loading
የአሸንዳ ክብረ በአል ከባህላዊ እሴትነቱ ባሻገር ለነጋዴዎች የገቢ ማስገኛ መንገድ ነው ።

አርትስ ቲቪ በመቀሌ ከተማ ያነጋገራቸው ነጋዴዎች በአሸንዳ በአል ነጋዴዎች ልጃገረዶች የሚለብሷቸውን ባህላዊ አልባሳት፣ፀጉርላይ የሚታሰሩ (እንቁ)የሚባሉ ማጌጫዎች ፣ በቀሚስ ላይ የሚደረግ የተገመደ ክር (ድሪ) የአንገትና የጆሮ ጌጣጌጦች በአዘቦቱ ቀን ከሚሸጡበት የ20 እና 30 ብር ጭማሪ አንዳለው ነው የተናገሩት። በአሉን ልጃገረዶች በተለየ መንገድ ስለሚያከብሩት የፀጉር ባለሙያዎችንም ትርፋማ የሚያደርግ እንደሆነ ተመልክተናል ።

በነገው እለት የሚከበረውን የአሸንዳ በአል አስመልክቶ በመቀሌ ከተማ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

የፓናል ውይይቱ አብይ አላማ ያለፉት አመታት የበዓሉን አከባበር መገምገም፣አሸንዳን በአለም አቀፍ ደረጃ ስለማስተዋወቅ እንዲሁም ከዩኔስኮ ጋር የተያያዙ ጥናቶች እና ሀሳቦችን ማንሳት ነው ተብሏል፡፡ የትግራይ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ዘነቡ ሐለፎም እንደገለፁት አሸንዳ ከባህላዊ እና ሃይማኖታዊ አንድምታው በተጨማሪ ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር እንዲሁም ፖለቲካዊ ተሳትፎአቸውን የሚያሳይ የነጻነት ቀን ነው ብለዋል፡፡ በውይይቱ የቀደሙ […]

ተወረወረች ጨረቃ …በመድሃኒዓለም ጫንቃ

ተወረወረች ጨረቃ በመድሃኒዓለም ጫንቃ . ይሄ አዳራሽ ….ኧኸ የማን አዳራሽ የጌታዬ ድርብ ለባሽ። . ይኸው ሲዞር ወገቧ ባቄላ ነው ቀለቧ . ይሄው ወገቤ ነጭ ጤፍ ነው ቀለቤ። በሚለው የልጃገረዶች ጨዋታ ለሚደምቀው አሸንድዬ በላሊበላ ዝግጅት እየተደረገ ነው።

አዲስ ይፋ የሆነው የትምህርት ፍኖተ-ካርታ ትምህርት ሚኒስቴርን ሦስት ቦታ የሚያደራጅ ነው::

አዲስ ይፋ የሆነው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ትምህርት ሚኒስቴርን በሦስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የሚያደራጅ መሆኑ ተጠቆመ። በትምህርት ዘርፍ አስተዳደር ላይ ማሻሻያ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጄይሉ ዑመር እንዳሉት ፍኖተ-ካርታው ብዙ መዋቅራዊ ለውጦችን የያዘ በመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር በሦስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንዲደራጅ የሚያደርግ ነው። በአዲስ መልክ የሚቋቋሙት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና […]

ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ እቃዎችን ማምረት ካልጀመረች የውጭ ምንዛሬ እጥረቷን ልትፈታ አትችልም ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ እቃዎችን ማምረት ካልጀመረች የውጭ ምንዛሬ እጥረቷን ልትፈታ አትችልም ተባለ፡፡ የዉጭ ምንዛሪ እጥረቷን ለመፍታት ድሮን ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ኢንደስትሪ እና የህክምና እቃዎች ማምረት ይኖርባታልም ተብሏል፡፡ ይህ የተባለዉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በኢትዮጵያ የታንዛኒያ አንምባሳደር ከሆኑት ቼንግሬ ሚካማን ጋር በምስራቅ አፍሪካ የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያና ማምረቻ ለማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በመከሩበት ወቅት ነዉ። ሳይንስና […]

የኒውዮርክ ፍርድ ቤት የቀድሞውን የትራምፕን ጠበቃ ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡

የቀድሞው የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠበቃ የነበሩት ሚካኤል ኮሆን ጥፋተኛ የተባሉት በ2016ቱ ምርጫ ለቅስቀሳ ከተመደበው ገንዘብ ህጉ ከሚፈቅደው ውጭ ክፍያ እንዲፈጸም አድርገዋል ተብለው ነው፡፡ ኮሆን በበኩላቸው ድርጊቱን መፈጸማቸውን አምነው ነገር ግን ይህን ያደረኩት ፕሬዝዳንቱ አዘውኝ ነው ብለዋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው የሚካኤል ኮሆን ጠበቃ ይህ ክፍያ ደንበኛየን ኮሆንን ወንወጀለኛ ካስባለ ለምን ፕሬዝዳንት ትራምፕን አያስጠይቅም ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡ […]

በአዲስ አበባ ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች ዛሬ ነፃ የህክምና አገልግሎት ይሰጣል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከዘመን እና ሞጋቾች ድራማ ጋር በመሆን ፥ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት ድረስ በመዲናዋ ጎዳና ላይ የሚገኙ ሰዎች የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋሉ። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ወር በገባ በ16ኛው ቀን በቀጣይነት እንደሚሰጥ እና ወደ ሌሎች ከተሞችም ለማስፋት መታቀዱን የዘመን ድራማ ደራሲ አቶ መስፍን ጌታቸው ተናግረዋል። ሰኔ 16 ቀን በአዲስ አበባ […]

በአዲስ አበባ ከአዲስ አመት በፊት በክፍለከተማና በወረዳ አመራሮች ላይ ለዉጥ ይደረጋል ተባለ፡፡ 

በዚህ ሳምንትም በክፍለከተማ ደረጃ ያሉ ዋና ዋና አመራሮች እንደ አዲስ እንደሚዋቀሩ የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት በድህረ ገፁ አስታዉቋል፡፡ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በወቅታዊ የከተማዋ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ የተጀመረውን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ እና አሁን እየታየ ያለውን ሀገራዊ ተስፋ ለማደናቀፍ እንዲሁም የመዲናችንን ሰላም ለማደፍረስ ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ በመሆኑ ህብረተሰቡ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ደቡብ አፍሪካን ሊጎበኙ ነው፡፡

ኢ.ቢ.ሲ በድረገፁ እንዳስነበበው የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኤስ .ኤ.ቢ.ሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ዶክተር አብይ አህመድ ከቀጠናው ሀገራት ውጭ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት የመጀመሪያው በደቡብ አፍሪካ እንዲሆን ፍላጎት አላቸው፡፡ አቶ ኃይለማርያም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሰርል ራማ ፖሳ አድርሰዋል፡፡ በፀረ አፓርታይድም ይሁን በነጻነት ትግል ወቅት […]