loading
አውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎቼን ወደ ኢትዮጵያ እልካለሁ ማለቱ ተሰማ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2013 ህብረቱ ከአሁን ቀደም ምርጫውን ለመታዘብ ያስቀመጣቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጋፉ ቅድመ ሁኔታዎች በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት አላገኙም ነበር፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ሳምንታዊ መግለጫ ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ሩሲያ፣ አሜሪካና ሌሎች ሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ባለሙያዎቻቸውን እንደሚልኩ አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመግለጫው የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብ፣ የሰብዓዊ ቀውስን እንዲሁም 6ተኛ ሀገራዊ ምርጫን በተመለከተ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሰፊ ገለጻ ተደርገጎላቸዋል ብሏል፡፡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ማብራሪያ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ከየሀገራቱ መሪወች ጋር ውይይት እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡ በተለይ ም/ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጋር ያረጉት ውይይትና ሀገሪቱ የህብረቱ መሪ እያለች የአፍሪካ ችግር በአፍሪካዊያን እንዲፈታ
ስለተጫወተችው ሚና አስታውሰዋል፡፡

የህዳሴ ግድብ ድርድር ጉደዳይ በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር እንዲፈታ ኮሞሮስ ገንቢ ሚና እንድትጫወት ጥሪ መቅረቡም ተገልጿል። ቀደም ሲል ከግብፅና ሱዳን ጋር ውይትት አድርገው ወደ አዲስ አበባ የመጡት የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርና የሪፓብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ሺሴኬዲ ድርድሩን ያስቀጥላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *