loading
የዐረብ ሊግ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈረም ለመንግስታቱ ድርጅት ጥያቄ አቀረበ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11፣ 2013  የዐረብ ሊግ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈረም ለመንግስታቱ ድርጅት ጥያቄ አቀረበ፡፡በጋዛ የተቀሰቀሰው ግጭት እንዲቆም እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ድርድሩ ሂደት ዳግም እንዲጀመር ነው ሊጉ ጥሪ ያቀረበው፡፡ የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በፈረንጆቹ ግንቦት 20 በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ዙሪያ ለመምከር ቀጠሮ መያዙን በድርጅቱ የአረብ ሊግ ተወካይ መጅድ አብደልፈታህ ተናግረዋል፡፡ ተወካዩ አህራም […]

በህንድ በ24 ሰዓታት ውስጥ ክብረ ወሰን የሆነ የኮሮናቫይረስ ሞት ተመዘገበ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11፣ 2013 በህንድ በ24 ሰዓታት ውስጥ ክብረ ወሰን የሆነ የኮሮናቫይረስ ሞት ተመዘገበ በህንድ እየተባባሰ የመጣውን የኮሮናባይረስ ወረርሽኝ መቆጣጠር ያቃታቸው ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ በህዝባቸው ዘንድ የነበራቸውን አመኔታ ዝቅ እንዲል አድርጎባቸዋል፡፡ በ24 ሰዓታት ውስጥ 4 ሽህ 529 ዜጎቿን በቫይረሱ የተነጠቀቸው ህንድ አሁንም በወረርሽኙ ጠንካራ ክንድ እየተደቆሰች ትገኛለች፡፡በየቀኑ በአማካይ ከ250 ሺህ በላይ ሰዎች […]

19 ክትባት ለሚከተቡ ሰዎች የአንድ ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 የኮቪድ ኦሃዮ በተሰኘችው አሜሪካዋ ክፍለ ሃገር የኮቪድ 19 ክትባት ለሚከተቡ ሰዎች አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኝ የሎተሪ ቁጥር እንደሚሰጣቸው ከተገለፀ በኋላ የተከታቢዎች ቁጥር በእጅጉ መጨመሩ ተገለፀ:: የኦሃዮ ክፍለ ሃገር አስተዳዳሪ ማይክ ዲዋይን በክትባቱ ላይ ጥርጣሬ ያላቸውን ሰዎች ለማበረታታትና የሚከተቡ ሰዎችን ቁጥር ለመጨመር ለእያንዳንዱ ክትባቱን የተከተበ ሰው አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኝ […]

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ማንኛውም ኃይል ከሩሲያ ግዛት ቅንጣት መሬት ለመውሰድ ቢሞክር፣ “ጥርሱን እናራግፍለታለን” ሲሉ አስጠነቀቁ።

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2013 የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ማንኛውም ኃይል ከሩሲያ ግዛት ቅንጣት መሬት ለመውሰድ ቢሞክር፣ “ጥርሱን እናራግፍለታለን” ሲሉ አስጠነቀቁ። ፕሬዚዳንቱ ከከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ጋር ባደረጉት የቪዲዮ ስብሰባ በተናገሩትና በቴሌቪዥን በተላለፈው ንግግራቸው፣ አንዳንድ የውጭ ሃገራት በከርሰ-ምድር ሃብት የበለፀገውን ሳይቤሪያ የተባለውን የሩሲያን ግዛት አስመልክቶ ከሚሰጡት አስተያያት ተነስተው መሆኑን ገልፀዋል። ከውጭ ሃገራት ተነገሩ የተባሉት ነገሮች በቀድሞዋ […]

የማይናማር መሪ አውንግ ሳን ሱኪ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2013 የአውንግ ሳን ሱኪ የመጀመሪያው የችሎት ውሎ የቀድሞዋ የማይናማር መሪ አውንግ ሳን ሱኪ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰማ:: ባለፈው ፌብሯሪ ወር መግቢያ ላይ በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣናቸው የተወገዱት መሪዋ ለ4 ወራት በእስር ሲቆዩ ችሎት ቀርበው አያውቁም፡፡ ችሎት ፊት ከመቅረባቸው በፊት ለ30 ደቂቃ ያህል ጠበቆቻቸው ጋር እንዲወያዩ የተፈቀደላቸው ሱኪ የጤንነታቸው ሁኔታ […]

ከአንድ ክፍለ ዘመን በኋላ የተጠየቀው ይቅርታ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 20፣ 2013 ከአንድ ክፍለ ዘመን በኋላ የተጠየቀው ይቅር ጀርመን በቅኝ ግዛት ዘመን በናሚቢያ ላይ የዘር ማጥት ወንጀል መፈጸሟን ባአደባባይ አምና በመቀበል ይቅርታ ጠየቀች፡፡ የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄይኮ ማስ በ20ኛ ክፍለ ዘመን መባቻ ሀገራቸው ናሚቢያን በቅኝ ግዛት በምታስዳድርበት ወቅት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን መግደሏን በማስታወስ የሀገሬው ሰዎች ይቅር እዲሏቸው ጠይቀዋል፡፡ የውጭ […]

የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን በድብቅ ጋብቻ መፈጸማቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23፣ 2013 የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን በድብቅ ጋብቻ መፈጸማቸው ተሰማ:: ይህ ጋብቻ ለቦሪስ ጆንሰን ሦስተኛቸው ሲሆን ለባለቤታቸው ሲሞንድስ የመጀመሪያቸው ነው የ56 ዓመቱ የብሪታንያ (ዩኬ) ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ከ33 ዓመቷ ካሪ ሲሞንድስ ጋር በዛሬው ዕለት በዌስትሚንስትር ባለው ቤተክርስቲያን በድብቅ ጋብቻ መመስረታቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ጋብቻው በድብቅ የጠቅላይ ሚንስትሩ እና […]

ቻይና በቤተሰብ ምጣኔ ላይ ትተገብረው የነበረውን የሁለት ልጅ ፖሊሲ ልታሻሽል ነው፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23፣ 2013 ቻይና በቤተሰብ ምጣኔ ላይ ትተገብረው የነበረውን የሁለት ልጅ ፖሊሲ ልታሻሽል ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናትን ዋቢ ያደረገው የሺንዋ ዘገባ መንግስት ጥንዶች ሶስት ልጆችን እንዲወልዱ ሊፈቅድ መሆኑን ያመለክታል፡፡መንግስት ከዚህ በፊት ጥንዶች ሁለት ልጆች ብቻ እንዲኖራቸው የሚያስገድድውን ፖሊሲ ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ አሁን ላይም ይህን ፖሊሲ በመቀየር ጥንዶች ሶስት ልጆችን እንዲወልዱ የሚፈቅደው የውሳኔ ሃሳብ […]

ህንድ በ39 ቀናት 100 ሺህ ዜጎቿን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ አጣች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25፣ 2013  በህንድ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር ከ400 ሺህ በላይ ሲያሻቅብ ከዚህም ግማሽ ያህሉ ሞት በሁለተኛው ዙር ወረርሽኝ የተከሰተ ነው ተባለ፡፡ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ የተመታችው ህንድ እስካሁን ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ መጠቃታቸውን ይፋ አድርጋለች፡፡ በህንድ 400 ሺህ 312 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ህይዎታቸውን ሲያጡ ከነዚህ መካከል 100 ሺህ የሚሆኑት የሞቱት በ39 ቀናት […]

በኢራቅ በኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ማዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6፣ 2013 በኢራቅ በኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ማዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተሰማ፡፡ በማገገሚያ ማዕከሉ በተቀሰቀሰው ቃጠሎ ከ64 በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ 70 የሚሆኑት ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀገሪቱ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡ ፖሊስ የእሳት አደጋው መንስኤ በውል ባይታወቅም በሆስፒታሉ የሚገኝ ኦክስጂን መፈንዳት የአደጋው ሳይሆን እንዳልቀረ ነው የገለጸው፡፡ አደጋውም […]