loading
40 የኪነጥበብ ባለሞያዎች በተመረጡ ሦስት የመንግስት ሆስፒታሎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሊሰጡ ነዉ፡፡

40 የኪነጥበብ ባለሞያዎች በተመረጡ ሦስት የመንግስት ሆስፒታሎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሊሰጡ ነዉ፡፡

የበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ ብዙ ታካሚ በሚያስተናግዱ ሆስፒታሎች በጽዳት ፣በኤሌክትሪክና በቧንቧ ጥገና እና በህክምና መሳሪያ ጥገና ላይ ያተኩራል ተብሏል፡፡

“ ዝቅ ብለዉ ከፍ ያደረጉንን መሪዎች ቁጭ ብለን አናይም “ የሚል መሪቃል ያነገቡት የኪነጥበብ ባለሞያዎቹ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋራ በጋራ በሰጡት መግለጫ ፤በጥቁር አንበሳ፣በአለርትና በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከፊታችን ሐምሌ 16 ጀምሮ የበጎፍቃድ አገልግሎቱን መስጠት እንደሚጀምሩ ተናግረዋል፡፡

በጤናጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ጥበቃ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ዳንኤል ገ/ሚካኤል ርህራሄ እንክብካቤና ጥንቃቄ የተሞላበት አገልግሎት በመንግስት ተቋማት እንዲሰጥ ከመንግስት ጎን እንደ አርቲስቶቹ አይነት በጎ ፍቃደኛ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡

አርቲስቶችን በመወከል አርቲስት መስፍን ጌታቸዉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከያዟቸዉ ስራዎች አንዱን የበጀት ጉድለትን በበጎ ፍቃደኝነት ስራዎች ለመሙላት የሚለዉን ሀሳብ ለመደገፍ ነዉ በጎ ፍቃድ አገልግሎቱ ላይ የምንሰማራዉ ብሏል፡፡

የበጎ ፍቃድ ስራዎቹን ባለሞያዎች እንዲያግዟቸዉ አርቲስቶቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *