loading
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ የምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ እንዲራዘም ወሰነ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ የምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ እንዲራዘም ወሰነ:: ቦርዱ ይህን ውሳኔ ያለፈው በአንደሰንድ የምጫ ክልሎች በተለያዩ ምክንያቶች መራዘሙን መነሻ በማድረግ መሆኑን ተናግሯል፡፡ በዚህም መሰረት በምእራብ፣ በምስራቅ ወለጋ እንዲሁም በቄለም ወለጋና በሆሮጉድሩ ዞኖች 31 ምርጫ ክልሎች መካከል በ24ቱ ምዝገባው ከሚያዝያ 29 – ግንቦት 13 ቀን 2013 ድረስ […]

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ለ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላፉ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27 ፣ 2013 በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ለ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላፉ::በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቨገንሲ ተርክሂን ኢትዮጵያውያን የዛሬ 80 ዓመት ለተቀዳጁት ድል የሚታሰብበት የአርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በዚህ ክስተት ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን ከፋሽስት ወረራ ነፃ ያወጡበት 80ኛ ዓመት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ ብለዋል። በአውሮፓውያኑ 1935 የፋሺዝም ጭቆናን በመጋፈጥ […]

የምንቃወመው መንግስት እንጂ የምንቃወማት ሀገር ልትኖረን አትችልም::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27 ፣ 2013 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እንደጀግኖች እናቶቻችንና አባቶቻችን ሀገራችንን እናስቀድም ሲሉ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት 80 ዓመት የአርበኞች ቀንን አስመልክተው ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ነው፡፡ ጀግኖች አርበኞቻችን ሀገራችንን ከአምስት ዓመቱ የኢጣልያ ወረራ ነጻ ያደረጉበትን ቀን ስናስብ ሶስት ቁምነገሮችን እየተማርን ነው ብለዋ ጠቅላይ ሚኒስትሩ። አንደኛው ከሁሉም በላይ ሀገርን ማስቀደም […]

ህወሃትና ሸኔ በሽብርተኝነት ተፈረጁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወትና ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ አጸደቀ፡፡ ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሂደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው ነው በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያጸደቀው፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በአገር እና በህዝብ ላይ የሽብር ተግባራትን በመፈፀም ላይ በመሆናቸው በሽብርተኝነት መፈረጃቸው አግባብ […]

የወታደራዊ ቅርስ ጥበቃና ሙዚየም ማቋቋም በትውልዱ ላይ የሃገር ፍቅር ስሜት ለማስረጽ አቅም አለው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 የወታደራዊ ቅርስ ጥበቃና ሙዚየም ማቋቋም በትውልዱ ላይ የሃገር ፍቅር ስሜት ለማስረጽ አቅም አለው ተባለ:: የወታደራዊ ቅርስ ጥበቃና ወታደራዊ ሙዚየም በኢትዮጵያ በሚኖረው ፋይዳ፣ ተግዳሮትና መልካም አጋጣሚዎች ዙሪያ የምክክር አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው። በአውደ ጥናቱ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ፍስሃ ወልደሰንበት፣ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ተወካዮችና የቀድሞ […]

በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ 86 በመቶ የሚሆን የቆዳ ስፋት በአጋር አካላቶች እንደሚሸፈን ተገለፀ።

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ 86 በመቶ የሚሆን የቆዳ ስፋት በአጋር አካላቶች እንደሚሸፈን ተገለፀ። የትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ሂደቱ በኋላ የሰብዓዊ ድጋፍ 3.7 ቢሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለማዳረስ እየተሞከረ መሆኑናይህም የሰብዓዊ ድጋፎ ግን አልተዳረሰም የሚለውን ብዥታ እደሚያጠራው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል። በኢትዮጲያ በኩል ቀሪው 14 በመቶ የቆዳ ስፋት ይሸፈናል ነው […]

ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ግዜ የማር ወይንን አስተዋወቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 በኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ተቋም እና በጎንደር ዩኒቨርስቲ ትብብር ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረተ አዲስ የማር ወይን የቅምሻ እና የማስተዋወቂያ ሥነ ሥርዓት ትናንት ማምሻውን በስካይ ላይት ሆቴል ተካሄዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ ጥናታዊ ትንታኔ፣ ውይይት፣ ማብራሪያ፣ ምሥጋና፣ ወደ ፊት የታሰቡ ዕቅዶች እና የግብይት መሥመሩን መቀላቀያ ሐሳብ ቀርበውበታል። የጥናቱ ባለቤት ፕሮፌሰር ብርሃኑ አንዷለም እንደገለፁት […]

በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው ያለመግባባት መፈታቱ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው ያለመግባባት መፈታቱ ተገለፀ:: በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው ያለመግባባት በሀገር ሽማግሌዎች እና በመንግሥት ጥረት መፈታቱ ተገልጿል። ስምምነቱን ተከትሎም ቅራኔ ውስጥ የነበሩት አካላት በጋራ የአፍጥር መርሀግብር በሸራተን አዲስ አከናውነዋል። የመጅሊስ አባላት ወደ አንድ እንዲመጡ ለሠሩ ሽማግሌዎች ምስጋና ቀርቧል። በቀጣይም ገለልተኛ አስመራጭ […]

ምክር ቤቱ የአውሮፖ ህብረት 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ላለመታዘብ የያዘውን አቋም ዳግም እንዲመለከት ጠየቀ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 ምክር ቤቱ የአውሮፖ ህብረት 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ላለመታዘብ የያዘውን አቋም ዳግም እንዲመለከት ጠየቀ::የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአውሮፖ ህብረት 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ላለመታዘብ የያዘውን አቋም ዳግም እንዲያጤን ጠየቀ።ምክር ቤቱ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ውይይት ባካሄደበት ወቅት የተደረሰበት የአቋም ላይ መግለጫ መስጠቱን ዋልታ ዘግቧል፡፡ ብረት ምርጫውን ላለመታዘብ የያዘው አቋም […]

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ:: በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በተደረገ ክትትል በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ከእነ ተጠርጣሪዎቹ ተያዘ፡፡እንደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፃ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረው ዶላር የተያዘው ሃሙስ ለአርብ አጥቢያ በአዲስ አበባ የካ […]