loading
ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ለመገናኘት መጠየቃቸው ተነገረ::

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 25፣2014 ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ለመገናኘት መጠየቃቸው ተነገረ:: የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር በሞስኮለመገኘት ቢጠይቁም እስካሁን ምላሽ አላገኙም ተብሏል። ፖፕ ፍራንሲስ ለጣሊያኑ ኮሪየር ዴላ ሴራ ጋዜጣ እንደተናገሩት የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ኪሪል ጦርነቱ […]

ሰሜን ኮሪያ በአንድ ዓመት ውስጥ 14ኛውን የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 ሰሜን ኮሪያ በአንድ ዓመት ውስጥ 14ኛውን የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች፡፡ ፒዮንግያንግ የአሁኑን የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራውን ያደረገችው የኒውክሌር መርሃ ግብሯን በከፍተኛ ፍጥነት ለማሳደግ እየሰራች መሆኗን ይፋ ባደረገች በሳምንት ውስጥ ነው ተብሏል፡፡ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2017 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል ባስወነጨፈች በአንድ ወር ጊዜ ሌላ […]

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ቻይና በታይዋን ላይ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ ሀገራቸው ጣልቃ እደምትገባ አስጠነቀቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ቻይና በታይዋን ላይ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ ሀገራቸው ጣልቃ እደምትገባ አስጠነቀቁ፡፡ ባይደን በእስያ ጉብኝታቸው ጃፓን ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ቤጂንግ በታይዋን ላይ አንዳች ጥቃት ለማድረስ ከሞከረች ሀገራቸው የሃይል እርምጃ እንደምትወስድ ነው የተናገሩት፡፡ ፕሬዚዳንቱ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ዋሽንግተን ታይዋንን ከቻይና ጥቃት የመጠበቅ ሀላፊነት አለባት ብለዋል፡፡ከጃፓኑ ጠቅላይ […]

ቻይና የታይዋን የአየር መከላከያ ክልል ጥሳ በመግባት የጠብ አጫሪነት ተግባር እየፈጸመች ነው ስትል አሜሪካ ወቀሰች፡፡

አዲስ አበባ፣ግንቦት 23፣2014 ቻይና የታይዋን የአየር መከላከያ ክልል ጥሳ በመግባት የጠብ አጫሪነት ተግባር እየፈጸመች ነው ስትል አሜሪካ ወቀሰች፡፡ የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ 30 የቤጂንግ የውጊያ አውሮፕላኖች ወደ አየር ክልላችን ዘልቀው ገብተዋል፤ ከነዚህ መካከል ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት ተዋጊ ጄቶች ናቸው ብሏል፡፡ ቻይና በታይዋን ሁለተኛውን ግዙፍ ወታደራዊ ቅኝት ያደረገችው ትንሿ ደሴት ከአሜሪካ ጋር በደህንነትና በፀጥታ ዙሪያ […]

ሞሳድ የኢራኑን ፕሬዚዳንት ለመግደል አሲሯል-የኢራን የስለላ ምንጮች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 እስራኤል የኢራኑን ፕሬዚዳንት ለመግደል ማቀዷን ደርሸበታለሁ ሲል የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አስታወቀ፡፡ ቴልአቪቭ ይህን የምታርገው በኢራን መረጋጋት እንዳይፈጠር ለማድረግ መሆኑንም አብዮታዊ ዘቡ አብራርቷል፡፡ ተቋሙ በይፋዊ የቴሌግራም ቻናሉ ባሰፈረው ጽሁፍ የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከቴህራን ውጭ በሚገኙበት ወቅት ግድያው እንዲፈጸምባቸው እቅድ መንደፉን የደህንነት መረጃ ያላቸው ምንጮች ነግረውኛል […]

ሞስኮን ያልበረገራት የምእራባዊያን የነዳጅ ማእቀብ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 በሩሲያ ላይ የተጣለው የነዳጅ ግብይት ማእቀብ ግቡን እዳልመታ የሚገልጽ አዲስ ሪፖርት ይፋ ሆነ፡፡ ሪፖርቱ ፕሬዚዳንት ቭላደሚር ፑቲን ጦራቸውን ወደ ዩክሬን ባዘመቱ በ100 ቀናት ውስጥ ሞስኮ ከነዳጅ ሽያጭ 98 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን ይገልጻል፡፡ ይህን ሪፖርት ይፋ ያደረገው ተቀማጭነቱ ፊንላንድ የሆነ በኢነርጂና ንጹህ አየር ላይ ምርምር የሚያደርግ ገለልተኛ ተቋም ነው […]

ትራምፕ እንዲከሰሱ ድምፅ የሰጡት ተወካይ በምርጫ መሸነፍ…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 በካፒቶል ህንፃ በተነሳው ግርግር ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲከሰሱ ድምፅ የሰጡት የሪፓበሊካን ተወካይ በዳግም ምርጫ ተሸነፉ፡፡ በኖርዝ ካሮላይና ለአምስት ዓመታት በህግ አውጭ ምክር ቤት ተወካይነት ያገለገሉት ቶም ራይስ የተሸነፉት በቀድሞው ፕሬዚዳንት በሚደገፉት ሩሴል ፍራይ በተባሉ እጩ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ፍራይ ማሸነፋቸውን ካወቁ በኋላ ባደረጉት ንግግር መራጩ ህዝብ በግልፅ ቋንቋ በካርዱ ተናግሯል፤ […]

በጠቅላይ ሚኒስትራቸው እምነት ያጡ የእንግሊዝ ሚኒስትሮች ስራ መልቀቅ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2014 በእንግሊዝ በጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እምነት አጣን በማለት የሥራ መልቀቂያ የሚያስገቡ ባልስልጣናት ተበራክተዋል ተባለ፡፡ በርካታ ሚኒስትሮች ከጆንሰን ጋር መስራት እደማይችሉ በመግለፅ ነው የሥራ መልቀቂያቸውን ያስገቡት ተብሏል፡፡ የአብዛኞቹ ምክንያት ተመሳሳይ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩና አስተዳደራቸው ላይ ያላቸው እምነት ከእለት ወደ እለት እየተሸረሸረ መምጣቱ መሆኑን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡ በትናንትናው እለት የሥራ […]

አውስትራሊያ የኮቪድ-19 ስርጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ቤት ሆኖ መስራትን እንደ አማራጭ እያጤነችው መሆኑ ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 አውስትራሊያ የኮቪድ-19 ስርጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ቤት ሆኖ መስራትን እንደ አማራጭ እያጤነችው መሆኑ ተነገረ፡፡በኮቪድ-19 ምክንያት ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱን ተከትሎ የአውስትራሊያ ዜጎች ቤታቸው ውስጥ ሆነው እንዲሰሩ እና ጭምብል እንዲለብሱ ተጠይቀዋል። ሀገሪቱ በአዳዲስ የኦሚክሮን ተህዋሲ የሶስተኛ ዙር ማዕበል ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የተጠቂዎችን መጨመር ለመቋቋም የሁለተኛ ምዕራፍ […]

ሩሲያ አሜሪካ በዩክሬኑ ጦርነት ቀጥተኛ ተሳታፊ ናት ስትል ከሰሰች፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 ሩሲያ አሜሪካ በዩክሬኑ ጦርነት ቀጥተኛ ተሳታፊ ናት ስትል ከሰሰች፡፡ ይህ የሞስኮ ወቀሳ የተሰማው የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ ምክትል ሃላፊ ቫዲም ስኪቢትስኪ ከአሜሪካ የተበረከተላቸው የረዥም ርቀት የሮኬት ማስወንጨፊያ ስርዓቶች በጥሩ የሳተላይት ምስል እና እውነተኛ መረጃ አቀባይ መሆናቸውን ከገለፁ በኋላ ነው፡፡ ምክትል ሃላፊው ከቴሌግራፍ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ ከጥቃቱ በፊት በአሜሪካ እና በዩክሬን […]