loading
ኮሚሽኑ የፀረ ሙስና ትግሉን ላገዙ ግለሰቦችና ተቋማት እውቅና ሰጠ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2013  የፌዴራል ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የፀረ ሙስና ትግሉን አግዘዋል ላላቸው ለ10 ተቋማት፣ ለ286 ግለሰቦች እና ለ229 ተማሪዎች እውቅና ሰጠ። እውቅና የተሰጣቸው ተማሪዎችም በሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ላይ በተዘጋጁ ጥያቄዎች አሽናፊ ለሆኑ ለዘጠነኛ እና አስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች ነው።

“ኮሚሽኑ ትኩረት ለትውልድ ሥነ ምግባር ግንባታ” በሚል መሪ መልእክት 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው። ሽልማት የተበረከተላቸው ተቋማት እና ግለሰቦች ሙስናንና ብልሹ አሠራርን በመታገል ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ያበረከቱ ናቸው። የፌዴራል የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ፀጋ አራጌ ሙስናን እና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የዜጎች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ ሽልማቱም መሥረቅ እና ማጭበርበር ለሀገር እድገት ነቀርሳ እና ከፍተኛ የሞራል ዝቅጠት የሚያመጣ መሆኑን ለማመላከት የተካሄደ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *