loading
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት ተረከበች::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12፣ 2013 አሜሪካ ለኢትዮጵያ የለገሰችውን 453 ሺህ 600 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ጤና ሚኒስቴር ተረከበ:: በአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የተደረገው ድጋፍ  ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተባለው  ክትባት ሲሆን ቃል ከገባችው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶዝ 453 ሺህ 600 ዶዙ አዲስ አበባ  ገብቷል።

ድጋፉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ተረክበዋል።
አሜሪካ ለኢትዮጰያ ለመለገስ ቃል ከገባችው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ ከትባት ውስጥ 453 ሺህ 600 ዶዙን ነዉ ዛሬ ያስረከበችዉ

አሜሪካ በሚቀጥሉት ሳምንታት 25 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ19 ክትባት ለ49 የአፍሪካ አገራት ድጋፍ እ ነደምታደርግ ታውቋል። በመጀመሪያው ዙር 1 ሚሊዮን ዶዝ ለቡርኪናፋሶ፣ ለጅቡቲ እና ኢትዮጵያ ተደራሽ ይሆናል ኢትዮጵያ ቫይረሱን ለመከላከል እስካሁን ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የአስተራዘኒክ እና ሲኖፋርም የተባሉ ክትባቶችን መስጠቷ ይታወቃል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *