loading
ኢትዮጵያውያን የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም በያሉበት ሆነው ድምጻቸውን የሚያሰሙበት መርሃ ግብር ዛሬ ይካሄዳል::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2013 ኢትዮጵያውያን የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም በያሉበት ሆነው ድምጻቸውን የሚያሰሙበት መርሃ ግብር ዛሬ ይካሄዳል:: በፕሮግራሙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ አገራትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ" በሚል መሪ ሐሳብ በያሉበት ሆነው ለአንድ ሰዓት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ፡፡ ከመልእክት ከማስተላለፊያ መንገዶች አንዱ ጣልቃ ገብነቱን የሚቃወም የዲጂታል ፊርማ ማሰባሰብ መሆኑም ታውቋል፡፡

መርሃ-ግብሩ ብሔራዊ ክብር በሕብር የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን ንቅናቄውን ያዘጋጁት የማህበረሰብ አንቂዎች፣ አርቲስቶች፣ ሲቪክ ማህበራትና ታዋቂ ግለሰቦች ናቸው። መርሃ-ግብሩ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ አገራትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም አጋርነታቸውን የሚያዩበት ነው፡፡

በአንድ ሰዓቱ መርሃ-ግብር ብሔራዊ ክብር በሕብር እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ የውጭ አገራት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማክበር አለባቸው የውጭ አገራት ጣልቃ ገብነታቸውን ያቁሙ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ከማከናወን የሚያግደን ሃይል የለም  እና ምርጫውን ማካሄድ የውስጥ ጉዳያችን ነው:: የሚሉ ሐሳቦችን ያዘሉ መልዕክቶች ይተላለፋሉ።

ዜጎች የማህበራዊ ትስስር ገጾችን በመጠቀም እንዲሁም በአደባባይ በመውጣት መልዕክታቸውን ማስተላለፍ ይችላሉ ተብሏል፡፡ ንቅናቄው የታለመለትን ግብ እንዲመታ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣም  ጥሪ ተላልፏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *