loading
ኢትዮጵያ ለሽምግልና ልትቀመጥ ነዉ፡፡

ኢትዮጵያ የምትሸመግለዉ ኤርትራንና ጅቡቲን ነዉ፡፡ የዉጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በሰጡት መግለጫ በሁለቱ ሀገራት መሀከል ያለዉ ችግር ተቀርፎ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲሰፍን ኢትዮጵያ ለጅቡቲዉ ፕሬዝዳንት መልክት ልካለች ብለዋል፡፡ ሁለቱ ሀገራትም ለሽምግለና ለመቀመጥ መልካም ፍላጎትን አሳይተዋል ተብሏል፡፡

ሱዳንና ኢትዮጵያ የድንበር ቁጥጥርን ለማስወገድ ተስማሙ::

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር የምታደርገውን ቁጥጥር ለማቆም ቁርጠኛ መሆንዋን አስታውቃለች፡፡ ሱዳን ከውሳኔ ላይ የደረሰችው የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሀፊዝ አብዱል ራህማን ከኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በካርቱም በገቡት ስምምነት መሰረት ነው፡፡ የሀገራቱን ግንኙነት እንደሚያጠናክር የተነገረለት ስምምቱ እውን የሚሆነውም በሁለቱ ሀገራት የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ኡሁሩ ኬንያታ ደቡብ ሱዳኖችን አድንቀዋል፡፡

የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ይበል የሚያሰኝ ሲሉ አሞካሽተውታል፡፡ በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ ሀይሎች ከጦርነት ይልቅ ሰላምን እንደ አማራጭ መውሰዳቸው ብልህነት ነው ያሉት ኬንያታ ሀገራቸው ይሄን የተቀደሰ ሀሳብ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል፡፡ ሱዳን ካርቱም ላይ የተደረገው ስምምነት የፕሬዝዳንት ሳልቫኪር የቀድሞው ምክትላቸውና የአሁኑ ተቀናነቃኛቸው ዶክተር ሪክ ማቻር ወደ […]

የዚምባብዌ መንግስት የተቋዋሚ አባላትን ፍርድ ቤት አቆመ፡፡

ተቃዋሚዎቹ የተከሰሱት በዚምባቡዌ በተካሄደዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኤመርሰን ምናንጋግዋ ማሸነፋቸዉን ተከትሎ በሀገሪቱ በተቀሰቀሰዉ አመጽ እጃችሁ አለበት ተብለዉ ነዉ ፡፡ የኬንያዉ ዴይሊ ኔሽን እንደዘገበዉ 27 የተቃዋሚ ፓርቲ አበላት ላይ የዚምባብዌ አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡ ከተከሳሾቹ መካከል ዘጠኙ ሴቶች ናቸዉ ፡፡ ፕሬዝደንቱ በአንድ በኩል የሙቭመንት ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ፓርቲን ለአመጹ መነሻ ነዉ በማለት ሲከሱ በሌላ በኩል በግርግሩ ሳቢያ […]

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት ለማ መገርሳ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ወደ አስመራ የተጓዙበት ጉዳይ በስኬት ተጠናቋል ተባለ፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ የሚመራውና የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ የሚገኙበት የልዑካን ቡድን፣ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ- መንበር ኣቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራውና አቶ ኢብሳ ነገዎ፣ ኣቶ አቶምሳ ኩምሳ፣ ኣቶ ቶሌራ አደባ እና ኣቶ ገመቹ ኣያና የሚገኙበት የልዑካን ቡድን ዛሬ በአስመራ ኤርትራ በመገናኘት ወንድማዊ መንፈስ በተንጸባረቀበትና በሙሉ መተማመን በተካሄደ የእርቅ ውይይት ያሉ ስምምነቶችና […]

ግብጽ ጥንታዊ ቅርሶቿን አስመለሰች፡፡

ግብጽ ከ500 ዓመት በላይ እድሜ ያላቸውን ቅርሶቿን ከእንግሊዝ መረከቧን የሀገሪቱ የባህል ሚኒስትር ኢሳም አብደል ዳይም ተናግረዋል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ቅርሶቹ የጥንታዊት ግብጽን ታሪኮች የሚያሳዩ የድንጋይ ላይ ጽሁፎችና ስዕሎች ናቸው፡፡ አብደል ዳይም እነዳሉት እነዚህ ጽሁፎች እና ስዕሎች በስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሙህዲን አል ካፊጂ በተባለ ጥበበኛ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ግብጽ ከ50 ዓመት በፊት ከ33 ሺህ በላይ […]

ግብጽ እስረኞችን በይቅርታ መፍታቷን ቀጥላለች፡፡

የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ግብጽ በሳምንት ዉስጥ ለሁለተኛ ግዜ እስረኞችን በይቅረታ ፈታለች፡ ታራሚዎቹ ይቅርታዉን ያገኙት በፕሬዝዳንት አብደልፈታ አልሲሲ በኩል ሲሆን ቁጥራቸዉም 1 ሺህ 188 ይሆናል ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር ነዉ የዘገበዉ፡፡ በይቅርታ ከተለቀቁ እስረኞች መካከል 723ቱ ቅደመ ሁኔታ የተቀመጠላቸዉ መሆኑንም ዘገባዉ አመልክቷል፡፡

የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳልህ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ።

የኤርትሪያን ፕሬስ እንደዘገበዉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከኢፌዴሪ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጉብኝቱ ዳግም የተጀመረውን የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እንደሚያግዝም ታምኖበታል። ኢትዮጵያና ኤርትራ ለ20 አመታት አቋርጠውት የነበረውን ግንኙነት ዳግም መጀመራቸው ይታወሳል። በቅርቡም የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ወደ ኤርትራ በማቅናት ከኤርትራው […]

ናይጄሪያ የሰብል ምርት እጥረት አሳስቧታል።

በአፍሪካ በህዝብ ብዛቷ ቀዳሚ የሆነችው ናይጄሪያ በየዓመቱ ስድስት መቶ ሚሊዮን ቶን ሩዝ ለምግብ ፍጆታ ታውላለች። ሲ ጂቲ ኤን እንደዘገበው ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉን የምታስገባው ከቻይና ነው ። የናይጀሪያ የግብርና ተማራማሪዎች በሃገሪቱ ያለውን የምርት እጥረት ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው። ተማራማሪዎቹ ከቻይና የተሻሻለ የሩዝ ዝርያ በማስገባት አርሶ አደሮቹን ምርታማ ለማድረግ ነው እየሰሩ ያሉት። የተሻሻለው ዝርያ ቀድሞ […]