loading
ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ እርሳቸውን ተክተው ከተሾሙት በመንግታቱ ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይ ጋር መከሩ

ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ እርሳቸውን ተክተው ከተሾሙት በመንግታቱ ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይ ጋር መከሩ፡፡ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት የአፍሪካ ህብረት ልዩ  ተወካይ ሆነው የተሾሙትን ሀና ሰርዋ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ልዩ ተወካይዋ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅን በመተካት የተሾሙ ሲሆን የጉብኝታቸው ዓላማም ለፕሬዝዳንቷ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት ለማስተላለፍና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር ነው ተብሏል። […]

ኢትዮጵያዊያን አምባሳደሮች አመታዊ  ጉባኤያቸውን እያካሄዱ ነው ፡፡

ኢትዮጵያዊያን አምባሳደሮች አመታዊ  ጉባኤያቸውን እያካሄዱ ነው ፡፡ ኢትዮጵያን በውጭ የሚወክሉ አምባሳደሮች ቆንስላ ጄኔራሎች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጄኔራሎች የሚሳተፉበት ጉባኤ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነው፡፡ ጉባኤው  በዋናነት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት  እና በውጭ የሚገኙ ሚሲዮኖች የስራ እንቅስቃሴ ፣የሚያጋጥሙ  ችግሮች እና መፍትሄዎቸቻው ላይ ያተኩራል ተብሏል፡፡ ሌላው የውይይቱ አጀንዳ ክልላዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች በኢትዮጵያ እና በጎረቤት አገራት […]

በአማራና ትግራይ ህዝቦች መካከል ግጭትም የግጭት ፍላጎትም የለም አሉ የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች

በአማራና ትግራይ ህዝቦች መካከል ግጭትም የግጭት ፍላጎትም እንደሌለ የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ገለጹ። የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በተለያዩ አካባቢዎች ሲያደርጉት የነበረውን የሰላም ጉዞ አስመልክቶ በአዲስ አበባ የማጠቃለያ መድረክ አካሄደዋል። በመድረኩ ላይም ከተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች ተሳትፈዋል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና […]

በምዕራብ ኦሮሚያ ሶስት ዞኖች 18 የመንግስትና የግል ባንኮች ተዘረፉ

በምዕራብ ኦሮሚያ ሶስት ዞኖች 18 የመንግስትና የግል ባንኮች ተዘረፉ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ፣ ቄለም እና ሆሮ ጉዱሩ ዞኖች በሚገኙ 18 የመንግስት እና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታውቋል። የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ዝርፊያው የተፈጸመው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ቅርንጫፎች እንዲሁም በኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ […]

የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይትና ድርድር የሚመራበት ረቂቅ ደንብ ፀደቀ

የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይትና ድርድር የሚመራበት ረቂቅ ደንብ ፀደቀ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ጋር በቀጣይ የሚያደርጉት ውይይትና ድርድር የሚመራበት 16 አንቀጽ ያለው ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይተው ማፅደቃቸውን፣ በውይይቱ ከተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለማወቅ መቻሉን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ፓርቲዎቹ ከዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት በጉዳዩ ላይ በጋራ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ በውይይቱ […]