loading
ባለፉት ሁለት ቀናት በኢትዮጵያ በኮቪድ- 19 ምክንያት 20 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 ባለፉት ሁለት ቀናት በኢትዮጵያ በኮቪድ- 19 ምክንያት 20 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ፡፡የጤና ሚኒስቴር የ24 ሰዓታት የኮቪድ-19 መረጃ እንደሚያመለክተው በተከታታይ በሁለት ቀናትውስጥ 20 ሰዎች ህይወታቸውን በቫይረሱ አጥተዋል፡፡ ቫይረሱ ሀገራችን ከገባ ጀምሮም ህይወታቸው በቫይረሱ ያለፈ ሰዎች ቁጥር 4 ሺህ 4 መቶ 50 ደርሷል፡፡የጽኑ ህሙማንም ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን ፤ የ24 ሰዓታቱ ሪፖርት የጽኑ ህሙማን ቁጥርም 342 መድረሱን አመልክቷል፡፡

ኮቪድ- 19 ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ 3 ሚሊዮን 89 ሺህ 301 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ያደረጉ ሲሆን ፤ ከነዚህ ዉስጥ 286 ሺህ 286 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ፡፡ ከነዚህ ዉስጥ 264 ሺህ 872 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን ፤ በአሁኑ ግዜ ቫይረሱ ያለባቸው 16 ሺህ 962 መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡ ክትባቱ በኢትዮጵያ መሰጠት ከተጀመረበት ግዜ አንስቶ እስካሁንም 2 ሚሊዮን 297 ሺህ 485 ሰዎች መከተባቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *