loading
የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት በሥራው ላይ ችግር አጋጠመው::

አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014  የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በባቡር መስመር ላይ በሚፈጠሩ ችግሮች ምክንያት ሥራው መስተጓጎሉን አስታወቀ። የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ትራንስፖርት ዘርፍ በማቀላጠፍ የጀርባ አጥንት ይሆናል ተብሎ በሚታመንበት በኢትዮ ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ደህንነት ዙሪያ በቢሾፍቱ ከተማ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው። በውይይቱ ላይ የሚመለከታቸው አካላት እና በመስመሩ አካባቢ ያሉ የዞንና የወረዳ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ዳይሬክተር ኢንጅነር ጥላሁን ሰርካ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎቱ ላይ የሚከሰቱ ችግሮች እንዳይከሰቱ ህብረተሰቡ ከሃዲዱ መስመር ሊጠበቁ ፥ እንስሳትንም ሊጠብቁ ይገባል ብለዋል። ባለፉት ዓመታት በባቡር ትራንስፖርቱ ላይ ከፍተኛ የስርቆት፥ የጸጥታ እና የአደጋ ችግሮች ሲያጋጥሙ እንደነበርም አንስተዋል።

በሰፊው ይስተዋል የነበረው ይህ ችግር በብዙ አካባቢዎች መሻሻል ቢታይበትም በባቡሩ መተላለፊያ መስመሮች በሚገኙት በአዳማ ፥ በቢሾፍቱ እና ፊጦ ባሉ መስመሮች መካከል ችግሩ አሁንም እንዳለ ገልጸዋል። በአንድ ጉዞ ብቻ ከ2 ሺህ 100 ቶን በላይ እቃ በማጓጓዝ የኢትዮጵያን የወጪ እና ገቢ ትራንስፖርት
ለማቀላጠፍ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ተብሎ የሚታመንበት የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት፥ አሁን ላይ በሚያጋጥሙት የተለያዩ ችግሮች ምክንያት መስተጓጎል እያጋጠመው መሆኑን ፋና ዘግቧል::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *