loading
በሳዑዲ አረቢያ እስርቤቶች የሚገኙ ኢትጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013 በሳዑዲ አረቢያ የተለያዩ ማቆያ ማእከላትና እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ተገለፀ፡፡ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት በሪያድ የሚገኘነውን የኢትዮጵያ ኤምባሲን ጠቅሶ በፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር በመቀናጀት በሳምንት ሶሶት በረራዎችን በማድርግ በሳዑዲ አረቢያ የተለያዩ ማቆያ ማዕከላትና እስር ቤቶች የሚገኙ ዜጎችን ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ለአገራቸው እንዲበቁ ይደረጋል ብሏል፡፡ በሳምንት ሶስት በረራዎች በማድረግ በየሳምንቱ አንድ ሺህ ዜጎችን ወደ አገር እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን፣ በዚህ የማስመለስ ሥራ ቅድሚያ ወደ አገር እንዲገቡ የሚደረጉት ሴቶች፣ ህጻናት፣ ታማሚ እና አረጋውያን ዜጎቻችን ይሆናሉ ተብሏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *