loading
በበጀት ዓመቱ የጤና መሰረተ ልማት ግንባታዎች አፈጻጸም አበረታች ነው ተባለ::

በበጀት ዓመቱ የጤና መሰረተ ልማት ግንባታዎች አፈጻጸም አበረታች ነው ተባለ::

ጅማ ከተማ ላይ ሲካሄድ በነበረው የጤና ተቋማት ግንባታ አፈጻጸም ግምገማ ላይ አማራ፣ ሶማሌ፣ አፋር ክልልና እና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የተሻለ አፈጻጸም እንዳሳዩ ተነግሯል።

በጤና ሚኒስቴር የጤና መሠረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታደሠ የማነ በግምገማዉ ወቅት እንደተናገሩት፤ የአገልግሎትና የጥራት ችግር ያለባቸውን 200 ጤና ጣቢያዎችን የማስፋፋት፣ የውሃና የመብራት ችግር ያለባቸውን 200 ጤና ጣቢያዎችን የማሟላት እንዲሁም ለ170 ጤና ጣቢያዎች ከፀሃይ ሃይል መብራት የማቅረብ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነዉ ።

በአገር አቀፍ ደረጃ በበጀት ዓመቱ ጠረፋማ ለሆኑ ጤና ጣቢያዎች 2500 የመኖሪያ ቤት ግንባታዎችም አየተሰሩ ነዉ፡፡

የግንባታ መዘግየቶች መኖራቸውን፣ በግንባታ ግብዓቶች ወጪ መጨመር፣ የዉጭ ምንዛሬ እጥረት ፤ በአንዳንድ ክልሎች የነበረው የጸጥታ ችግር ፣ የስራ ተቋራጮች ድክመት እና የአማካሪ ድርጅቶች የክትትል ማነስ፣ እንደችግር ተነስተዋል፡፡
የአፈጻጸም ችግር ያለባቸውን ተቋራጮች እና አማካሪ ድርጅቶች ውልን በማቋረጥ፣ በህግ እንዲጠየቁ እና በቀጣይም በግንባታው ዘርፍ በጨረታ የማይወዳደሩትን የመለየት ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል  በመፍሄነት ተቀምጧል ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *