loading
የሲሚንቶ ግብይትን ለመቆጣጣር የወጣው መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ ተነሳ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 7፣ 2013  የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሲሚንቶ ግብይትን ለመቆጣጣር የወጣው መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ መነሳቱን አስታወቀ፡፡ በዚህ መሰረት የግብይት ሂደቱ በነፃ ገበያ መርህ እንዲከናወን ተወስኗል ብሏል። የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ እቃዎች ዋጋ ጥናት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት፥ በሲሚንቶ ግብይት ላይ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት ሲባል ወደ ቀደመ የነፃ ገበያ አሰራር ተመልሰናል ብለዋል።

በዋነኛነትም የክረምት ወቅት የሲሚንቶ ፍላጎት ስለሚቀንስ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች ሲሚንቶ ባልተጋነነ ዋጋ እንዲሸጡ የበኩላቸውን እንደሚያደርጉ ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውሰዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም በአቅርቦቱ ላይ ያለውን ክፍተት የፋብሪካዎችን አቅም በማጠናከር ለመሙላትና ከውጪ ለማስገባት መንግስት መወሰኑን ገልጸዋል ኢዚአ ዘግቧል። የፋብሪካዎች የምርት መሸጫ ዋጋም ከሚኒስቴሩ ጋር በመነጋገር በተጠና እንዲሆን ስምምነት
ተደርሷልም ነው ያሉት። አሰራሩም በነፃ ገበያ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቀጥል መወሰኑንም ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *