loading
ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት ከነገ ጀምሮ በጤና ተቋማት ይሰጣል-ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6፣ 2013 ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት ከነገ ጀምሮ በጤና ተቋማት ይሰጣል-ጤና ሚኒስቴር

በአዲስ አበባ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ባሉ የጤና ተቋማት ለኮሮና ቫይስ ተጋለጭ የሆኑ የህበረተሰብ ክፍሎች እንዲከተቡ ጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ
በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የኮቪድ ክትባት ከወሰዱ ሶስት ወር የሞላቸው ዜጎች ከነገ ጀምሮ እንደሚከተቡ እና በክልሎች ደግሞ ክትባቱን ከሐምሌ 9 ጀምሮ መውሰድ እንደሚቻል ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ጨምሮ የባንክ፣ የገቢዎችና ጉምሩክ፣ የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የህፃናት ማቆያና መደበኛ የኮሌጅ መምህራን እንዲሁም ሌሎች የተመረጡ ተቋማት ሰራተኞች መታወቂያቸውን በማሳየት ክትባቱን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ወስደው ሁለተኛውን በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ሰዎች ከነገ ጀምሮ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የጤና ተቋም መከተብ እንደሚችሉ ዶክተር ሊያ ገልፀዋል፡፡
የጤና ሚኒስትሯ አክለውም በክልል ከተሞች ከዓርብ ሃምሌ 9 ቀን ጀምሮ ክትባቱ እንደሚሰጥ ነው ያብራሩት፡፡
በሀገራችን አልፋና ቤታ የተባሉ የኮቪድ-19 ዝርያዎች መኖራቸው የተረጋገጠ ሲሆን ዴልታ የተሰኘው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በሀገራችን ስለመከሰቱ ጥናት እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡
በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ካለው ስርጭት አኳያ በኢትዮጵያም ሊጠበቅ እንደሚችል ዶክተር ሊያ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ እስከ ዛሬ ድረስ 277 ሺህ ዜጎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 4 ሺህ 343 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *