loading
የሕብረ ብሔራዊ አንድነት መገንቢያ መሠረቱ አብሮና ተባብሮ ለመኖር መወሰን ነው ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2014 የሕብረ ብሔራዊ አንድነት መገንቢያ መሠረቱ አብሮና ተባብሮ ለመኖር መወሰን ነው ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡ አቶ አገኘው ተሻገር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ሆነው መሾማቻን ተከተሎ ባደረጉት ንግግር ያሳለፍናቸው ጥቂት የለውጥ ዓመታት የአገራችንን ዕድገትና ሰላም በማይፈልጉ በሕዝባችን ላይ ሞትና አካል መጉደል፣ ንብረት መውደምና መፈናቀል፣ ስጋትና መጠራጠር በሰፊው የታየበት፣ በአንጻሩ ደግሞ በዚህ ክፉ ጊዜ ያልከዱን መልካም አሳቢዎቻችንና ታሪካዊ ወዳጆቻችን

በዓለም የፍርድ አደባባይ ላይ ኢትዮጵያ ስለምትከተለው የብልጽግና መንገድ ጥብቅና የቆሙበት ነበር ብለዋል፡፡ በውጭም በአገር ውስጥም ያሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው አገራቸውን ለማሻገር ሌት ከቀን የታተሩበት ነበር ያሉት አቶ አገኘሁ፤ በሕዝብ የተመረጠው መንግሥትም በየደረጃው ባካሄደው የመንግሥት ምሥረታ ውስጥ ሁሉንም አካታች በሆነ መንገድ አስፈፃሚ አካላትን ለማዋቀር ጥረት እንደተደረገም አስታውሷል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ አስቸጋሪና የፈተና ወቅት የማይሳኩ የሚመስሉ ታላላቅ ድሎች ያስመዘገብንባቸውና እንደ አገርም ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት አጋጣሚ ነበር ማለት ይቻላል ብለዋል አቶ አገኘው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *