loading
ቦርዱ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት የገጠማቸውን የምርጫ ክልሎች ይፋ አደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት መከሰቱን አረጋግጫለሁ አለ፡፡ ቦርዱ ይህን ያለው በሎጀስቲክስ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ባደረገው ውይይት ነው፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሪፖርታቸውን በዝርዝር ካቀረቡ በኋላ ከፓርቲዎች ጋር በችግሮቹና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡ […]

የግድቡ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ የወቅቱ ወሳኝ ጥያቄ ነው ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2013 በታላቁ የህደሴ ግድብ ግንባታ ዓለም አቀፍ የውሃ ህጎች ላይ የሚመክር 9ኛው ሃገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉባኤ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ተጀመረ። ለሁለት ቀን በሚቆየው ጉባኤ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ዓለም አቀፍ የውሃ ህጎችን መሰረት ያደረጉ ሰባት ጥናታዊ ፅሁፎች በምሁራን ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ታውቋል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ድኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ […]

ኢትዮጵያ የላሙን ወደብ ልትጠቀም ነዉ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4፣ 2013 የኬንያ መንግስት የላሙ ወደብ ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት ሁኔታዎችን እያመቻች መሆኑን ገለጸ:: የኬንያ መንግስት የላፕሴት ኮሪደር ልማት አካል የሆነውን የላሙ ወደብ ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት ሁኔታዎችን እያመቻች መሆኑን ገልጿል። የላፕሴት ኮሪደር ልማት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ሚኒስትር ሜና አኬንዶ በኬንያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ጉብኝት በማድረግ ከአምባሳደር መለስ ዓለም ጋር ተወያይተዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው የኢትዮጵያ […]

በኢትዮጵያ ኮሮና ወረርሽኝ የመያዝና በቫይረሱ የመሞት ምጣኔ መቀነሱ ተነገረ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013 በኢትዮጵያ ኮሮና ወረርሽኝ የመያዝና በቫይረሱ የመሞት ምጣኔ መቀነሱ ተነገረ:: የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው ዓባይነህ በኮሮና ወረርሽኝ የመያዝና በቫይረሱ የመሞት ምጣኔ መቀነሱን አስታውቋል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት መቀነሱ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና ከጤና ሚኒስቴር ጋር ለ15 ወራት ሥጋት ሆኖ በዘለቀው የኮሮና ወረርሽኝ ላይ የተደረጉ የምርምር ጥናቶች […]

ደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ዳግም ወደ ጥብቅ የእንቅስቃሴ እቀባ ተመለሰች::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2013 ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ በሰጡት መግለጫ በሀገሪቱ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ምክንያት ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በ59 በመቶ መጨመሩን ይፋ አድርገዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የምሽት የሰዓት እላፊ እና የአልኮል ሽያጭ ላይ ገደቦችን መጣል ግድ ሆኖብናል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፡፡ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ሲባል ከምሽቱ አራት ሰዓት እስከ ሌሊቱ አስር ሰዓት ያሉ እንቅስቃሴዎች እንዲገደቡ […]

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በምርጫ ጣቢያ 05 የክልል ምክር ቤት የምርጫ ወረቀት በመቀያየሩ ምርጫው ከ 2 ሰዓት ተኩል በላይ ዘግይቷል፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14፣ 2013 በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በምርጫ ጣቢያ 05 የክልል ምክር ቤት የምርጫ ወረቀት በመቀያየሩ ምርጫው ከ 2 ሰዓት ተኩል በላይ ዘግይቷል፡፡ በክፍለ ከተማው ወረዳ 3 በምርጫ ክልል 23 የቦሌ ክፍለ ከተማ የምርጫ ወረቀቶች በስህተት በመላካቸው ነው ምርጫው በሰዓቱ ያልተጀመረው፡፡ በዚህ የምርጫ ክልል ለአዲስ አበባ ክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩት ምክትል […]

ድምጽ በመስጠት ላይ እንዳሉ ምጥ የተያዙት ነፍሰጡር እናት በሰላም ተገላገሉ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14፣ 2013 ድምጽ በመስጠት ላይ እንዳሉ ምጥ የተያዙት ነፍሰጡር እናት በሰላም ተገላገሉ፡፡ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ አበራሽ ጉታ በጠዋቱ ድምጻቸውን ለመስጠት ወደ ሃጤ አንዶዴ ሄጦሳ ዙሪያ ምርጫ ጣቢያ በመምረጥ ላይ እንዳሉ ነበር በምጥ የተያዙት፡፡ በምጥ ላይ እንዳሉ ድምጻቸውን ከሰጡ በኋላ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በሰላም መገላገላቸውን አማራ ሚዲያ […]

በትግራይ እንደተፈፀመ በተሰማው የአየር ጥቃት የተጎዱ ወገኖችን በፍጥነት ወደ ሕክምና ስፍራ ማድረስ አልተቻለም ተባለ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 16፣ 2013 በትግራይ እንደተፈፀመ በተሰማው የአየር ጥቃት የተጎዱ ወገኖችን በፍጥነት ወደ ሕክምና ስፍራ ማድረስ አልተቻለም ተባለ፡፡ ከተጎጂዎቹ መካከል ወደ መቀሌ ሐይደር ሆስፒታል እስካሁን መድረስ የቻሉት አንድ የ2 ዓመት ሕጻን እና 5 አዋቂ ቁስለኞች መሆናቸውን አርትስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ አርትስ ቲቪ ወደ አካባቢው ደውሎ ለማጣራት ባደረገው ጥረት ከመቀሌ በስተምዕራብ 25 ኪሎ ሜትር […]

ምርጫው ዓለም አቀፍ መስፈርትን አያሟላም-ባልደራስ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18፣ 2013 ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ዝቅተኛውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መስፈርት የማያሟላ ነው አለ፡፡ ፓርቲው በፌስቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው ፅሁፍ በተለያዩ ጊዜያት ሳይንሳዊ ጥናቶች አካሂጄ ነው እዚህ መደምደሚያ ላይ ደረስኩት ብሏል፡፡ ምርጫው ችግር እንዳለበት በማሳያነት ካቀረባቸው ምክንያቶች መካከል በድምፅ አሰጣጥ ወቅት የምርጫ አስፈፃሚዎች የገዢው ፓርቲ እንዲመረጥ የሚረዱ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አመሰገኑ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21፣ 2013 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰላማዊ ምርጫ እንዲሳካ አስተዋጽዖ ላደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምስጋና አቀረቡ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ አንድ ሳምንት በኋላ ዛሬ ጠዋት ከፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝቼ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና የወጣችበት ሰላማዊ ምርጫ እንዲሳካ ላደረጉት አስተዋጽዖ […]