loading
ሃገር በቀል ዕውቀቶች በምርምር አልፈውና በቴክኖሎጂ ተደግፈው ወደ ህብረተሰቡ ለማውረድ የሚያስችል መመርያ ፀደቀ

ሃገር በቀል እውቀቶች በምርምር አልፈውና በቴክኖሎጂ ተደግፈው ወደ ህብረተሰቡ ለማውረድ የሚያስችል መመርያ ማፅደቁን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመማር መስተማር ስራዎቻቸው በተጨማሪ የአካባቢያቸውን ማህበረሰብ እና ከዛም አልፎ ሀገሪቱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ግኝቶችን በምርምር ማምጣት ይጠበቅባቸዋል። በሀገሪቱ የሚገኙ አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎችም በተወሰነ ደረጃ ይህን አብይ ጉዳይ ለማሟላት ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ይታወቃል። ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ዪኒቨርስቲዎች […]

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሰላም በሚል መሪ ቃል ኮንፈረንስ ተካሄደ።

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሰላም በሚል መሪ ቃል ኮንፈረንስ ተካሄደ። በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመጀመሪያው የሰላም ኮንፈረንስ ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተካሂዷል። ”ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሰላም” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ኮንፍረንስ ላይ ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተወከሉ የአስተዳደር አካላትና ተማሪዎች ተሳትፈዋል። የሰላም ሚኒስትር ዴእታ ወይዘሮ አልማዝ መኮነን በኮንፈረንሱ ላይ፥ ሀገራችን ከበርካታ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ውህደት የተገነባች በመሆኗ አንዳችን ላንዳችን […]

What should we expect from 5G?

What should we expect from 5G? Every day, global media publish news that creates a picture of an unstoppable technology race among the world’s economic giants. The assumption is, the winner will take it all – substantial economic profits and technological dominance. However, as the United States and China enter a new trade war, the […]

የኮሮና ቫይረስ ትምህርት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ለመከላከል የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ ተደረሰ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 19 ፣ 2012 የኮሮና ቫይረስ ትምህርት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ለመከላከል የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ ተደረሰ:: የትምህርት የወደፊት ዕጣ ፈንታን የሚመለከተው ዓለም አቀፉ የባህል ተቋም ዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ኮሚሽንን 2ኛ ስብሰባ ተካሂዷል።በዚህም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆኖነዋል።በውይይቱም የኮረሮ ቫይረስ በትምህርትና ልማት ላይ በረጅም ጊዜ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ […]

የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ለሦስት ምሁራን የፕሮፌስርነት ማዕረግ ሰጠ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በማስተማርና ምርምር ስራዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሦስት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታዉቋል። የዩኒቨርስቲው ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዘውዱ እምሩ ለኢዜአ እንደተናገሩት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረጉ የተሰጠው በተሰማሩባቸው የማስተማርና የምርምር መስኮች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ምሁራን ነው። የፕሮፌሰርነት ማዕረጉ የተሰጠውም ለዶክተር ይሄነው ገብረስላሴ በአፈር ሳይንስ ፣ ለዶክተር አብርሃ ፀጋዬ በፕላንት ኢኮሎጂ ኤንድ ኢትዮ ቦታኒ እንዲሁም ለዶክተር ከፍያለው አለማየሁ በእንስሳት ብዜት የትምህርት ዘርፎች የላቀ ውጤት በማስመዘገባቸው እንደሆነ አብራርተዋል። ምሁራኑ በዩኒቨርስቲው በመማር ማስተማር፣ ችግር ፈች ምርምሮችን በማካሄድና ፅሁፎቻቸውን በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገራት በሚገኙ ጆርናሎች በማሳተም እውቅና ያተረፉ በመሆናቸው ነው ብለዋል ። ሙሁራኑ በተጨማሪም ተማሪዎችን በማማከር፣ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ተመድበው በሰጡት የአመራር ብቃትና ባስመዘገቡት ውጤት ተመዝነው የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጣቸው መደረጉን አስረድተዋል ።የምሁራኑን አስተዋጽኦ የዩኒቨርስቲው ሴኔት ገምግሞ ያቀረበውን ውጤት በስራ አመራር ቦርድ በማፀደቅ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንደተሰጣቸው ከዶክተር ዘውዱ ገለፃ ለማወቅ ተችሏል ።

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2012 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ ጀመሩ ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2012 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ ጀመሩ :: በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርቱን እንዲከታተሉ እና ከአማካሪዎቻቸው ጋርም የሚገናኙበት ምቹ ሁኔታ በመኖሩ ትምህርታቸውን ማጠናቀቅ ጀምረዋል።በሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ኤባ ሚጀና፣ የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ባይኖርም ጅማ […]

በመዲናዋ “አንድ መምህር ለአንድ ቤተሰብ” በሚል የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጀመረ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ14፣ 2012 በመዲናዋ “አንድ መምህር ለአንድ ቤተሰብ” በሚል የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጀመረ::የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ከወጣቶች እና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ እንዲሁም የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር ጋር በመተባበር ነው መርሃ ግብሩን የጀመረው። ይፋ በተደረገው የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የሰራ ኃላፊዎች፣ የከተማው […]

የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ከተከሰተ ግዜ ጀመሮ በራስ ተነሳሽነት የሚደረግ ትምህርት ወይም ሰልፍ ለርኒግ መጨመሩን የደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ገለፁ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ28፣ 2012  የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ከተከሰተ ግዜ ጀመሮ በራስ ተነሳሽነት የሚደረግ ትምህርት ወይም ሰልፍ ለርኒግ መጨመሩን የደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ገለፁ::ሰልፍ ለርኒግ ወይም እራስን በራስ የማሰተማር ስራ የኮቪድ 19 በሀገራችን ከተከሰተ ግዜ ጀምሮ በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች መታየቱን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡ዓለማት እራስን በራስ ከማስተማር ጋር ተያይዞ ረዥም ርቀት መጓዛቸውን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ እንደ እትዮጵያ ባሉ በማደግ ላይ በሚገኙ […]