loading
በኢትዮጵያ ትምህርት አሁንም ቀዳሚ የልማት አጀንዳ ነዉ ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ ትምህርት አሁንም ቀዳሚ የልማት አጀንዳ ነዉ ተባለ፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በ206ኛው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት / UNESCO / የስራ አስፈጻሚ ቦርድ ስብሰባ ላይ አገራቸውን በመወከል ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ትምህርት አሁንም ቅድሚያ የተሰጠው የልማት አጀንዳ ነው ብለዋል፡፡

በአገሪቱ ግንባር ቀደም የልማት አጀንዳ የሆነውን ትምህርት ተገቢነቱ እንዲረጋገጥና መጪውን ትውልድ እንዲመጥን የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ የመከለስና ሥርዓተ ትምህርቱን የማሻሻል ሥራዎች በመከናወን ላይመሆናቸውን ዶክተር ጥላዬ ገልጸዋል፡፡

ፍኖተካርታው ከዘላቂ የትምህርት ልማት ግቦች ጋር የተገናዘበ እንዲሆንና ሥርዓተ ትምህርቱን የማሻሻል ተግባር በውጤታማነት እንዲፈጸም በዘርፉ ልምድ ያላቸው የዓለም አቀፉ የትምህርት ቢሮ / IBE / ባለሙያዎች ድጋፍ እንደማይለያቸውም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ጥረት ከተደረገባቸው የማሻሻያና የለውጥ እርምጃዎች መካከልም ኢኮኖሚውን ለማነቃቃትና የግልና የመንግስት ተሳትፎን ለማሻሻል ስትራቴጂክ ዘርፎችን ሊበራላይዝድ ለማድረግ እየተሰራ ያለው ተግባር እንደሚገኝበት ተናግረዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት / UNESCO / በበጎ ፈቃድ በትምህርት ዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችና ችግሮች እንዲፈቱና ወደኋላ የቀሩ መንግስታትና ማህበረሰቦችም የቅድሚያ ትኩረት እንዲያገኙ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያደንቁ  ዶክተር ጥላዬ ገልጸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *