loading
የአየር ላንድ መንግስት ቅርሶችን በአረንጓዴ ብርሃን ማስዋብ በሚል በላሊበላ የአረንጓዴ ብርሃን ዝግጅት አካሄደ

የአየር ላንድ መንግስት ቅርሶችን በአረንጓዴ ብርሃን ማስዋብ በሚል በላሊበላ የአረንጓዴ ብርሃን ዝግጅት አካሄደ፡፡ ዝግጅቱ ቅርሶችን በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ተብሏል። ያም ሆኖ የአንድ ምሽቱ ተግባር ከዚህ ቀደም ከተያዘውና ላሊበላን በዘላቂነት ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ከተባለው ፕሮጀክት ጋር አልገናኝ ማለቱ ለብዙዎች ጥያቄ ፈጥሯል ። የአርትስ ሪፖርተር ከስፍራው ያጠናቀረችው ዘገባ እንደሚያስረዳው። በያዝነው ወር አየርላንድ እና ኢትዮጵያም […]

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ላሉ 170ሺህ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ያግዛል  የተባለ የ2 ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ ጸደቀ

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ላሉ 170ሺህ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ያግዛል  የተባለ የ2 ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ ጸደቀ።   ፈንዱን ያጸደቀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ ለወጣቶች ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ ለመመደብ የቀረበ ረቂቅ ሰነድ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል፡፡   በዚህም መሠረት ዝርዝር ዕቅዶችን በማዘጋጀት እና ከወጣቱ ጋር ሰፊ የምክክር መድረኮችን በማዘጋጀት የጋራ […]

የጌዲዮ ተፈናቃዮች ከገቢዎች ሚኒስቴር የአልባሳትና የምግብ ድጋፍ አገኙ

የጌዲዮ ተፈናቃዮች ከገቢዎች ሚኒስቴር የአልባሳትና የምግብ ድጋፍ አገኙ።   የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን በትናንትናው ዕለት ከምዕራብና ምስራቅ ጉጂ ዞኖች እንዲሁም ጌዲኦ ዞን አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች የተጠለሉበት ቦታ በመገኘት ነው ከ21 ሚሊየን ብር በላይ የሚወጣ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ያደረጉት። ለተፈናቃዮች የተደረገው ድጋፍ  ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለተጎጂዎች እንዲደርስ ለማስቻል የተፈናቃይ ተወካዮችና የዞኑ አመራሮች በተገኙበት ገደብ ከተማ ላይ […]

ኮፊ አረቢካ በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ተፈላጊነቱ እያደገ ነው ተባለ

ኮፊ አረቢካ በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ተፈላጊነቱ እያደገ ነው ተባለ።   በቻይናውያን ዘንድ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መጥቷል የተባለው ይኸው የኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ በሃገሪቱ በተካሄደ ዓለም ዓቀፍ ልዩ የቡና ትርኢት ቀርቧል።   ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ይኸው አውደትርዒቱ ከመጋቢት 2 እስከ 8 ቀን 2011 ዓ.ም በቻይና ፑኤር ከተማ ተካሂዷል። እንደ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት  ገለፃ […]

በታንዛንያ እስር ቤት የነበሩ 235 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው

በታንዛንያ ታንጋ በሚባል ከተማ በሚገኝ ማዌይኒ በሚባል እስር ቤት የነበሩ 235 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅኅፈት ቤት አስታውቋል። ስደተኞቹን ኢትዮጵያውያን የመመለሱን ስራ  የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከብሄራዊ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከታንዛንያ መንግስት ጋር በመተባበር እየሰራ ነው ተብሏል። ከ3 ቀናት በፊት በተመሳሳይ ቦታ የነበሩ 50 […]

ዲሱ የአልጄሪያ ጠቅላይ ሚንስትር አዲስ ካቢኔ ላዋቅር ነው አሉ

አዲሱ የአልጄሪያ ጠቅላይ ሚንስትር አዲስ ካቢኔ ላዋቅር ነው አሉ። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ኦያሂያ በሀገሪቱ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ስልጣናቸውን መልቀቃቸው የሚታወስ ሲሆን እርሳቸውን ተክተው ኑረዲን ቤዶኡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ተሹመዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ገለልተኛ የሆኑ ባለሙያዎችን ያካተተ አዲስ ካቢኔ ለመሰየም ውይይት ማድረግ መጀመራቸውን የሀገሪቱ ዜና ወኪል ኤፒኤስ ዘግቧል፡፡ አዲስ […]

መረጃዎች የአውሮፕላን አደጋውን መንስኤ በተመለከተ ወደ ቦይንግ እየጠቆሙ ነው

መረጃዎች የአውሮፕላን አደጋውን መንስኤ በተመለከተ ወደ ቦይንግ እየጠቆሙ ነው። ብዙ ተስፋ የተጣለበት እና ለምርመራ ወደ ፈረንሳይ የተላከው የመረጃ ሳጥንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ከኢንዶኔዢያው ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው የሚያሣይ መረጃ አቀብሏል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት ከሆነውና ቢሾፍቱ አቅራቢያ ከወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላን ስብርባሪ ውስጥ የመረጃ መዝጋቢ ሳጥን(ብላክ ቦክስ) መገኘቱ የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ሲቃትቱ ለነበሩ ልቦች ሁሉ እፎይታን አስገኝቷል። ይህ ሳጥን በዚህ ፍጥነት ሊገኝ መቻሉ  በአደጋው  ዙሪያ የሚሰነዘሩ መላምታዊ መረጃዎችን በማስቀረት ሳይንሳዊ […]