loading
አማርኛ ቋንቋን የአፍሪካ ኅብረት የስራ ቋንቋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2014 አማርኛ ቋንቋን የአፍሪካ ኅብረት የስራ ቋንቋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ፤ በመዲናችን የተካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ስኬታማ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡ ኅብረቱ የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከል ተቋምን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መወያየቱንም ተናግረዋል፡፡


የኮቪድ- 19 መፍትሄዎቸ፣ የሰላምና የጸጥታ ችግር፣ የመንግስት ለውጦቸ እና የመፈንቅለ መንግስት ጉዳዮች አሳሳቢ ሆነው መታየታቸውን ጠቁመው፥ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ሌላኛው አጀንዳ እንደነበር ገልጸዋል። የአፍሪካ የፋይናንስና የእርስ በእርስ ንግድን ማጠናከር የሚለውም ጉዳይ ውይይት የተደረገበት አጀንዳ
ነበር ብለዋል፡፡


አማርኛ ቋንቋን የአፍሪካ ኅብረት የስራ ቋንቋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ዲና፥ ስዋሂሊኛ የኅብረቱ አንዱ የስራ ቋንቋ ሆኗል ብለዋል።
ኢትዮጵያዊቷ ሴት የኔፓድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው መመረጣቸው ትልቅ ስኬት መሆኑንም አመላክተዋል በመግለጫቸው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *