loading

  አቶ ገዱ አንድአርጋቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ አቶ ለማ መገርሳ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር እና እንጂነር አይሻ መሀመድ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽ ልማት ሚኒስትር በመሆን ተሾሙ። ይህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ነው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አቅራቢነት የቀረበለትን የሚኒስትሮች ሹመት ነዉ ያፀደቀው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ለአራት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ለአራት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ። በዚሁ መሰረት  ቀድሞ የኦዲፓ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የነበሩትን ዶ/ር አለሙ ስሜን የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቀድሞ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽ ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ጃንጥራር አባይን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር ቀድሞ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰመስተዳድር […]

የሴቶችን ተጠቃሚነት እና እኩልነትን ለማረጋገጥ የተቀናጀና ትብብርን መሰረት ያደረገ እንቅስቃሴ” ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ

በኢትዮጵያ የሴቶችን ተጠቃሚነት እና እኩልነትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ የተቀናጀና ትብብርን መሰረት ያደረገ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አስገነዘቡ። “መተባበር ለላቀ ውጤት” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው እና በሥርዐተ ጾታ እኩልነት እና ሴቶችን በማብቃት ዙሪያ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የውይይት መድረክ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ አዳራሽ ዛሬ ረፋድ ላይ ሲጀመር ፕሬዚዳንቷ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተፈጠረውን መልካም […]

አዲስ አበባ  ዘመናዊ ቤተ መፅሐፍት ለገነባላት ነው

አዲስ አበባ  ዘመናዊ ቤተ መፅሐፍት ለገነባላት ነው። የቤተ-መፅሐፍት ግንባታው አራት ኪሎ ከፓርላማ ፊትለፊት ከአርበኞች ህንፃ ጎን የሚገነባ  ሲሆን በ38,687 ካሬ ሜትር ላይ ያርፋል ተብሏል፡፡ በአንድ ጊዜ 3ሺህ 500 ሰው የማስተናገድ አቅም ያለውና በቀን እስከ 10,000 ሰው መቀበል የሚችለው ማዕከሉ ለህፃናት እና አዋቂዎች የሚሆን  የማንበቢያ እና የአረንጓዴ ስፍራ አለው ነው የተባለው፡፡ እንደ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ገለፃ […]