loading
አይኦኤም ለ 1ነጥብ 8 ሚሊዮን ተፈናቃዮች መጠለያ ለመስጠት 21 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል አለ፡፡

አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014  አይኦኤም ለ 1ነጥብ 8 ሚሊዮን ተፈናቃዮች መጠለያ ለመስጠት 21 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል አለ፡፡ ከትግራይ፣ አማራ እና ሶማሌ ክልሎች የተፈናቀሉ እና በአሁኑ ወቅት በመጠለያ ጣቢያዎች እንዲሁም በሰዎች ቤት ተጠግተው ለሚኖሩ ዜጎች መጠለያ ለማዘጋጀት የሚያስፈልገው ወጪ 21 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ድርጅት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በፌደራል መንግሥት እና በሽብር ቡድኑ መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ የተፈናቀሉ ከ 233ሺህ በላይ ሰዎች በ53 መጠለያዎች ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ እነዚህ መጠለያዎች ከዚህ ቀደም ትምህርት ቤት የነበሩ ሲሆኑ አሁን ወደ ተፈናቃዮች ማቆያነት ተለውጠው አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች ሜዳ ላይ ለመተኛት መገደዳችዉን የአይኦኤም ኢትዮጵያ መረጃ ይጠቁማል፡፡ በመጠለያ ጣቢዎቹ ምግብ፣ዉሃ፣ ህክምና አገልገሎት እና ሌሎችም መሠረታዊ አቅርቦቶች ለሟሟላት የሚውለው በጀት እየተገባደደ እንደሚገኝ ድርጅቱ መግለጹን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *