በኮፓ ኢጣሊያ ግማሽ ፍፃሜ ሚላን ከላትሲዮ በአቻ ውጤት ሲለያዩ ዛሬ ምሽት ሌላኛው ግጥሚያ ይደረጋል፡፡
ኤስ ሚላንን ያስተናገደው ላትሲዮ ያለግብ በአቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ መቐለ ከጅማ አባ ጅፋር ይጫወታሉ
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ መቐለ ከጅማ አባ ጅፋር ይጫወታሉ የሊጉ የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ተስተካካይ ጨዋታ በመቐለ 70 እንደርታ እና ጅማ አባ ጅፋር መካከል ትግራይ ስታዲየም ላይ ቀን 9፡00 ላይ ይጫወታሉ፡፡ በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ የሚሰለጥኑት መቐለ፤ በተከታታይ ስምንት ጨዋታዎች ላይ ድልን ያሳኩ ሲሆን ዘጠነኛውን ድል በጅማው ቡድን ላይ በመቀዳጀት የሊጉን መሪነት ከተከታዮቻቸው በነጥብ ርቀው ያስቀጥላሉ […]
ከ23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለ33 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረበ
ከ23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለ33 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረበ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን በመጋቢት 12 ቀን 2011 ዓ.ም ከማሊ አቻው ጋር ላለበት ጨዋታ 33 ተጫዋቾች በዕጩነት የተመረጡ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ ተጫዋቾቹ የካቲት 26/2011 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚገኘው የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተገኝተው ሪፖርት […]