loading
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር በአዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ፋና እንደዘገበዉ አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር በቁጥጥር ስር የዋሉት በዛሬው እለት አዲስ አበባ አትላስ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነው። የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት በትናንትናው እለት ባካሄደው አስቸኳይ የአቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት ከአቶ አብዲ በተጨማሪ የ6 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብትን አንስቷል።      

ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ የ1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ተፈቅዶላታል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እንዳሉት ድጋፉ በቀጥታ የሀገሪቱን በጀት የሚደግፍ ነው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የዓለም ባንክን ጨምሮ ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት  በ97 በኢትዮጵያ በተካሄደው ምርጫ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ ለቀጥታ በጀት የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አድርገው አያውቁም፡፡ ለገንዘቡ መገኘት አሁን በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ ዋኛው ምክንያት መሆኑንም ዶክተር አብይ ተናግረዋል፡፡ የዓለም ባንክ ግሩፕ ፕሬዝዳንት ጂም ያንግ ኪም በበኩላቸው […]

አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ ከ27 አመታት በኋላ ዛሬ አዲስ አበባ ገባች::

አርቲስ አለም ፀሐይ ወዳጆ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የጥበብ አፍቃሪዎችና የቀድሞ የስራ ባልደረቦቿ አቀባበል አድርገውላታል፡፡ በተለያዩ የጥበብ ስራዎች የምትታወቀው አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ ዘመን ተሻጋሪ የሆኑ በርከት ያሉ የዘፈን ግጥሞቿ በታዋቂ አቀንቃኞች ተዘፍኗል። ከጥበብ ተልይቼ መኖር አልችልም የምትለው አርቲስቷ በአሜሪካን ጣይቱ የተሰኘ የጥበብ ማዕከል መስርታ የግጥም ምሽቶችን ድራማዎችንም በማዘጋጀት የጥበብ ስራዋን ያለዕረፍት ስትከውን ለ2 […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጥቅምት ወር መጨረሻ ለይ ጀርመን ሊጓዙ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከጀርመኗ ቻንስለር መራሂተ መንግስት ወይዘሮ አንግላ መርከል ጋር በስልክ አውርተዋል፡፡ የጠቅለይ ሚንስቴር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በገፃቸው እንዳስነበቡት ቻንስለር መርከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባጭር ጊዜ እያካሄዱ ላሉት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሪፎርም ስራዎች በተለይም ከኤርትራ ጋር ለተፈጠረው ሰላም አድናቆታቸውን በመግለጽ እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋቸዋል፡፡ ቻንስለሯም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ጀርመን ተገኝተው […]

ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሆናቸው ልጃገረዶች የካንሰር መከላከያ ክትባት በጥቅምት ወር መሰጠት ሊጀመር ነው፡፡ 

በአገር አቀፍ ደረጃ ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሆናቸው ልጃገረዶች በመደበኛነት የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባትን ከጥቅምት 2011 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማትና በሚዘጋጁ ጊዜያዊ የክትባት ማዕከሎች ሊሰጥ መሆኑን የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በድረገጹ አስታዉቋል፡፡ የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወካይ አቶ አስናቀ ዋቅጅራ የማህጸን በር ካንሰር በሽታ በአገራችን ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በስፋት በወሊድ ዕድሜ ክልል የሚገኙ […]

የመንግስት ባለስልጣናት ቪ8 ተሽከርካሪዎችን ከተማ ውስጥ እንዳይጠቀሙ የሚከለክለው መመሪያ በቀጣዩ ሳምንት ተግባራዊ መሆን ይጀምራል

  ኤፍ.ቢ.ሲ  እንደዘገበዉ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የሌሎች ተቋማት ሀላፊዎች ቪ8 ተሽከርካሪዎችን ከተማ ውስጥ እንዳይጠቀሙ የሚከለክለው መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ ነው። መመሪያው ባለስልጣናቱ እና የስራ ሀላፊዎቹ ከዚህ ቀደም በከተማ እንቅስቃሴ ወቅት ይጠቀሙባቸው የነበሩ ቪ8 ተሽከርካሪዎችን ለመስክ ስራ ብቻ እንዲጠቀሙ የሚደነግግ መሆኑንም የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሐጂ ኢብሳ በሰጡት መግለጫ፥ […]

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ቁጥር ወደ 30 ለማድረስ እየሰራሁ ነው አለ፡፡

በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ቁጥር ስድስት ደርሷል፡፡ የፓርኮቹ መገንባት እና ስራ ላይ መዋል የኢንቨስትመንት ዘርፉን ውጤታማ እንደሚያደርግ እና አሁን ካሉት ስድስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደስራ የገቡ እና በቅርቡ ስራ የሚጀምሩ መኖራቸውን በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተካ ገብረ እየሱስ ተናግረዋል፡፡ የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጥቅምት 2011 ስራ የሚጀምር ሲሆን በቂሊንጦም የመድሃኒት ማምረቻ ኢንዱስተሪ ፓርክ ሊገነባ መሆኑን ሰምተናል፡፡ […]

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በ2010 በጀት አመት 3.7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አገኘው አለ፡፡

ይህን ያለው ኢንቨስትመንት ኮሚሽኑ ዛሬ ባቀረበው የአመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ነው፡፡ የተገኘው ገቢ ባለፈው አመት ከተገኘው የሚያንስ መሆኑን እና የባለፈው አመት ገቢ 4.1 ቢሊዮን እንደነበረ የኢትዮጲያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በላቸው መኩሪያ ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽኑ በበጀተ አመቱ 4.6 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ያቀደ ቢሆንም 3.7 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው ገቢ ያረገው የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ፣የመድሃኒት […]