዱ በሀፍታር ሰራዊት ስር በመውደቁ የተነሳ እንደአወሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2014 ጀምሮ ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ ነበር፡፡ከስድስት ዓመታት በፊት ትሪፖሊን ለመቆጣጠር አልመው ጦርነት ያወጁት ሀፍታር […]

የብሩንዲ ህገ መንግስታዊ ርድ ቤት የሀገሪቱን የምርጫ ውጤት አፀና ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2012 የብሩንዲ ህገ መንግስታዊ ርድ ቤት የሀገሪቱን የምርጫ ውጤት አፀና ::ፍርድ ቤቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያቀረቡትን የምርጫ ውጤት ተጭበርብሯል የሚል ቅሬታ ውድቅ በማድረግ ኢቫሪስት ንዳይሺሚ አዲሱ የብሩንዲ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን ይፋ አድርጓል፡፡ የዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪው አጋቶን ሩዋሳ ባቀረቡት ቅሬታ ንዳይሺሚ በ68 በመቶ የድምፅ ብልጫ አሸንፈዋል መባሉን ፈጽሞ የማንቀበለው ነው ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ […]

የአልቃይዳ የሰሜን አፍሪካ መሪ አብደልማሌክ ድሩክደል በፈረንሳይ ጦር ተገደሉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 የአልቃይዳ የሰሜን አፍሪካ መሪ አብደልማሌክ ድሩክደል በፈረንሳይ ጦር ተገደሉ፡፡ የፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አብደልማሌክ ድሩክደል በሰሜናዊ ማሊ ግዛት በፈረንሳይ ወታደሮች መገደሉን አስታውቋል፡፡ እንደ አልጄዚራ ዘገባ የሰሜን አፍሪካ የአለቃይዳ አዛዥ በማሊ ለሰባት ዓመታት በፈረንሳይ ወታደሮች ሲታደን መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በሽብረተኛ ቡድን መሪው መገደል ዙሪያ ከአልቃይዳ በኩል ምንም የተባለ ነገር […]

የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ጥቃት የሚደርስባቸው ዜጎች ቁጥር መጨመሩ አሳስቦኛል አለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ጥቃት የሚደርስባቸው ዜጎች ቁጥር መጨመሩ አሳስቦኛል አለ፡፡ ድርጅቱ በሪፖርቱ እንደስታወቀው ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ በሀገሪቱ ምስራቃዊ ግዛት 1 ሺህ 300 የሚሆኑ ንፁሃን ሰዎች መገደላቸው ታወቋል፡፡ በተለይ ኢቱሪ፣ ሰሜንና ደቡባዊ ኪቩ አካባቢዎች የጥቃቱ ሰለባ የሚሆኑ ዜጎች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ነው ተብሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት […]

ግብፅ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 47 ዶክተሮቿን በሞት ማጣቷ ትልቅ ስጋት ሆኖባታል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2 ፣ 2012 ግብፅ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 47 ዶክተሮቿን በሞት ማጣቷ ትልቅ ስጋት ሆኖባታል ተባለ::የብግብፅ የህክምና ማህበር በሰጠው መግለጫ የሀገሪቱ የጤና አጠባበቅ ስርዓት በፍጥነት ካልተስተካከለና ለሀኪሞች ልዩ እንክብካቤ ካልተደረገላቸው የበለጠ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ብቻ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሰባት ዶክተሮች መሞታቸው ሁኔታው ምን ያህል አደገኛ እየሆነ መምጣቱን ያሳያል ነው የተባለው፡፡ ከሁለት […]

ኬንያዊያን ፖሊስ በንፁሀን ዜጎች ላይ የሚፈፅመውን ግድያ ያቁም የሚል ተቃውሞ እያሰሙ ነው::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2 ፣ 2012 ኬንያዊያን ፖሊስ በንፁሀን ዜጎች ላይ የሚፈፅመውን ግድያ ያቁም የሚል ተቃውሞ እያሰሙ ነው:: በኬንያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የተጣለውን የእንቅስቃሴ እገዳ ተከትሎ ፖሊስ ህግ በማስከበር ሰበብ በርካታ የሰብዓዊ መብቶችን እየጣሰ እንደሆነ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰዎች ተናግረዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው መንግስት እገዳውን ከጣለ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በፖሊስና በነዋሪዎች መካከል በተከሰቱ ግጭቶች ከ15 ያላነሱ […]

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ድርድረ በሚኒስትሮች ደረጃ ተካሄደ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3 ፣ 2012 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ድርድረ በሚኒስትሮች ደረጃ ተካሄደ፡፡ዉሃ መስኖና እና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በበይነ-መረብ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ታዛቢዎች በተገኙበት በውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ ተካሂዷል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የሙሌት እና ዓመታዊ የውሃ አለቃቅ በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል የሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር […]

የብሩንዲው ፕሬዚዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ በልብ ህመም በድገንገት ህይዎታቸው አለፈ ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3 ፣ 2012የብሩንዲው ፕሬዚዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ በልብ ህመም በድገንገት ህይዎታቸው አለፈ ::የብሩንዲ መንግስት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ፕሬዚዳንቱ በልብ ህመም መሞታቸው ተረጋግጧል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ቅዳሜ በአንድ የቮሊቦል ጨዋታ ውድድር ላይ ታድመው የነበረ ሲሆን በዚያው ምሽት ታመው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ የጤናቸው ሁኔታ መሻሻል አሳይቶ የነበረ ቢሆንም ሰኞ እለት በተደረገላቸው […]