loading
በመዲናዋ የአዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ተጧጡፈዋል

በመዲናዋ አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ተጧጡፈዋል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 1.4 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር ስፋት ያለውን የሽሮሜዳ ቁስቋም አስፓልት መንገድ እንዲሁም  ከ5 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመትና 25 ሜትር ስፋት ያለው የአቃቂ ቱሉ ዲምቱ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶችን አስጀምሯል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊው ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተቋማቱ ሀላፊዎች  እና ተወካዮች ጋር በዘርፉ ማሻሻያዎች ዙሪያ ነው የተወያዩት ፡፡ ውይይቱ የተደረገው ዘርፉ  ብቁ ተፎካካሪ እንዲሆን እና ኢኮኖሚን ለማሳደግ ያለውን ሚና ለማጠናከር ነው ተብሏል፡፡ ውይይቱ እስካሁን በፋይናሱ ዘርፍ በተደረጉት ለውጦች፣ የፖሊሲ እና የአስተዳደር ችግሮችን መለየት እና ኃላፊነቶች ግልፅ ማድረግ  ላይ ያተኮረ እንደነበርም […]

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመች

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመች የውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የመግባቢያ ሰነዱን  የተፈራረመው ገልፍ የኤሌክትሪክ ትስስር ከተባለ የባህረ ሰላጤው አባል ሀገራት  የኃይል አቀርቦት ተቋም እና የዓለም አቀፉ የኃይል ትስስር ድርጅት ጋር ነው፡፡ ሰነዱ የሃይል አቅርቦትን መሰረት ያደረገ ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል  ነው ተብሏል፡፡ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይም  የውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር […]

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቤቶች ልማት ዘርፍ ላይ ከሚሳተፉ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር ተወያዩ

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቤቶች ልማት ዘርፍ ላይ ከሚሳተፉ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር ተወያዩ የአዲስ አበባ  ከተማ ምክትል ከንቲባ  ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቤቶች ልማት ዘርፍ ላይ ከሚሳተፉ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር ተወያዩ። ምክትል ከንቲባው በቤቶች ልማት ላይ ተሳታፊ ከሆኑ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር በያዝነው በጀት ዓመት በሚተላለፉ 134 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች ዙሪያ […]

ኢትዮጵያና ቱርክ በባህልና በቅርስ ጥበቃ ዘርፍ በትብብር እንደሚሰሩ ተገለጸ

ኢትዮጵያና ቱርክ በባህልና በቅርስ ጥበቃ ዘርፍ በትብብር እንደሚሰሩ ተገለጸ ይህ የተባለው በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳሁን የተመራ የልዑካን ቡድን ከቱርክ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ፕሬዝዳንት ሰርዳር ካም ጋር አንካራ ላይ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡ ሁለቱ አገራት በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ትብብራቸውን ይበልጥ በማጠናከር ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። በዚህ ወቅት ዶ/ር ሂሩት የቱርክ የትብብር ኤጀንሲ በኢትዮጵያ […]

በአዲስ አበባ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ ተጠናቅቀው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ይደረጋል ተባለ።

በአዲስ አበባ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ ተጠናቅቀው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ይደረጋል ተባለ የከተማው ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በመንገድ ግንባታ ዘርፍ ለሚሳተፉ የአልሚ እና አማካሪ ድርጅቶች የከተማ አስተዳደሩ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ ምክትል ከንቲባው አስተዳደሩ በመንገድ ግንባታው ዘርፍ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ከገንቢ እና አማካሪ ድርጅቶች ጋር ተቀራርቦ ከመስራት በተጨማሪ ግንባታዎችን በሚያጓትቱ ድርጅቶች ላይ እርምጃ […]

ስድስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ለጨረታ ሊቀርቡ መሆኑ ተነገረ።

ስድስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ለጨረታ ሊቀርቡ መሆኑ ተነገረ በኢትዮጵያ መንግስትና በግል አጋርነት የሚተገበሩ ስድስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናታቸው ተጠናቆ ለጨረታ ሊቀርቡ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚንስትር ዴኤታው ዶክተር ተሾመ ታፈሰ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት  መግለጫ እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ያቋቋመው ቦርድ በመንግስትና የግል አጋርነት ይተገበራሉ ብሎ ከለያቸው 16 ፕሮጀክቶች ውስጥ አስራ ሶስቱ የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክቶች […]

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ውዝፍ ክፍያ ማስከፈል ጀምሬያለሁ አለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ውዝፍ ክፍያ ማስከፈል ጀምሬያለሁ አለ የአገልግሎት ክፍያ በወቅቱ ካልከፈሉ ደንበኞች እስካሁን 340 ሚሊየን ብር መሰብሰቡንም ተናግሯል የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እንደተናገሩት አገልግሎቱ ከዚህ በፊት ያልከተፈሉ ውዝፍ ክፍያዎችን ተከታትሎ እየሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል። አሁን ከሰበሰበው በተጨማሪ ከ350 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ከደንበኞች ያልተሰበሰበ ውዝፍ ክፍያ አለኝ ይላል አገልግሎቱ። የማስከፈሉ ስራ መቀጠሉን […]