ያለምንም የፖለቲካ ልዩነት ለኢትዮጵያ ህልውና በጋራ መቆም አለብን-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ::
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣2013 ዜጎች ያለምንም የፖለቲካ ልዩነት ለኢትዮጵያ ህልውና በጋራ መቆም እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የኢዜማ ፓርቲ አመራርና አባላት “ደሜን ለእናት ሀገሬ” በሚል መሪ ሃሳብ በብሔራዊ ደምባንክ በመገኘት ደም ለግሰዋል። የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የደም ልገሳ መርሃ ግብር የተዘጋጀው ፓርቲው ለሀገሩ ህልውና መስዋዕትነት እየከፈለ ላለው […]