loading
በሱዳን የተከሰተው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የህዝባዊ አመፅ ስጋት ፈጥሯል ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2013 በሱዳን የተከሰተው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የህዝባዊ አመፅ ስጋት ፈጥሯል ::ሱዳን ድጎማ ማንሳቷን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በሊትር የ140 የሱዳን ፓውንድ ጭማሪ ማሳየቱ ተሰማ፡፡ ካርቱም የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት ምክር ተቀብላ የነዳጅ ድጎማ ማንሳቷ ያስከተለው የዋጋ ንረት
ህዝባዊ ከባድ አመፅ እንዳይቀሰቀስ ስጋት ላይ ጥሏታል ነው የተባለው፡፡ በዚህም የተነሳ ለአልበሽር ከመንበራቸው መወገድ መነሻ ምክንያት የሆነው የዳቦ ዋጋ ጭማሪ በነዳጅ ተቀይሮ አዲሱ አስተዳደር ላይ አነጣጥሯል፡፡

ሱዳን ከወሰደቻቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መካከል አንዱ የሆነው የነዳጅ ድጎማን ማንሳት አሁን ላይ በ150 የሱዳን ፓውንድ ይሸጥ የነበረውን አንድ ሊትር ነዳጅ ወደ 290 ፓውንድ እንዲያሻቅብ አድርጎታል፡፡ ሱዳን የዚህ አይነት የኢኮኖሚ መሻሻያ ግዴታ ውስጥ የገባቸው ያለባትን የ49 ቢሊዮን ዩሮ ብድር ለማቃለል ከሚያዟት መንገዶች አንዱ መሆኑ ስለተነገራት ነው፡፡

በአንድ ጊዜ በ128 በመቶ ጭማሪ ያሳየው የነዳጅ ዋጋ በቋፍ ላይ ነበረውን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ይበልጥ አደጋ ውስጥ ከቶታል ተብሏል፡፡ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በሃይል ከስልጣን ተወግደው የሽግግር ምክር ቤቱ ሀገሪቱን መምራት ከጀመረ ወዲህ የኑሮ ውድነቱ በከፍተኛ መጠን መባባሱ ነው የሚነገረው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *