loading
የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች የሰላም ሳምንት አወጁ

የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች የሰላም ሳምንት አወጁ የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች እስከመጪው እሁድ ጥር 5 ቀን  2011 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የሰላም ሳምንት ማወጃቸው ተነግሯል። በዚህ የሰላም ሳምንት ወቅትም የሰላም እና የመቻቻል የውይይት መድረኮችን ጨምሮ  የተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚካሄዱ መሆኑንም ነው ያስታወቁት። በኢትዮጵያ መረጋጋት እና ዘላቂነት ያለው ሰላም እንዲሰፈን የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም ነው የጉጂ ኦሮሞ […]

ላልይበላን በቀንና በማታ መጎብኘት የሚያስችል የአረንጓዴ ብርሃን ቴክኖሎጂ ሊተገበር ነው ተባለ

ላልይበላን በቀንና በማታ መጎብኘት የሚያስችል የአረንጓዴ ብርሃን ቴክኖሎጂ ሊተገበር ነው ተባለ፡፡ ከፍተኛ የቱሪዝም ፍሰትን የሚጨምር ነው የተባለው ይኸው ቴክኖሎጂ ተግባራዊ የሚደረገው ከአየር ላንድ መንግስት ጋር በመተባበር ነው። የአየር ላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናትን በጎበኙበት ወቅት የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንዳሉት ቴክኖሎጂው በአክሱም ፣ሐረር እና አዲስ አበባ ላይ ተግባራዊ ይደረጋል። የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር እንደተናገሩት አየር ላንድ […]

የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም ሙዚየም ዛሬ ተመረቀ።

የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም ሙዚየም ዛሬ ተመረቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም ሙዚየምን ዛሬ አስመረቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅርሶችን ጠብቃና ተንከባክባ እዚህ አድርሳለች ብለዋል። አሁን ያለው […]

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ወደ ሽሬ አቅንተዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ወደ ሽሬ አቅንተዋል። ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ሽረ ከተማ ሲደርሱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የከተማው ነዋሪ ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። ዛሬ ሽሬ ከተማ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የከተማው ነዋሪ ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። ወይዘሮ ዝናሽ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ለሚሰራ […]

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ተወያዩ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ተወያዩ፡፡ ሀበሻ ለፍቅር የሚል ማህበር ያቋቋሙት የኮሚኒቲ አባላቱ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በኢትዮጵያ  ስላለው የለውጥ እንቅስቃሴ እና በዳያስፖራው ተሳትፎ፣ እንዲሁም ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ባለው ለውጥ ደስተኞች መሆናቸውን የገለጹት የኮሚኒቲ አባላቱ ለውጡ በመካከለኛውና በታችኛው እርከንም ሊተገበር ይገባል ብለዋል፡፡ በሀገሪቱ የሚስተዋለውን ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከላከል […]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአዲስ አበባ በ43 ሚሊዮን ብር ወጪ የደህንነት ካሜራዎችን እየገጠምኩ ነው አለ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአዲስ አበባ በ43 ሚሊዮን ብር ወጪ የደህንነት ካሜራዎችን እየገጠምኩ ነው አለ፡፡ በመዲናዋ ከቀይ ሽብር ሰማዕታት ሀውልት  እስከ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አደባባይ ቁጥራቸው 140 የሆኑ የደህንነት ካሜራዎች መገጠማቸው ተነግሯል፡፡ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱልባሲጥ አህመድ፣ የመጀመሪያው ዙር የከተማዋ የደህንነት ካሜራ ገጠማና ስራ 90 በመቶ  ተጠናቋል ብለዋል። ገጠማቸው […]

የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ። ከመላው ሃገሪቱ የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች የተሳተፉበት ሃገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል ፡፡ በኮንፈረንሱ ላይ ለወጣቱ ትውልድ ሃገራዊ እሴቶችን በማውረስ ዘመናዊነትን በጥበብ እና በብልሃት እንዲላበስ፥ የሃገር ሽማግሌዎች ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል አሳስበዋል። ሚኒስትሯ የሃገር ሽማግሌዎች ሰላምን ከማስፈንና […]

በቡራዩ  ከተማ  የእሳት አደጋ በንብረ ትላይ  ጉዳት አደረሰ፡፡

በቡራዩ  ከተማ  የእሳት አደጋ በንብረ ትላይ  ጉዳት አደረሰ፡፡ በቡራዩ ከተማ ለኩ ኩሌ ቀበሌ ከሌሊቱ 8 ሰአት ከሰላሳ ላይ ኢንተማ ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሻማ የሚያመርት ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ ወድሟል፡፡ የቡራዩ  ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መርጊያ ሁንዴሳ ለአርትስ ቴሌቭዥን  እንደተናገሩት በእሳት አደጋው  ከፋብሪካው አቅራቢያ የሚገኙ ሁለት  ሱቆች ተቃጥለዋል፡፡ በቃጠሎ አደጋው […]