loading
በአክሱም ጽዮን ለሀገራችን ሰላም ምህላ እየተደረገ ነዉ፡፡

በምህላዉ ከ50 ሺህ ሰዉ በላይ እየታደመ እንደሚገኝ በአክሱም ጺዮን የስብከተ ወንጌል ምክትል ሀላፊ በኩረ ትጉሃን ስቡህ ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡
ከነሐሴ አንድ ጀምሮ የፍልሰታ ጾምን አስመልክቶ የተጀመረዉ ምህላ አስከ ጾሙ ማብቂያ ድረስ ይቀጥላል፡፡፡በአክሱም ፂዮን ሁልጊዜ ወር በገባ ከ1-7 ባሉት ቀናት ምህላ የሚደረግ ሲሆን የፍልሰታ ፆም አስመልክቶ ደግሞ እስከ ጾም ፍቺ ምህላ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በኩረ ትጉሃን የዘንድሮዉን ምህላ ከበፊቱ የሚለየዉ በአንዳነድ የሀገራችን አካባቢዎች የተከሰተዉ ግጭት
እንዲረገብ ህጻናትም ሳይቀር የተሳተፉበት በመሆኑ ነዉ ብለዋል፡፡
ምህላዉ ከለሊቱ 10 ሰዓት እስከ ጠዋት 1 ሰዓት የሚካሄድ ሲሆን ምዕመኑም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ጀምሮ ለምህላዉ ቦታ በመያዝ ምህላዉን እያካሄደነዉ ብለዋል፡፡
በምህላዉ ለመሳተፍ ከሀገር ዉጭና ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሰዎች እንዳሉ የተናገሩት በኩረ ትጉሃን፤ በምህላዉ ታቦት እንዲወጣ ይደረግና ታቦቱንም በመያዝ ከቤተክርስትያኒቱ በተክለሃይማኖት አድርገዉ በፒያሳ በመዞር ወደ ቤተክርስትያንዋ ታቦቱን በማስገባት ምህላዉ እንደሚካሄድ ሰምተናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *